Get Mystery Box with random crypto!

​​ፍሩት ሳላድ ( Fruit salad ) • 1/2 ኩባያ የተከተፈ አናናስ • 1/2 ኩባያ የ | Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂

​​ፍሩት ሳላድ ( Fruit salad )

• 1/2 ኩባያ የተከተፈ አናናስ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ እንጆሪ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ የወይን ፍሬ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ ማንጎ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ ሙዝ
• 1/2 ኩባያ የተከተፈ አፕል
• 1 የሾርባ ማንኪያ የሚሆን የናና ቅጠል (mint)

- 1 የሾርባ ማንኪያ ወለላ ማር
- 1/2 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ቆዳ ፍቅፋቂ
-2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
- 1/2 የሻይ ማንኪያ የቀረፋ ፓውደር cinnamon powder

አሰራር

• ከላይ የተዘረዘሩትን ፍራፍሬወች በጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ መቀላቀል
• በሌላ አነስተኛ ጎድጓዳ እቃ ውስጥ ማር , ቀረፋ ፓውደር,የሎሚ ቆዳ ፍቅፋቂውን እና የሎሚ ጭማቂውን ቀላቅሎ የተዘጋጀው ፍራፍሬ ላይ ጨምሮ በደምብ በመቀላቀል የናና ቅጠል ነስንሶ ማቅረብ

ለተጨማሪ ጣእም 1/2 ኩባያ የሚሆን የብርቱካን ጁስ መጨምር
ከ2-3 ሰአት አቀዝቅዞ ማቅረብ