Get Mystery Box with random crypto!

​​የሽምብራ እና ቲማቲም ሾርባ ለረመዳን ( chickpea and tomato soup for Ramad | Ethio Kushna ኢትዮ ኩሽና🌭🍗🍕🍔🍟🍰🎂

​​የሽምብራ እና ቲማቲም ሾርባ ለረመዳን
( chickpea and tomato soup for Ramadan )

የሚያስፈልጉን

• 3 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት
• 2 የሽይ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት
• 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል
• 1 ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
• 2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ድምብላል ( coriander)
• 1/2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ከሙን ( cumin)
• 1/2 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ ( cinnamon)
• ግማሽ ኪሎ ቲማቲም በትንንሹ የተከተፈ
• 2 ቃሪያ በደቃቁ የተከተፈ
• ጨው እና ቁንዶ በርበሬ
•2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማ
• 2 የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ፐርሲል
• 3 ኩባያ ውሀ
• 2 የታሸገ የቆርቆሮ ሽምብራ

አሰራር

• ዘይት ከጋሉ በሁዋላ ነጭ ሽንኩርት,ዝንጅብል እና ቀይ ሽንኩርት ለ3 ደቂቃ አካባቢ መጥበስ
• ድምብላል,ከሙን እና ቀረፋ ጨምሮ ለተጨማሪ 1 ደቂቃ ማብሰል
• የተከተፈውን ቲማቲም እና ቃሪያ ጨምሮ ከ15-20 ደቂቃ በአነስተኛ የእሳት መጠን ማብሰል
• በመቀጠል ሽምብራውን ጨምሮ ለተጨማሪ 20 ደቂቃ ማብሰል
• በመጨረሻም ፐርሲል እና ጨው ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ለትንሽ ደቂቃ ካበሰሉ በሁዋላ በማውጣት ትኩሱን ማቅረብ