Get Mystery Box with random crypto!

ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioi — ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioi — ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books
የሰርጥ አድራሻ: @ethioi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.78K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-14 07:53:45
5.0K views04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 07:53:36 "ሕይወት አዙሪት ናት። ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው። ራቁትህን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ። በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ። የሕይወትን ትግል እየዳህክ ትጀምራለህ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ። ዘመንም ተምኔታዊ ነው። መስከረም ጥቅምንት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል። ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ። ሕይወት አዙሪት ናት! መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው። የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና። የጀመርክበትን አትናቅ፤ ትጨርስበታለህና። ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ፥ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር፥ ነግደህ ሀብት ብታገኝ፣ ተሹመህ ህዝብ ላይ ብትሰለጥን፣ ክብረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው። " (መርበብት፣ ገፅ 314-315)

ሀሁ መጻሕፍት
አድራሻ ፦ ቁ.1 አ.አ ስታዲየም ናሽናል ታወር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ.0911006705
5.0K viewsedited  04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 08:11:41
9.2K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 08:11:31 የዓለማየሁ ገላጋይ አዲስ መፅሐፍ በታላቅ ቅናሽ ሽያጭ ላይ ነኝ ።
ሀሁ መጻሕፍት
አድራሻ ፦ ቁ.1 አ.አ ስታዲየም ናሽናል ታወር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ.0911006705
8.2K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 14:32:14
13.0K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 14:32:08 ገበያ ላይ ጠፍተው የነበሩ መጽሐፍት ወደ መደብራችን ጎራ ብለዋል።

ሀሁ መጽሐፍት መደብር

አድራሻ ቁ. 1 ስታድየም ናሽናል ታወር ግራውንድ ፍሎር
2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ

ስ.ቁ 0911006705
10.4K viewsedited  11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 06:42:15
13.9K views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 06:42:07 ይህ ወቅት ድንቅ ነው። የተማከሩ ይመስል በርካታ ጸሐፊያንና ሊቃውንት የመጻሕፍት አበርክቶአቸውን በተመሳሳይ ጊዜ የዘከሩበት ነው። በእርግጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቤተክርስቲያናችን የንባብም የመፃፍም ልማድ የተነቃቃበት ጊዜ ነው ማለት ይቻላል። ይህ መነቃቃት ግን የቅርቡን መቶዎች ዓመታትን የጽሕፈትና፣ የምዕመናንን የንባብ ባሕል ያነጻጸረ እንደሆነ ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ መረዳት ያስፈልጋል። ይህ መነቃቃት በወግ ከተያዘና በአገባብ ከተመራ ፍሬው የሚንዠረገግበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

እኔም በአቅሜ ወቅታዊ መስሎ በተሰማኝ አንድ ርዕስ ላይ ጥቂት ነገር ለመጫር መረጃዎች ሰብስቤ፣ አቀናጅቼና አብረው ሊቀርቡ የሚችሉ ሌሎች ጽሑፎችን አጠናቅሬ አፈፃፀሙ ላይ ሳተኩር የተለያዩ የመጻሕፍት ጅረቶች ከልዩ ልዩ አፍላጋት በዙሪያዬ ይጎርፉ ጀመር። የደብተራ በአማን "ተኀሥሦ"፣ የዲያቆን ሄኖክ "የብርሃን እናት"፣ የመጋቤ ብሉይ ወ ሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን "መጽሐፈ ምዕዳን" በተለያዩ ኅብረ ቀለማት ሚዲያውን ሲያጥለቀልቁት ከመደነቅ በተሻገረ ጉጉት እየተናጥሁ ተመለከትሁ።

ጉጉቴ ይዘታቸውን ምንጫቸው እንደሚወስነው ስለተረዳሁ ይመስለኛል። ጥቂት ቀደም ብለው ለንባብ የበቁት እንደ "የልቡና ችሎት"፣ "ሳብራ"፣ "ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ"፣ "መንገደ ብርሃን" "ሚተራሊዮን" ... መጣሁ መጣሁ የሚሉት የመምሕር ፋንታሁን ዋቄ "ኦርቶዶክሳዊነትና የሠይጣን መንግሥት" እና "ሥዝም ሰብአዊነት" የኢዮብ ቱሉ "ንጥቂያ" ... መካከል አንድ አነስ ያለች ሥራ ይዤ መቀላቀሌ መሰለኝ። ነገሩን ያየሁት ለአንድ ታላቅ በዓል ዝግጅት ከአንድ ታላቅ ገበያ ዶሮ ገዝቼ የበግ ጠቦትና የፍየል ሙክት፣ ወይፈንና ሰንጋ ከሚነዱ ሰዎች መካከል ኩስ ኩስ እያልኩ እንደሆነ ነው። ያም ሆኖ ከንባብ የሚያጎድል የለምና ምንም ታናሽ ብትሆን ይህችን መጽሐፍ ለአንባቢያን አበርክቻለሁ።

በመጽሐፏ ውስጥ የታሪክ ምሑራንን ያህል ጥልቅ ባይሆንም በአንድ ታሪካዊ ሙግት ላይ መከራከሪያዬን አቅርቤያለሁ። ጥቂት ስብከታዊ ጽሑፎችና ምልከታዎችም ተካተዋል። የእቅበተ እምነት ጽሑፎችም አሉበት። ለማዋዛት ያህል ውስን ገጠመኞቼንም የመጽሐፌ አካል አድርጌያቸዋለሁ። ይህች "ጩጬ" መጽሐፍ በማንኩሳ ማተሚያ ቤት ስትዋብና ስትኳል ከርማ በነገው ዕለት ወደ ብርሃን ትወጣለች። ከነገ በስቲያም ጀምሮ በዋና አከፋፋዩ ሀሁ መጻሕፍት ቤት አማካኝነት ወደየመጻሕፍቱ መደብርና ወደ አንባቢዎቿ እጅ ትደርሳለች።

መጽሐፏ ውስጥ በተጠቀሰ አድራሻ አስተያየታችሁን እንደምታኖሩ ተሥፋ አደርጋለሁ። እርማት፣ ምክር፣ ትችት፣ ተግሳፅና ነቀፋ.. ሁሉንም ዓይነት አስተያየት እቀበላለሁ። የልብና የአንደበት ቅድስናችሁን እንዳያጎድፍ እሠጋለሁ እንጂ የፈለገ ሰው ሊሰድበኝና ሊረግመኝም ይችላል። ሁሉን በአኮቴት እቀበላለሁ። የትኛውም አስተያየት አንዳች ነገር ያመላክተኛል። ጌታ ቢፈቅድ በቀጣይ ለሚኖረኝ ዳጎስና ጠብሰቅ ላለ ሥራዬ ከአቀራረብ እስከ ይዘት ሁለንተናዊ ግብዐት ይሆነኛልና ስለ ሁሉም አመስጋኝ ነኝ።

ክብረት ይስጥልኝ...!
ማርያማዊት ገብረ መድን
ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጻሕፍት
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ. 0911006705
11.1K views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 09:25:36
11.4K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 09:25:07 "ሚተራሊዮን"

"ውሃ ተቃርኖ የሚመስሉ ጠባያት እንዳሉት ሁሉ ኢትዮጵያም ብዙ ተቃርኖዎችን ታቅፋ የምትኖር ሀገር ናት።ውሃ ሕይወት ሆኖ ያሳደገውን ሰብል በረዶ ሆኖ መቅሰፍት ሆኖ ያጠፋዋል። ኢትዮጵያም እንደ ውሃ በተቃርኖ የተሞላች ናት ፤ ደግ ስትሆን ክፋት፣ጥንታዊ ስትሆን ጀማሪ ፣ስልጣኔ ፋና ወጊ ስትሆን ኃላቀር፣ ባለፀጋ ስትሆን ደሀ፣ውብ ስትሆን ጎስቋላ፣ለብዙዎች መሆን ስትችል ለልጆቿ ያልሆነች፣ሰፊ ሆና የጠበበችን ውሃ ናት ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያ ውሃ ላይ ተኝታ ድርቅ የሚያሰቃያት፤የውሃ ማማ ሆና ሀይል የሚያጥራት ናት።ተበተነች ስትባል አንድ የምትሆን፣ደከመች ስትባል የምትበረታ፣ ብቻዋን ቀረች ስትባል ከብዙዎች መካከል የምትገኝ ናት ኢትዮጵያ። ሃይማኖትህን ያለ ሀገር ሆነህ የትም ልታከብረው ትችል ይሆናል፤ ሀገር ስታጣ ግን ሁሉን ታጣለህ።ኦርቶዶክስን ግብፅ፣እስልምናን መካ መዲና፣ ካቶሊክን ቫቲካን፣ ፕሮቴስታንትን ጀርመን ታገኝ ይሆናል። ኢትዮጵያ ግን የትም የለችም። ሃይማኖታችን የምንወደው ኢትዮጵያን ቀድሶ ስለሰጠን ነው። ኢትዮጵያን የምንወዳት ሃይማኖታችንን እጅግ መንፈሳዊና ከፈጣሪ ጋር የሚያገናኘን ንጹሕ መንገድ ስላደረገችልን ነው።

ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

የሀሁ መፅሐፍት መደብር አድራሻ፦
ቁ.1፦ ስታድየም ናሽናል ታወር ፣
ቁ.2፦ ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ፊት ለፊት እንገኛለን።
ስ.ቁ 09 11 00 67 05
10.5K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ