Get Mystery Box with random crypto!

#የደብረ_ሊባኖስ_አጭር_ታሪክ #ሼር ••• የደብረ ሊባኖስ የመጀመሪያው ቤተከርስቲያን በቅድስት | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

#የደብረ_ሊባኖስ_አጭር_ታሪክ #ሼር

••• የደብረ ሊባኖስ የመጀመሪያው ቤተከርስቲያን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በ1362 ዓ.ም.ተሰራ።

••• በ1402 ዓ.ም.እንደገና ሁለተኛዋ ቤተ ክርስቲያን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በእጨጌ ቴዎድሮስ ዘመን ታነፀች።

•••1406-1420 ዓ.ም. በዐፄ ይስሐቅ ዘመን በእጨጌ ዮሐንስ ከማ አማካኝነት ሦሰተኛዋ ቤተክርስቲያን በቅድስት ድንግል ማርያም ተሠርታ ሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቷ ተከበረ።

••• በ1474 ዓ.ም. እጨጌ መርሐ ክርሰቶስ (1455-1489 ዓ.ም.) አራተኛዋን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርሰቲያንን አሠራ።

•••በ1500-1533 ዓ.ም.በዐፄ ልብነድንግል ዘመነ መንግሥት አምስተኛው ቤተ ክርስቲያን በእጨጌ ጴጥሮስ አማካኝነት ተሠራ።ግራኝ ሐምሌ 24 ቀን 1523 ዓ.ም.ያቃጠላት ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው።

••• በ1533-1551 ዓ.ም. በዐፄ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት በእጨጌ ዮሐንስ አማካኝነት በግራኝ የተቃጠለው ስድስተኛው ቤተ ክርሰቲያን ተሠራ።

•••በ1603 ዓ.ም የደብረ ሊባኖስ ማኅበረ መነኮሳት ወደ ጎንደር በዐፄ ሱስኒዮስ ዘመን ተሻገሩ።ገዳሙም እየተዘነጋ ሄደ።

•••በ18ኛው መክዘ መነኮሳት ወደ ጥንቱ ደብረ ሊባኖስ መመለስ ጀመሩ።

•••በ1804 ዓ.ም. የሸዋው ንጉሥ ወሰን ሰገድ ሰባተኛውን ቤተ ክርስቲያን አትጋፊኝ በተባለው ቦታ ላይ ሠሩ።ነገርግን ከወራት በኋላ ተቃጠለ።

•••በ1873 ዓ.ም. ዐፄ ዮሐንስ የጥንቱን ቤተ ክርሰቲያን ቦታ አስፈልገውና አስመንጥረው 8ኛውን ቤተ ክርስቲያን ሥራ በአኩስም ጽዮን መልክ ባለ 16 ጉልላት አድርገው ጀመሩ

•••በ1885 ዓ.ም. ዐፄ ዮሐንስ ያሠሩት ቤተ ክርስቲያን ከ12 ዓመታት በኋላ የውጭና የውስጥ ሥራው አልቆ ታቦቱ ገባ።

•••በ1895 ዓ.ም. ዐፄ ምኒልክ 9ኛውን ቤተ ክርስቲያን ማሠራት ጀመሩ።

•••በ1900 ዓ.ም.ዘጠነኛው ቤተክርስቲያን ተጠናቀቀ።

•••በ1929 ዓ.ም.ግንቦት 12 ቀን በግራዝያኒ ትእዛዝ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ተጨፈጨፉ።ቤተ ክርስቲያኑ ተቃጠለ፤ቅርሱ ተዘርፎ ሮም ተወሰደ።

•••በ1952 ዓ.ም. ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሁን ያለውውን 10ኛውን ቤተ ክርስቲያን ማሠራት ጀመሩ።

•••በ1955 ዓ.ም. አሁን ያለው ዐሥረኛው ቤተ ክርስቲያን ተጠናቀቀ።

የመረጃ ምንጭ፦/ዲ.ዳንኤል ክብረት,ኢትዮጵያዊው ሱራፊ፣945-946/

የሀሁ መፃሕፍት መደብር ድራሻ፦
ቁ.1. ስታድየም ናሽናል ታወር፣
ቁ.2. ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ፊት ለፊት እንገኛለን።
ስ.ቁ 09 11 00 67 05