Get Mystery Box with random crypto!

​​የስትሮቤሪ እይስክሬም ( strawberry ice cream ) የሚያስፈልጉን • 1 ኩባያ | Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂

​​የስትሮቤሪ እይስክሬም ( strawberry ice cream )

የሚያስፈልጉን

• 1 ኩባያ (236.5ml) ወተት
• 2 ኩባያ (473.5 ml) ክሬም
•1 ኩባያ (200ግራም) ነጭ ስኳር (granulated sugar)
• 1/4 የሻይ ማንኪያ ጨው (sea salt)
• 2 የሻይ ማንኪያ የቫኒላ ፈሳሽ (vanilla)
• 2 ኩባያ (200ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ስትሮበሪ

አሰራር

1- በጎድጓዳ ስህን ስትሮበሪ እና ስኳር ቀላቅሎ ከ 15-20 ደቂቃ ማስቀመጥ
2- በመቀጠል የስትሮበሪውን ቅልቅል መፍጨት
3-በሌላ ጎድጓዳ ሰሀን የስትሮበሪውን ቅልቅል, ክሬም,ወተት,ጨው እና ቫኒላውን ጨምሮ በሚገባ ከቀላቀሉ በሁዋላ የአይስክሬም ማሽን ዉስጥ ጨምሮ ከ 25-30 ደቂቃ ማቆየት
4- በመጨረሻም በረዶ ቤት (freezer)በሚገባ እቃ ውስጥ በመጨመር መጠቀም