Get Mystery Box with random crypto!

'ሚተራሊዮን' 'ውሃ ተቃርኖ የሚመስሉ ጠባያት እንዳሉት ሁሉ ኢትዮጵያም ብዙ ተቃርኖዎችን ታቅፋ የ | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

"ሚተራሊዮን"

"ውሃ ተቃርኖ የሚመስሉ ጠባያት እንዳሉት ሁሉ ኢትዮጵያም ብዙ ተቃርኖዎችን ታቅፋ የምትኖር ሀገር ናት።ውሃ ሕይወት ሆኖ ያሳደገውን ሰብል በረዶ ሆኖ መቅሰፍት ሆኖ ያጠፋዋል። ኢትዮጵያም እንደ ውሃ በተቃርኖ የተሞላች ናት ፤ ደግ ስትሆን ክፋት፣ጥንታዊ ስትሆን ጀማሪ ፣ስልጣኔ ፋና ወጊ ስትሆን ኃላቀር፣ ባለፀጋ ስትሆን ደሀ፣ውብ ስትሆን ጎስቋላ፣ለብዙዎች መሆን ስትችል ለልጆቿ ያልሆነች፣ሰፊ ሆና የጠበበችን ውሃ ናት ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያ ውሃ ላይ ተኝታ ድርቅ የሚያሰቃያት፤የውሃ ማማ ሆና ሀይል የሚያጥራት ናት።ተበተነች ስትባል አንድ የምትሆን፣ደከመች ስትባል የምትበረታ፣ ብቻዋን ቀረች ስትባል ከብዙዎች መካከል የምትገኝ ናት ኢትዮጵያ። ሃይማኖትህን ያለ ሀገር ሆነህ የትም ልታከብረው ትችል ይሆናል፤ ሀገር ስታጣ ግን ሁሉን ታጣለህ።ኦርቶዶክስን ግብፅ፣እስልምናን መካ መዲና፣ ካቶሊክን ቫቲካን፣ ፕሮቴስታንትን ጀርመን ታገኝ ይሆናል። ኢትዮጵያ ግን የትም የለችም። ሃይማኖታችን የምንወደው ኢትዮጵያን ቀድሶ ስለሰጠን ነው። ኢትዮጵያን የምንወዳት ሃይማኖታችንን እጅግ መንፈሳዊና ከፈጣሪ ጋር የሚያገናኘን ንጹሕ መንገድ ስላደረገችልን ነው።

ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

የሀሁ መፅሐፍት መደብር አድራሻ፦
ቁ.1፦ ስታድየም ናሽናል ታወር ፣
ቁ.2፦ ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ፊት ለፊት እንገኛለን።
ስ.ቁ 09 11 00 67 05