Get Mystery Box with random crypto!

​​የቂንጬ ሰላጣ ( Bulgur wheat salad ) የሚያስፈልገን • ግማሽ ኩባያ የስንዴ ቂ | Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂

​​የቂንጬ ሰላጣ
( Bulgur wheat salad )

የሚያስፈልገን

• ግማሽ ኩባያ የስንዴ ቂንጨ
• 2 መካከለኛ ኩከምበር በደቃቁ የተከተፈ
• 3 ቲማቲም በደቃቁ የተከተፈ
• 1 ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
• 4 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ የፐርሲል ቅጠል
• 4 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ የናና ቅጠል
• 3-4 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
• 3-4 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት
• ጨው

አሰራር

• የቂንጬ ስንዴውን ከቀቀሉ በሁዋላ ማቀዝቀዝ
• በጎድጓዳ እቃ ውስጥ የተቀቀለውን ቂንጨ ,ቲማቲም,ኩከምበር,ሽንኩርት,ፐርሲል እና የናና ቅጠሉን በሚገባ መቀላቀል
• በአነስተኛ ጎድጓዳ እቃ ውስጥ የሎሚ ጭማቂ,ዘይት እና ጨው ከቀላቀሉ በሁዋላ ሰላጣው ውስጥ ጨምሮ በሚገባ ለውሶ ማቅርብ::