Get Mystery Box with random crypto!

' ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን ' - የዳዋ ዞን አስተዳደር በሶማሌ ክልል ዳዋ | Ethiopian News Hub 🇪🇹

" ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን " - የዳዋ ዞን አስተዳደር

በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ባጋጠመ ድርቅ በርካታ እንስሳት የሞቱ ሲሆን  የሰዎች ሕይወትም አደጋ ላይ መውደቁ ተገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር ያለው ሁኔታ ከአቅም በላይ መሆኑን አስታውቋል።

ከኦሮሚያ የቦረና ዞን ጋር የሚዋሰነው ዞኑ፣ በድርቅ የተነሳ ከሚሞቱ እንስሳት አልፎ ሰዎች #ለሆስፒታል እየተዳረጉ መሆኑን ገልጿል፡፡

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

" የድርቁ ጉዳት ከዞኑ አቅም በላይ ነው።

ዞናችን ከቦረና ጋር በሁለት ወረዳዎች በኩል ይዋሰናል፡፡ ወደ 700 ሺሕ የሚጠጋ አርብቶ አደር ነዋሪ ያለው ሲሆን፣ ለ3 ተከታታይ ዓመታት የደረሰው ድርቅ ከብቱን በሙሉ ጨርሶበታል።

በክልሉ አደጋ ሥጋት ቢሮና በተለያዩ የዕርዳታ ድርጅቶች ርብርብ ዘንድሮ ለድርቁ ተጎጂዎች ዕርዳታ እየቀረበ ነው ይሁን እንጂ ዕርዳታው በቂ አይደለም። ችግሩም ከአቅም በላይ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ለሚገኘው ለአጎራባቻችን ቦረና ዞን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንዳለው ሁሉ፣ ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን። "

ዳዋ ዞን በሥሩ ሞያሌ፣ ሙባረክ፣ ካደዱማና ሁደት የተባሉ አራት ወረዳዎች ያሉት ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ባለማግኘቱ ትልቁ የዳዋ ወንዝ ጭምር ደርቋል።

ድርቅ የሚቋቋሙ ግመሎችን ጨምሮ ከብቶችና ፍየሎች በከፍተኛ ቁጥር ማለቃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።