2023-01-21 06:04:36
Cheese soufflé
ቺዝ ሱፍሌ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
• 50 ግራም ፍርኖ ዱቄት (1 የቡና ስኒ)
• 50 ግራም የገበታ ቅቤ
• (1/2) ግማሽ ሊትር ወተት
• 4 እንቁላል
• 150 ግራም የተፈጨ ቺዝ (3 የቡና ስኒ)
• ጨውና ቁንዶበርበሬ
አዘገጃጀት
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ200° ሴንቲግሬድ ማሞቅ፤
2. በድስት ውስጥ ቅቤውን ማቅለጥ፤
3. የእንጨት ማማሰያ በመጠቀም ዱቄቱን እየጨመሩ ማማሰል፤
4. ቀስ በቀስ ወተቱን መጨመርና ማማሰል፤
5. ለ20 ደቂቃ በአነስተኛ እሳት ማብሰል፤
6. ጨውና የተፈጨ ቺዙን አስገብቶ በደንብ ማማሰልና ከእሳት ላይ ማውረድ፤
7. በሁለት ጎድጓዳ ሰሀን የእንቁላሉ አስኳሉን እና ነጩን መለየት፤
8. አስኳሉን ድስት ውስጥ ያለው ሊጥ ውሰጥ ቀስ በቀስ እያስገቡ በደንብ ማማሰልና ማዋሀድ፤
9. ነጩን የእንቁላል በደንብ መምታት (ነጭ እና አረፋማ እስከሚሆን ድረስ)፤
10. የተመታውን ነጩን የእንቁላል ቀስ በቀስ ሊጡ ውስጥ ጨምሮ በደንብ ማማሰል፤
11. ክሬም ካራምል መስሪያ ቅቤ ቀብቶ ሊጡን በጭልፋ አድርግ እኩል አዳርሶ ኦቨን ውስጥ ማስገባት፤
12. ለ20 ደቂቃ ወደ ላይ እስከሚነፋ ድረስ መጋገር።
975 viewsSamri Asefa, 03:04