Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 ) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 )
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students_only
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2023-04-01 11:54:33 #ተጨማሪ

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ድረስ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግሥት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ለድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ #ብቻ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9 እስከ 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 በመማር ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸውም ተገልጿል።

በመግለጫውም ተማሪዎ፣ ወላጆች፣ መዝጋቢዎች እና ከመምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.0K viewsAYY, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 16:09:31
#EAES

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለባቸው ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ፤ ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል ተብሏል።

@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
4.0K viewsAnwar, edited  13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 14:24:49
በደቡብ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቀነስ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

በክልሉ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 2.6 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸው ይታወቃል።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የታየው የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ችግሮች ለትምህርት ውጤታማነት መቀነስ ተጠቃሽ ምክንያት እንደሆኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በትምህርት ዘርፍ ላጋጠመው የውጤታማነት ችግር የመምህራን፣ የተማሪዎች፣ የአመራሩ እና የህብረተሰቡ ድርሻ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባ ተነስቷል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
4.3K viewsAYY, edited  11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 14:22:19
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካሰለጠናቸው ተማሪዎች በተጨማሪ በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች በድህረ ምረቃ 112 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ዩኒቨርስቲው ከቅዱስ ላሊበላ ቅርስና ጥናት ግቢ  25 ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በድህረ ምረቃ መርሀ ግብር አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 160 ሴት አና 430 ወንድ በድምሩ 592 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት አበበ ግርማ ( ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው በወልድያ፣ በመርሳና በላሊበላ ግቢዎች  በጤና፣ በቱሪዝም፣ በግብርናና በቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከላት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ2004 ዓ ·ም   ጀምሮ የምርምርና የልህቀት  ሥራ እየሠራ ይገኛል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
3.9K viewsAYY, 11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 14:37:21
ራያ ዩኒቨርሲቲ ስራውን በማስጀመር ዙርያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አደረገ

የራያ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት አመታት ከተቋረጠ በኋላ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዴት መጀመር እንዳለበት ከአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር በመጋቢት 12/2015 ዓ/ም ውይይት አካሄደ። የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለሁለት አመታት ከተራዘመ ጦርነት እና አስከፊ ሁኔታ በኋላ ሰራተኞቹን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በአዲስ መንፈስና ጉልበት የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲቀጥል ጠንካራና ጠንካራ ሆነው እንዲቀጥሉ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። በተጨማሪም ክልሉ ከገባበት ጥልቅና ውስብስብ ችግሮች ለመዳን ዩኒቨርሲቲው እና ህብረተሰቡ ጠንካራ ቁርጠኝነት ስለሚፈልግ የሀብት አጠቃቀምን በወቅቱ አጽንኦት ሰጥቷል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲስ መንፈስና ጉልበት ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት እና ተነሳሽነት ገልፀዋል ።
ባለፉት ሁለት አስከፊ አመታት ህብረተሰቡ ያጋጠሙትን የተወሳሰቡ የስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን ለመቅረፍ እና ለማቋቋም በሚችሉት ሁሉ የድርሻቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
4.3K viewsAYY, 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 09:44:48
ዩኒቨርሲቲው ደረጃውን የጠበቀ የፈተና ማዕከል እያስገነባ እንደሆነ ተገለፀ

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሚሰጡ ማንኛውም አይነት ፈተናዎች ተማሪዎች በራሳቸው  አቅም ብቻ እንዲሰሩ፣ በራስ የመተማመን አቅማቸው እንዲጎለብት እንዲሁም የትውልድ ነቀርሳ የሆነውን ኩረጃ ከዩኒቨርሲቲው ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የሚያስችል በሲሲቲቪ ካሜራ የተደገፈ በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎችን ማስተናገድና መፈተን የሚያስችል የፈተና ማዕከል እያስገነባ ይገኛል፡፡

ይህ የፈተና ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው አልፎ ከቅጥር ጋር ተያይዞ ለሌሎች መሰል ተቋማት ፈተናዎችን ለመስጠት የሚያገለግል እንደሆነ ከዩንቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
4.0K viewsAYY, 06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 14:04:00
#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል።

ኮሌጁ በመጀመሪያ ዲግሪ 228 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ 7 በአጠቃላይ 235 ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 16/2015 ዓ.ም ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች መስኮች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ የሁለተኛ ዲግሪ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የከፍተኛ ዲፕሎማ (HDP) እና የPGDT ሰልጣኞችን በዕለቱ ያስመርቃል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
4.4K viewsAYY, 11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 18:58:24
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ ያሰለጠናቸውን 39 ተማሪዎች አስመርቋል።

በአካዳሚው እየተሠጠ ያለው የመርከበኞች ስልጠና ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ኃይል ለውጭ ሀገራት እንድታቀርብ ማስቻሉን በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የመርከበኝነት ሥልጠናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በመካኒካል ኢንጅነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ አጠናቀው በውድድር የሚመረጡ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከአካዳሚው የሚመረቁ ሰልጣኞች በዓለም አቀፍ የመርከብ ድርጅቶች ተቀጥረው የመስራት ዕድል አላቸው ተብሏል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የመርከብ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ የሆነው አካዳሚው፤ እስካሁን ከ2 ሺህ በላይ መርከበኞችን አስመርቋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
4.6K viewsAYY, 15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 18:49:41
#ArsiUniversity

በ2015 ዓ.ም በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት መጋቢት 25 እና 26/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፡-

➧ የማህበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በበቆጂ ካምፓስ
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ 

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
4.9K viewsAYY, edited  15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:04:16
#MoE

250 ሺህ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው ሐምሌ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Academy
5.2K viewsAYY, edited  15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ