Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiokushna — Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiokushna — Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂
የሰርጥ አድራሻ: @ethiokushna
ምድቦች: ምግብ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.20K
የሰርጥ መግለጫ

Food world
@hawia3. Inbox
የተለያዩ የሀገር ውስጥ ና የውጪ ሀገር የምግብ አዘገጃጀት🍱🥪🌮🥞🍔🍟
እስካፌር ለምኔ የሚያስብሉ ምርጥ ሙያዎችን ያገኙበታል👨🏼‍🍳👩‍🍳👩‍🍳👩‍🍳👩‍🍳

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-26 20:25:03
ሰላም የኦዴሊያ ቤተሠቦች አዳዲስ እና ውብ ቱታዎችን በቅናሽ ዋጋ አዘጋጅተናል ይዘዙን ::
ለቤተሰብ እንዲሁም ለ ካፕሎች

Medium large በፈለጉት ሳይዝና ከለር አለን
ያሉበት ድረስ እናደርሳለን
@hawia3
@bezu99
@merryTF
806 viewsSamri Asefa, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 19:35:32 Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና pinned «​​የሽምብራ እና ቲማቲም ሾርባ ለረመዳን ( chickpea and tomato soup for Ramadan ) የሚያስፈልጉን • 3 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት • 2 የሽይ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት • 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል • 1 ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ • 2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ድምብላል ( coriander) • 1/2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ከሙን ( cumin) • 1/2 የሻይ…»
16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 21:28:24 ​​የስትሮቤሪ እይስክሬም ( strawberry ice cream )

የሚያስፈልጉን

• 1 ኩባያ (236.5ml) ወተት
• 2 ኩባያ (473.5 ml) ክሬም
•1 ኩባያ (200ግራም) ነጭ ስኳር (granulated sugar)
• 1/4 የሻይ ማንኪያ ጨው (sea salt)
• 2 የሻይ ማንኪያ የቫኒላ ፈሳሽ (vanilla)
• 2 ኩባያ (200ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ስትሮበሪ

አሰራር

1- በጎድጓዳ ስህን ስትሮበሪ እና ስኳር ቀላቅሎ ከ 15-20 ደቂቃ ማስቀመጥ
2- በመቀጠል የስትሮበሪውን ቅልቅል መፍጨት
3-በሌላ ጎድጓዳ ሰሀን የስትሮበሪውን ቅልቅል, ክሬም,ወተት,ጨው እና ቫኒላውን ጨምሮ በሚገባ ከቀላቀሉ በሁዋላ የአይስክሬም ማሽን ዉስጥ ጨምሮ ከ 25-30 ደቂቃ ማቆየት
4- በመጨረሻም በረዶ ቤት (freezer)በሚገባ እቃ ውስጥ በመጨመር መጠቀም
1.0K viewsSamri Asefa, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 21:28:24 ​​ብራውኒ ( Brownie)

የሚያስፈልጉን

•1/2 ኩባያ የገበታ ቅቤ
•1 ኩባያ ነጭ ስኳር
•2 እንቁላል
•1 የሻይ ማንኪያ የቫኒላ ጠብታ
•1/3 ኩባያ ካክዋ ፓውደር
•1/2 ኩባያ የፉርኖ ዱቄት
•1/4 የሻይ ማንኪያ ጨው
•1/4 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር

ከላይ ለሚቀባ ( frosting)

•3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
•3 የሾርባ ማንኪያ ካክዋ ፓውደር (cocoa powder)
•1 የሾርባ ማንኪያ ማር
•1 የሻይ ማንኪያ የቫኒላ ጠብታ ( vanilla essence)
•1 ኩባያ የተፈጨ ስኳር

አሰራር

•ኦቨን 350df ውይም 175 dc ላይ ማሞቅ
•የገበታ ቅቤውን ከፍ ባለ እቃ ካቅለጡ በሁዋላ ስኳር,እንቁላል እና ቫኒልውን መቀላቀል
•በመቀጠል ኮክዋ ፓውደር,ፉርኖ ዱቄት,ጨው እና ቤኪንግ ፓውደር ጨምሮ በሚገባ መቀላቀል
•የኬኩን ቅልቅል (ሊጥ) ኦቨን ውስጥ በሚገባ ትሪ ላይ ገልብጦ ከ25-30 ደቂቅ አብስሎ ማውጣት

ከላይ የሚቀብውን (frosting) ለመስራት

•በጎድጉዋዳ እቃ የገበታ ቅቤ,ኮክዋ ፓውደር,ማር,ቫኒላ እና የተፈጨ ስኳር ጨምሮ በሚገባ መቀላቀል

• በመጨረሻም የጋገርነው ብራውኒ ኬክ ላይ frosting ቀብቶ ቆራርጦ ማቅረብ
696 viewsSamri Asefa, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 21:28:24 ​​ፍሩት ሳላድ ( Fruit salad )

• 1/2 ኩባያ የተከተፈ አናናስ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ እንጆሪ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ የወይን ፍሬ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ ማንጎ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ ሙዝ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ አፕል
• 1 የሾርባ ማንኪያ የሚሆን የናና ቅጠል (mint)

- 1 የሾርባ ማንኪያ ወለላ ማር
- 1/2 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ቆዳ ፍቅፋቂ
-2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
- 1/2 የሻይ ማንኪያ የቀረፋ ፓውደር cinnamon powder

አሰራር

• ከላይ የተዘረዘሩትን ፍራፍሬወች በጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ መቀላቀል
• በሌላ አነስተኛ ጎድጓዳ እቃ ውስጥ ማር , ቀረፋ ፓውደር,የሎሚ ቆዳ ፍቅፋቂውን እና የሎሚ ጭማቂውን ቀላቅሎ የተዘጋጀው ፍራፍሬ ላይ ጨምሮ በደምብ በመቀላቀል የናና ቅጠል ነስንሶ ማቅረብ

ለተጨማሪ ጣእም 1/2 ኩባያ የሚሆን የብርቱካን ጁስ መጨምር
ከ2-3 ሰአት አቀዝቅዞ ማቅረብ
561 viewsSamri Asefa, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 21:28:24 ​​የቂንጬ ሰላጣ
( Bulgur wheat salad )

የሚያስፈልገን

• ግማሽ ኩባያ የስንዴ ቂንጨ
• 2 መካከለኛ ኩከምበር በደቃቁ የተከተፈ
• 3 ቲማቲም በደቃቁ የተከተፈ
• 1 ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
• 4 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ የፐርሲል ቅጠል
• 4 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ የናና ቅጠል
• 3-4 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
• 3-4 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት
• ጨው

አሰራር

• የቂንጬ ስንዴውን ከቀቀሉ በሁዋላ ማቀዝቀዝ
• በጎድጓዳ እቃ ውስጥ የተቀቀለውን ቂንጨ ,ቲማቲም,ኩከምበር,ሽንኩርት,ፐርሲል እና የናና ቅጠሉን በሚገባ መቀላቀል
• በአነስተኛ ጎድጓዳ እቃ ውስጥ የሎሚ ጭማቂ,ዘይት እና ጨው ከቀላቀሉ በሁዋላ ሰላጣው ውስጥ ጨምሮ በሚገባ ለውሶ ማቅርብ::
616 viewsSamri Asefa, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 21:28:24 ​​ሳልሳ (tomato salsa)

የሚያስፈልጉን

• 6 ከፍ ያለ ቲማቲም የተከተፈ
• 1 ቀይ ሽንኩርት የተከተፈ
• 2 የነጭ ሽንኩርት ፍሬ የተላጠ
• 2 አነስተኛ ቃሪያ
• 2 የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ፐርሲል
• 2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
• 1 የሻይ ማንኪያ ከሙን ፓውደር
• 1 የሻይ ማንኪያ ስኩዋር
• 1/2 የሻይ ማንኪያ ጨው

አሰራር

• ከላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ የምግብ መፍጫ ማሽን ውስጥ ጨምሮ መፍጨት
• ፍሪጅ ካቀዘቀዙ በሁዋላ ከድንች ቺፕስ ጋር ማቅረብ

Tip

ለተጨማሪ ጣእም 1/2 የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ የድንብላል ቅጠል (coriander)እና
1 የሾርባ ማንኪያ አቼቶ (red wine vinegar)
611 viewsSamri Asefa, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 21:28:23 ​​የሽምብራ እና ቲማቲም ሾርባ ለረመዳን
( chickpea and tomato soup for Ramadan )

የሚያስፈልጉን

• 3 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት
• 2 የሽይ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት
• 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል
• 1 ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
• 2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ድምብላል ( coriander)
• 1/2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ከሙን ( cumin)
• 1/2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ ( cinnamon)
• ግማሽ ኪሎ ቲማቲም በትንንሹ የተከተፈ
• 2 ቃሪያ በደቃቁ የተከተፈ
• ጨው እና ቁንዶ በርበሬ
•2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማ
• 2 የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ፐርሲል
• 3 ኩባያ ውሀ
• 2 የታሸገ የቆርቆሮ ሽምብራ

አሰራር

• ዘይት ከጋሉ በሁዋላ ነጭ ሽንኩርት,ዝንጅብል እና ቀይ ሽንኩርት ለ3 ደቂቃ አካባቢ መጥበስ
• ድምብላል,ከሙን እና ቀረፋ ጨምሮ ለተጨማሪ 1 ደቂቃ ማብሰል
• የተከተፈውን ቲማቲም እና ቃሪያ ጨምሮ ከ15-20 ደቂቃ በአነስተኛ የእሳት መጠን ማብሰል
• በመቀጠል ሽምብራውን ጨምሮ ለተጨማሪ 20 ደቂቃ ማብሰል
• በመጨረሻም ፐርሲል እና ጨው ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ለትንሽ ደቂቃ ካበሰሉ በሁዋላ በማውጣት ትኩሱን ማቅረብ
725 viewsSamri Asefa, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 12:23:06
ሰላም ዉድ የ @Unique_fashion1 ቤተሰቦች በአይነቱና በጥራት ልዪ የሆኑ እካዎችን አስገብተናል join ይበሉ ይቀላቀሉን
937 viewsSamri Asefa, 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 06:04:57 ​​chicken cutlets
ቺክን ኮትሌት

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
• 4 የፀዳ ዶሮ መላላጫ (600 ግራም ያህል የሚመዝን)
• 2 የቡና ስኒ (100 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
• 2 የተመታ እንቁላሌ
• 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
• 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
• 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• 4 የቡና ስኒ (200 ግራም) የዳቦ ዱቄት
አዘገጃጀት
1. ሥጋዉን በስጋ መበጥቀጫ መጠፍጠፍ፤
2.ጨዉ፣ቆንዶበርበሬ እና ፉርኖ ድቄቱን መቀላቀል፤
3.ስጋውን በተቀላቀለው ድቄት መለወስ፤
4.የተመታውን እንቁላል ውስጥ እየነከሩ ካወጡ በኅላ የዳቦ ዱቄቱ ላይ መተምተም፤
5.ስጋዉን በቢላዋው ጀርባ አራት ማእዘንቅርፅ መስጠት፤
6.የጋለ ዘይት ወስጥ ቅርፅ በተሰጠው በኩል
1.5K viewsSamri Asefa, 03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ