Get Mystery Box with random crypto!

​​ብራውኒ ( Brownie) የሚያስፈልጉን •1/2 ኩባያ የገበታ ቅቤ •1 ኩባያ ነጭ ስኳር •2 | Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂

​​ብራውኒ ( Brownie)

የሚያስፈልጉን

•1/2 ኩባያ የገበታ ቅቤ
•1 ኩባያ ነጭ ስኳር
•2 እንቁላል
•1 የሻይ ማንኪያ የቫኒላ ጠብታ
•1/3 ኩባያ ካክዋ ፓውደር
•1/2 ኩባያ የፉርኖ ዱቄት
•1/4 የሻይ ማንኪያ ጨው
•1/4 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር

ከላይ ለሚቀባ ( frosting)

•3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
•3 የሾርባ ማንኪያ ካክዋ ፓውደር (cocoa powder)
•1 የሾርባ ማንኪያ ማር
•1 የሻይ ማንኪያ የቫኒላ ጠብታ ( vanilla essence)
•1 ኩባያ የተፈጨ ስኳር

አሰራር

•ኦቨን 350df ውይም 175 dc ላይ ማሞቅ
•የገበታ ቅቤውን ከፍ ባለ እቃ ካቅለጡ በሁዋላ ስኳር,እንቁላል እና ቫኒልውን መቀላቀል
•በመቀጠል ኮክዋ ፓውደር,ፉርኖ ዱቄት,ጨው እና ቤኪንግ ፓውደር ጨምሮ በሚገባ መቀላቀል
•የኬኩን ቅልቅል (ሊጥ) ኦቨን ውስጥ በሚገባ ትሪ ላይ ገልብጦ ከ25-30 ደቂቅ አብስሎ ማውጣት

ከላይ የሚቀብውን (frosting) ለመስራት

•በጎድጉዋዳ እቃ የገበታ ቅቤ,ኮክዋ ፓውደር,ማር,ቫኒላ እና የተፈጨ ስኳር ጨምሮ በሚገባ መቀላቀል

• በመጨረሻም የጋገርነው ብራውኒ ኬክ ላይ frosting ቀብቶ ቆራርጦ ማቅረብ