Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian News Hub 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewshubet — Ethiopian News Hub 🇪🇹 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewshubet — Ethiopian News Hub 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ethionewshubet
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ ቴሌግራም ቻናላችን በደህና መጡ
👉በአለም ላይ ያሉ አዳዲስ ክስተቶችን
👉ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው መድረሻ! ልምድ ባካበቱ ጋዜጠኞች
👉አዳዲስ ዜናዎችን
👉ጥልቅ ትንታኔዎችን እና አስተያየቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ ያለመታከት ይሰራል። በኛ ቻናል ምንም አያመልጥዎትም - ከፖለቲካ እስከ ንግድ ፣ ከመዝናኛ እስከ ሳይንስ ያለውን ሁሉ አንሸፍናለን

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-26 22:01:31
ማንችስተር ዩናይትድ ሻምፒዮን ሆኗል

በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ኒውካስል ዩናይትድን 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
68 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 19:55:21
#MoE

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር።


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444
78 viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 15:43:08
ከህዝብ ዕይታ ርቆ የነበረው የባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ!!

ለወራት ከህዝብ ዕይታ ርቆ የነበረው እና ድምፁ ጠፍቶ የሰነበተው እስክንድር ነጋ ቡሬ ላይ ተገኝቶ ወደ ባህር ዳር የተወሰደ ሲሆን በአጠቃላይ ጉዳዮች ለማጣራት በማረፊያ ቤት እንደሚገኝ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
#ዳጉ_ጆርናል
74 views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 22:12:27
የእነ አባ ሳዊሮስ እግድ ተነሳ።

የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ እግድ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በቅርቡ የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ ፦

- የአባ ሳዊሮስ፣
- የአባ ኤዎስጣቴዎስ
- የአባ ዜና ማርቆስ #ዕግድ_መነሳቱን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቀሪዎቹ 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ተገልጿል።

#ተሚማ
74 views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 12:22:05
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያን ለማዉገዝ በተደረገ ስብሰባ ኢትዮጲያን ጨምሮ 15 የአፍሪካ ሀገራት ድምፀ ተአቅቦ አደረጉ

በትላንትናዉ እለት በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከአንድ አመት ገደማ በፊት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ የሚያወግዝ ውሳኔን 15 የአፍሪካ ሀገራት ድምፁን ተአቅቦ ሲያደርጉ 28 ሀገራት ደግፈዋል።የውሳኔ ሃሳቡ ወታደሮቹ ከዩክሬን እንዲወጡ እና ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቅ ነዉ፡፡

መለኪያው በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ሳይሆን ፖለቲካዊ ክብደትን ይይዛል።ዉሳኔዉ በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ሳይሆን ፖለቲካዊ ክብደት ያለዉ ነዉ፡፡በዉሳኔ ላይ በተሰጠዉ ድምጽ 141 የዓለም ሀገራት ሩሲን ሲያወግዙ፣ በ32 ድምፀ ተአቅቦ እና በሰባት ድምጽ ተቃውሞ ቀርቧል።ድምጸ ተአቅቦ ካደረጉ ሀገራት መካከል ግማሽ ያህሉ ከአፍሪካ ናቸዉ፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ብሩንዲ፣ ናሚቢያ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ጋቦን፣ ጊኒ፣ ሞዛምቢክ፣ ሱዳን፣ ቶጎ፣ ኡጋንዳ እና ዚምባብዌ ድምጽ ተአቅቦ ያደረጉ ሀገራት ናቸዉ፡፡ኤርትራ እና ማሊ ዉሳኔዉን የተቃወሙ ብቸኛ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።ሴኔጋል፣ቡርኪናፋሶ፣ካሜሩን፣ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ኤስዋቲኒ እና ጊኒ ቢሳው በምርጫው አልተሳተፉም።

ናይጄሪያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ግብፅ፣ ጋና እና ኬንያ ሩሲያን ከሚያወግዘዉ ድምጸ ዉሳኔዉን ከደገፉት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ይገኙበታል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የውሳኔ ሃሳቡን በደስታ መቀበላቸዉን በማንሳት ይህም የአለም አቀፍ ድጋፍ ትልቅ ምልክት ነው ብለዋል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
70 viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ