Get Mystery Box with random crypto!

ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioi — ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioi — ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books
የሰርጥ አድራሻ: @ethioi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.78K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-10-05 19:23:06
1.5K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 19:22:45 ፋኖነት መጽሐፍ በአሜሪካ እና አውሮፓ!

"ፋኖ ማለት እኔ ነኝ!" በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት የቀድሞው የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ እና በአሁኑ ሰዐት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት እያገለገሉ የሚገኙት የደራሲ ጌትነት ይርሳው "ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባኤ" የተሰኘው አዲሱ መጽሐፍ በሀገር ውስጥ ታትሞ በመነበብ ላይ ሲሆን በአንባብያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወቃል።

በውጭ ሀገራት ያለው በርካታ ኢትዮጵያዊ ወገናችንም መጽሐፉ ተደራሽ የሚሆንበት መንገድ እንዲመቻች በተደጋጋሚ ሲያነሳ የነበረ በመሆኑ ምክንያት በፋኖነት ደጋፊ ማህበር በሰሜን አሜሪካ አሳታሚነት የመጽሐፉ 3ኛ ዕትም፣ ከቀናት በኋላ ተጠናቆ በአሜሪካ ለሚኖሩ አንባብያን በስፋት ተደራሽ መሆን ይጀምራል።

ስለሆነም በአሜሪካ የምትኖሩ እና መጽሐፉን ከዋና አከፋፋዮች በመረከብ በየአካባቢያችሁ ለማሰራጨት ለምትፈልጉ ወገኖቻችን ሁሉ ቀጥሎ በተቀመጠው አድራሻ መሰረት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ስናሳውቅ በታላቅ ደስታ ነው።
* አሳታሚ እና ዋና አከፋፋይ:- የፋኖነት ደጋፊ ማህበር በሰሜን አሜሪካ፣ ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን የስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ:-
* ተፈሪ መኮነን:- (206 419 8746)
* ሙሉወርቅ ይንገስ:- (206 753 8090)
* * * * *
በተጨማሪም በአውሮፓ መጽሐፉን ተረክባችሁ ከአንባብያን ዘንድ የማድረስ ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖቻችን በሚከተለው አድራሻ መሰረት ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
* አደራ ከበደ:- (ሙኒክ ጀርመን)
* ስልክ ቁጥር:- (+49 176 80726071)
* ኢሜል:- adreakebede@yahoo.de
* * * * *
በአሁኑ ሰዓት የፋኖነት መጽሐፍ በሀገር ውስጥ በሀሁ መጽሐፍት መደብር (+251911006705) ዋና አከፋፋይነት (በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ የመፅሐፍት መደብሮችን ጨምሮ) በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኝ በመሆኑ ሀገር ውስጥ ሆናችሁ መጽሐፉን ያላገኛችሁ ወገኖቻችን በየአቅራቢያችሁ በሚገኙ የመጽሐፍት መደብሮች በመሄድ "ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባዔ" መጽሐፍን በእጃቸሁ ታስገቡ ዘንድ ለማሳወቅ እንወዳለን።
* * * * *
በአውስትራሊያ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ መጽሐፉ ተደራሽ የሚሆንበትን መንገድ ቀጥለን የምናሳውቅ ይሆናል።
* * * * *
ፋኖነት የአባቶቻችን የታላቅነታቸው መገለጫ ዕሴታችን ነው!
* * * * *
የደራሲው አድራሻ:-
ስልክ ቁጥር:- +251918717877
1.5K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 17:40:43
3.4K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 17:40:31 የዲያቆን ዳንኤል ክብረት " ፍቅር ወደ ጥላቻ የአደረገው ጉዞ " የተሰኘው አዲስ መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል ::
ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ታዎር
ስ.ቁ. 09 11 00 67 05
3.4K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 07:56:46
1.0K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 07:56:20 የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልክ ይችላል ' የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልክም።

እድሜ ጊዜ ነው። ሰው ሞተ የሚባለውኮ ጊዜው ሲያልቅ ነው። ጊዜ ሲረዝም እድሜ ሲያልቅ ደግሞ ሞት ነው።ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ህመም አይሆንብንም ?ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከእድሜህ እየቀነሰብህ ነው :: " አንድ ሊቅ እንዳለው ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜ ነው":: እንዴት የሰጠኸው ጊዜ ከእድሜህ ላይ የተቀነሰ ነውና::

#ሰበዝ ገፅ 156 በ ዶ/ር አለማየው ዋሴ እሸቴ


ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ ፦
ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 0911006705
1.0K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 08:21:34
177 views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 08:20:25 #የደብረ_ሊባኖስ_አጭር_ታሪክ #ሼር

••• የደብረ ሊባኖስ የመጀመሪያው ቤተከርስቲያን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በ1362 ዓ.ም.ተሰራ።

••• በ1402 ዓ.ም.እንደገና ሁለተኛዋ ቤተ ክርስቲያን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በእጨጌ ቴዎድሮስ ዘመን ታነፀች።

•••1406-1420 ዓ.ም. በዐፄ ይስሐቅ ዘመን በእጨጌ ዮሐንስ ከማ አማካኝነት ሦሰተኛዋ ቤተክርስቲያን በቅድስት ድንግል ማርያም ተሠርታ ሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቷ ተከበረ።

••• በ1474 ዓ.ም. እጨጌ መርሐ ክርሰቶስ (1455-1489 ዓ.ም.) አራተኛዋን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርሰቲያንን አሠራ።

•••በ1500-1533 ዓ.ም.በዐፄ ልብነድንግል ዘመነ መንግሥት አምስተኛው ቤተ ክርስቲያን በእጨጌ ጴጥሮስ አማካኝነት ተሠራ።ግራኝ ሐምሌ 24 ቀን 1523 ዓ.ም.ያቃጠላት ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው።

••• በ1533-1551 ዓ.ም. በዐፄ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት በእጨጌ ዮሐንስ አማካኝነት በግራኝ የተቃጠለው ስድስተኛው ቤተ ክርሰቲያን ተሠራ።

•••በ1603 ዓ.ም የደብረ ሊባኖስ ማኅበረ መነኮሳት ወደ ጎንደር በዐፄ ሱስኒዮስ ዘመን ተሻገሩ።ገዳሙም እየተዘነጋ ሄደ።

•••በ18ኛው መክዘ መነኮሳት ወደ ጥንቱ ደብረ ሊባኖስ መመለስ ጀመሩ።

•••በ1804 ዓ.ም. የሸዋው ንጉሥ ወሰን ሰገድ ሰባተኛውን ቤተ ክርስቲያን አትጋፊኝ በተባለው ቦታ ላይ ሠሩ።ነገርግን ከወራት በኋላ ተቃጠለ።

•••በ1873 ዓ.ም. ዐፄ ዮሐንስ የጥንቱን ቤተ ክርሰቲያን ቦታ አስፈልገውና አስመንጥረው 8ኛውን ቤተ ክርስቲያን ሥራ በአኩስም ጽዮን መልክ ባለ 16 ጉልላት አድርገው ጀመሩ

•••በ1885 ዓ.ም. ዐፄ ዮሐንስ ያሠሩት ቤተ ክርስቲያን ከ12 ዓመታት በኋላ የውጭና የውስጥ ሥራው አልቆ ታቦቱ ገባ።

•••በ1895 ዓ.ም. ዐፄ ምኒልክ 9ኛውን ቤተ ክርስቲያን ማሠራት ጀመሩ።

•••በ1900 ዓ.ም.ዘጠነኛው ቤተክርስቲያን ተጠናቀቀ።

•••በ1929 ዓ.ም.ግንቦት 12 ቀን በግራዝያኒ ትእዛዝ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ተጨፈጨፉ።ቤተ ክርስቲያኑ ተቃጠለ፤ቅርሱ ተዘርፎ ሮም ተወሰደ።

•••በ1952 ዓ.ም. ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሁን ያለውውን 10ኛውን ቤተ ክርስቲያን ማሠራት ጀመሩ።

•••በ1955 ዓ.ም. አሁን ያለው ዐሥረኛው ቤተ ክርስቲያን ተጠናቀቀ።

የመረጃ ምንጭ፦/ዲ.ዳንኤል ክብረት,ኢትዮጵያዊው ሱራፊ፣945-946/

የሀሁ መፃሕፍት መደብር ድራሻ፦
ቁ.1. ስታድየም ናሽናል ታወር፣
ቁ.2. ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ፊት ለፊት እንገኛለን።
ስ.ቁ 09 11 00 67 05
178 viewsedited  05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 08:23:30 ጋዜጠኛ- በወላጆቻችንና በእኛ በልጆቻቸው መካከል ፣ በልጅነትዎ የታዘቡት ዛሬ ጎልቶ የሚታይዎት የስነ-ልቦና ልዩነት ወይንም የትውልድ ዘንቆ (Generational gap) አለ ?

ጸጋዬ ገ/መድህን - አለ! ግልጥ ነው ፤ ልጅ ሆኜ ታላላቆቼ በተግባራቸው እንዳስገነዘቡኝ ፣ ለምሳሌ አንድ ሰው በአንድ ውል ተፈጣጠመ ፣ ቃሉን ሰጠ ፣ መሀላ ገባ ከተባለ ስጋ ወደሙን እንደተቀበለ ይከብዳልና ፤ ያ ሰው ለገባለት መሀላ ህሊናውን ያስገዛል ፤ በቃሉ ይታሰራል ፤ በቃሉ ይከበራል ፤ በቃሉ ይፈረጃል ።

ትንሽ ልጅ ሆኜ አምቦ ከተማ አማራውም "ቃሌን አልከዳም ቃል ገብቻለው"ይላል ::

ኦሮሞውም "ሴሪ ሴሩማ" ወይንም "ሴራ ቁርጥ ነው"ይላል ::

አማራውም "የተናገሩት ከሚሞት የወለዱት ይሙት"ይላል ::

ኦሮሞውም"ቃልን ነገር አይሰብረውም ፣ ጦር አይመልሰውም"ይላል ።
ስለዚህም ህዝቡ ከባህላዊ ስነምግባሩና ፤ ከስነ-ልቦናዊ ባህሪ ጽናት የተነሳ እከሌ ቃሉን ሰበረ ሲሉት ይደነግጣል ። ዛሬ ግን አንድ ጮሌ ወይንም አንድ ካድሬ ወይንም አንድ የስልጣን ልክፍተኛ ፣ ከአንድ መሀላ ወደሌላ መሀላ ፤ ከአንድ ድርጅት ወደሌላ ድርጅት እንደ ቅሪላ ዘጠኝ ጊዜ ሲንፏቀቅ ፣ ጎበዝ! ነው ብለን እናደንቀው ይሆናል እንጂ ነውር ነው ብለን አንደነግጥም ። አዎን በእኛና በወላጆቻችን መሀል ጉልህ የሆነ የትውልድ ዘንቅ (Generation gap) አለ ይላል ።

ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ ፦
ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ.    0911006705
827 viewsedited  05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:13:15
1.8K views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ