Get Mystery Box with random crypto!

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ! የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲሱ የትምህርትና ሥ | Ethiopian News Hub 🇪🇹

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ!

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እና በ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዳስታወቁት፤ሚኒስቴሩ የሥራ ገበያውን እና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መቁረጫ ነጥብን እንዳዘጋጀም ነው የጠቆሙት፡፡

በዚህም መሰረት ከቴክኒክና ሙያ ውጪ ባሉ ማዕከላት የሚስተናገዱትን ሳይጨምር በሥልጠና ዘመኑ 608,666 የሚሆኑ ሰልጣኞች ወደ ቴክኒክና ሙያ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትሯ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው፤ በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች ግን የሚስተናገዱት በ 2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል፡፡

የ2015 ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ላይ ተያይዟል።