Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ በአንድ ግቢው ውስጥ ጨቅላ ህጻን በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ተጥሎ ህይወቱ አልፎ ተገኘ | Ethiopian News Hub 🇪🇹

በአዲስ አበባ በአንድ ግቢው ውስጥ ጨቅላ ህጻን በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ተጥሎ ህይወቱ አልፎ ተገኘ

ከ15 ቀናት በፊት በዚሁ ግቢ ውስጥ መንታ ህጻናት ህይወታቸዉ አልፎ ተገኝቷል


ትላንት የካቲት 19 ከምሽት 5:43 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታዉ አባጃሌ በተባለዉ አካባቢ ጨቅላ ህጻን በመጸዳጃ ቤት ተጥሎ ህይወት አልፎ መገኘቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል ።

የህጻኑን አስከሬን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከመጸዳጃ ቤት ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብሰራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ህጻኑ በተጠለበት በዚሁ ግቢ ዉስጥ ከ15 ቀናት በፊት ሁለት መንታ ህጻናት ህይወታቸዉ አልፎ በመገኘቱ የህጻናቱን ወላጅ እናት በቁጥጥር ስር አዉሎ ፓሊስ እያጣራ ባለበት ሁኔታ ይህ ክስተት ማጋጠሙንም አቶ ንጋቱ ጨምረው ነግረውናል።

ትላንት ምሽት በመጸዳጃ ቤት ተጥሎ የተገኘዉን ጨቅላ ህጻን የማን እንደሆነ ጉዳይም ፖሊስ እያጣራ ይገኛል።