Get Mystery Box with random crypto!

ፋኖነት መጽሐፍ በአሜሪካ እና አውሮፓ! 'ፋኖ ማለት እኔ ነኝ!' በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት የ | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

ፋኖነት መጽሐፍ በአሜሪካ እና አውሮፓ!

"ፋኖ ማለት እኔ ነኝ!" በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት የቀድሞው የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ እና በአሁኑ ሰዐት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት እያገለገሉ የሚገኙት የደራሲ ጌትነት ይርሳው "ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባኤ" የተሰኘው አዲሱ መጽሐፍ በሀገር ውስጥ ታትሞ በመነበብ ላይ ሲሆን በአንባብያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወቃል።

በውጭ ሀገራት ያለው በርካታ ኢትዮጵያዊ ወገናችንም መጽሐፉ ተደራሽ የሚሆንበት መንገድ እንዲመቻች በተደጋጋሚ ሲያነሳ የነበረ በመሆኑ ምክንያት በፋኖነት ደጋፊ ማህበር በሰሜን አሜሪካ አሳታሚነት የመጽሐፉ 3ኛ ዕትም፣ ከቀናት በኋላ ተጠናቆ በአሜሪካ ለሚኖሩ አንባብያን በስፋት ተደራሽ መሆን ይጀምራል።

ስለሆነም በአሜሪካ የምትኖሩ እና መጽሐፉን ከዋና አከፋፋዮች በመረከብ በየአካባቢያችሁ ለማሰራጨት ለምትፈልጉ ወገኖቻችን ሁሉ ቀጥሎ በተቀመጠው አድራሻ መሰረት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ስናሳውቅ በታላቅ ደስታ ነው።
* አሳታሚ እና ዋና አከፋፋይ:- የፋኖነት ደጋፊ ማህበር በሰሜን አሜሪካ፣ ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን የስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ:-
* ተፈሪ መኮነን:- (206 419 8746)
* ሙሉወርቅ ይንገስ:- (206 753 8090)
* * * * *
በተጨማሪም በአውሮፓ መጽሐፉን ተረክባችሁ ከአንባብያን ዘንድ የማድረስ ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖቻችን በሚከተለው አድራሻ መሰረት ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
* አደራ ከበደ:- (ሙኒክ ጀርመን)
* ስልክ ቁጥር:- (+49 176 80726071)
* ኢሜል:- adreakebede@yahoo.de
* * * * *
በአሁኑ ሰዓት የፋኖነት መጽሐፍ በሀገር ውስጥ በሀሁ መጽሐፍት መደብር (+251911006705) ዋና አከፋፋይነት (በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ የመፅሐፍት መደብሮችን ጨምሮ) በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኝ በመሆኑ ሀገር ውስጥ ሆናችሁ መጽሐፉን ያላገኛችሁ ወገኖቻችን በየአቅራቢያችሁ በሚገኙ የመጽሐፍት መደብሮች በመሄድ "ፋኖነት በምስጢራዊው ጉባዔ" መጽሐፍን በእጃቸሁ ታስገቡ ዘንድ ለማሳወቅ እንወዳለን።
* * * * *
በአውስትራሊያ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ መጽሐፉ ተደራሽ የሚሆንበትን መንገድ ቀጥለን የምናሳውቅ ይሆናል።
* * * * *
ፋኖነት የአባቶቻችን የታላቅነታቸው መገለጫ ዕሴታችን ነው!
* * * * *
የደራሲው አድራሻ:-
ስልክ ቁጥር:- +251918717877