Get Mystery Box with random crypto!

'ሕይወት አዙሪት ናት። ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው። ራቁትህን | ሀሁ መጻሕፍት /Hahu books

"ሕይወት አዙሪት ናት። ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው። ራቁትህን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ። በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ። የሕይወትን ትግል እየዳህክ ትጀምራለህ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ። ዘመንም ተምኔታዊ ነው። መስከረም ጥቅምንት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል። ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ። ሕይወት አዙሪት ናት! መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው። የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና። የጀመርክበትን አትናቅ፤ ትጨርስበታለህና። ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ፥ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር፥ ነግደህ ሀብት ብታገኝ፣ ተሹመህ ህዝብ ላይ ብትሰለጥን፣ ክብረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው። " (መርበብት፣ ገፅ 314-315)

ሀሁ መጻሕፍት
አድራሻ ፦ ቁ.1 አ.አ ስታዲየም ናሽናል ታወር
ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ
ስ.ቁ.0911006705