Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ- በወላጆቻችንና በእኛ በልጆቻቸው መካከል ፣ በልጅነትዎ የታዘቡት ዛሬ ጎልቶ የሚታይዎት የስ | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

ጋዜጠኛ- በወላጆቻችንና በእኛ በልጆቻቸው መካከል ፣ በልጅነትዎ የታዘቡት ዛሬ ጎልቶ የሚታይዎት የስነ-ልቦና ልዩነት ወይንም የትውልድ ዘንቆ (Generational gap) አለ ?

ጸጋዬ ገ/መድህን - አለ! ግልጥ ነው ፤ ልጅ ሆኜ ታላላቆቼ በተግባራቸው እንዳስገነዘቡኝ ፣ ለምሳሌ አንድ ሰው በአንድ ውል ተፈጣጠመ ፣ ቃሉን ሰጠ ፣ መሀላ ገባ ከተባለ ስጋ ወደሙን እንደተቀበለ ይከብዳልና ፤ ያ ሰው ለገባለት መሀላ ህሊናውን ያስገዛል ፤ በቃሉ ይታሰራል ፤ በቃሉ ይከበራል ፤ በቃሉ ይፈረጃል ።

ትንሽ ልጅ ሆኜ አምቦ ከተማ አማራውም "ቃሌን አልከዳም ቃል ገብቻለው"ይላል ::

ኦሮሞውም "ሴሪ ሴሩማ" ወይንም "ሴራ ቁርጥ ነው"ይላል ::

አማራውም "የተናገሩት ከሚሞት የወለዱት ይሙት"ይላል ::

ኦሮሞውም"ቃልን ነገር አይሰብረውም ፣ ጦር አይመልሰውም"ይላል ።
ስለዚህም ህዝቡ ከባህላዊ ስነምግባሩና ፤ ከስነ-ልቦናዊ ባህሪ ጽናት የተነሳ እከሌ ቃሉን ሰበረ ሲሉት ይደነግጣል ። ዛሬ ግን አንድ ጮሌ ወይንም አንድ ካድሬ ወይንም አንድ የስልጣን ልክፍተኛ ፣ ከአንድ መሀላ ወደሌላ መሀላ ፤ ከአንድ ድርጅት ወደሌላ ድርጅት እንደ ቅሪላ ዘጠኝ ጊዜ ሲንፏቀቅ ፣ ጎበዝ! ነው ብለን እናደንቀው ይሆናል እንጂ ነውር ነው ብለን አንደነግጥም ። አዎን በእኛና በወላጆቻችን መሀል ጉልህ የሆነ የትውልድ ዘንቅ (Generation gap) አለ ይላል ።

ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጻሕፍት መደብር
አድራሻ ፦
ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ.    0911006705