Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Students Books(Grade 9-12 )

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 ) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_students_only — Ethio Students Books(Grade 9-12 )
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_students_only
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 282
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2023-04-05 18:30:12
ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለዓለም አቀፍ የአይሲቲ የፍፃሜ ውድድር አለፉ

በዘንድሮው የሁዋዌ ግሎባል አይሲቲ የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በሚደረገው ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል

ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ተመዝግበው በበይነ መረብ አማካይነት ፈተና የወሰዱ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ፈተናውን ማለፍ የቻሉ 63 ተማሪዎች በብሔራዊ የአይሲቲ ውድድር ላይ ሲሳተፉ ቆይተዋል። 
በተያዘው 2015 ዓ.ም. ታህሳስ ወር በአዲስ አበባ ሁዋዌ እና የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በመተባበር በተካሄደው ውድድር በድምሩ 15 የሚያልፉ ተማሪዎች ተለይተው ቀጣይ ዙር ውድድር ላይ ቆይተዋል።
ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ወደ ዓለም አቀፉ የሁዋዌ ኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) የፍፃሜ ውድድር ማለፋቸውን የሁዋዌ ኩባንያ የኢትዮጵያ ቢሮ ለአዲስ ዘይቤ በላከው መግለጫ አስታውቋል። ተማሪዎቹ በቻይና በሚካሄደው የሁዋዌ አይሲቲ የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉም ይጠበቃል።
የሁዋዌ ኢትዮጵያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሊሚንግ ዪ በውድድሩ የተሳተፉ ተማሪዎችን አመስግነው የሁዋዌ የአይሲቲ ውድድር በዓለም ዙሪያ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአይሲቲ ዘርፍ ውድድር እያደረጉ ሃሳባቸውን እንዲለዋወጡ ያስቻለ መድረክ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.5K viewsAYY, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 17:59:45 Share 'English work sheet 11.pdf'


#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_AcAdmy
1.5K viewsAYY, 14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 18:34:49 EXTREME ENGLISH

FOR GRADE 11&12
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.8K viewsAYY, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 19:37:16
በ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ የህጋዊነት ማረጋገጫ ተደርጎ 900 የሚሆኑት ሐሰተኛ ሆነው ተገኙ።

የትምህርት ማስረጃዎቹ ተመሳስለው የተሠሩ፣ ዕውቅና ከሌለው ተቋም የተሰጡ፣ ባልተፈቀደ የሙያ መስክ የሰለጠኑ እንዲሁም የመቁረጫ ነጥብና የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው የሠለጠኑ መሆናቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለሥስልጣን አሳውቋል።

የተወሰኑ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባለሥልጣኑ ዕውቅና ውጪ ካምፓስ አስፋፍተውና ፍቃድ ባላገኙበት የትምህርት ዘርፍ ስልጠና ሲሰጡ መገኘታቸውንም ባለሥስልጣኑ አረጋግጧል።

ባልተፈቀደላቸው የትምህርት መርሃ ግብር እና ከተቀመጠላቸው ቁጥር በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው ሲያስተምሩ የነበሩ ተቋማት መገኘታቸውንም የባለሥስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሽፈራው ሽጉጤ ገልጸዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.2K viewsAYY, edited  16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 12:04:45
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሞዴል ፈተና ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ ሳምንት ይሰጣል።

ሞዴል ፈተናው ከመጋቢት 27 እስከ 29/2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

ሞዴል ፈተናው ስታንዳርዱን ጠብቆ በቢሮው መዘጋጀቱን የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ገልጸዋል።

ፈተናው ተማሪዎች ራሳቸውን ለዋናው ፈተና ዝግጁ ማድረግ እንዲችሉ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.3K viewsAYY, edited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:38:20 የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ አዋጅ

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ራስ ገዝ ሲሆኑ የሚሾሙላቸው ፕሬዝዳንቶች የፖለቲካ ፓርቲ አባል እንዳይሆኑ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል።

ባለፈው ሐሙስ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ፤ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች አሿሿም እና የሥራ ዘመን ላይ ለውጦችን አድርጓል።

ረቂቁ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንት ሹመት የሚከናወነው “በዩኒቨርሲቲው ቻንስለር ይሆናል” ሲል ያስቀምጣል።

የዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንት የሚሾመው “በዓለም አቀፍ ደረጃ ግልጽ በሆነ ውድድር” መሆኑን የሚያትተው አዋጁ፤ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው ቦርድ አቅራቢነት ከሚቀርቡ ሦሥት ዕጩዎች መካከል የዩኒቨርሲቲው “ቻንስለር” ፕሬዝዳንቱን እንደሚሾሙ በረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

በረቂቁ መሰረት ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ያሸነፈ ግለሰብ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ከሆነ ከፓርቲ አባልነት ለመልቀቅ መስማማት ይኖርበታል።

በቀዳሚነት ራስ ገዝ እንደሚሆን የሚጠበቀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ብልጽግና ፓርቲን ወክለው አባል ናቸው።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊልም በተመሳሳይ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲን ወክለው የፓርላማ አባል ናቸው።

ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሆነው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠናም በተመሳሳይ ብልጽግናን ወክለው ፓርላማ ገብተዋል።

ረቂቅ አዋጁ ያስተዋወቀው ሌላኛው አዲስ ነገር “የዩኒቨርሲቲ ቻንስለር” የተባለውን የኃላፊነት ቦታ ሲሆን በአዋጁ መሰረት የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ አደረጃጀት የሚጀምረው ከ“ቻንስለር” ነው።

ቻንስለሩ በዩኒቨርሲቲው የውስጥ አስተዳደር ውስጥ ሳይገባ “እንደ ከፍተኛ አምባሳደር የሚያገለግል፣ ሃብት የሚያፈላልግና ሌሎች በጎ ተግባራትን የሚያከናውን” እንደሚሆን በረቂቁ ተቀምጧል።

በአዋጁ መሰረት ራስ ገዝ ለሚሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች “ቻንስለር” የሚሾመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን ቻንስለሩ ለአምስት ዓመት የሚያገለግል ይሆናል።

በረቂቁ ጠንካራ የፋይናንስ አቅምና አካዳሚያዊ ተወዳዳሪነት፤ ራስ ገዝ ለመሆን ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች መካከል ተጠቅሰዋል።

ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ በትምህርት ሚኒስቴር ዕቅድ ተይዟል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዚህ በጀት ዓመት የራስ ገዝ አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች በመንግስት ከሚሰጣቸው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በስጦታ፣ በኑዛዜ፣ ከፈጠራ ገቢ እና ከትምህርት ከፍያ ሊያገኙ እንደሚችሉ በረቂቁ እንደሰፈረ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘገባ ያሳያል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.2K viewsAYY, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 13:58:09 በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች የምግብ አገልግሎት የሚመደበው በጀት ማስተካከያ እንዲደረግበት ተቋማቱ ጠይቀዋል። 

እስካሁን ባለው አሰራር ለተማሪዎች ቀለብ በቀን ለአንድ ተማሪ 15 ብር ሲበጀት ቆይቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ግን ለአንድ ተማሪ በቀን እስከ 100 ብር እንደሚያወጡ ይገልጻሉ፡፡

አሁን ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ለሌላ ሥራ የሚመደበው በጀት ለተማሪ ምገባ እየዋለ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢፕድ የሰጡ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ወቅታዊ ገበያውን መሠረት ባደረገ መልኩ የዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል፡፡

ለዩኒቨርሲቲዎቹ ለምግብ አገልግሎት የሚመደበውን በጀት ለማስተካከል ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያውን የማሻሻል ሥራ እየሠራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በ19 ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተደረገ ጥናትን መሰረት ያደረገ አማካይ የምግብ ዋጋ ለገንዘብ ሚኒስቴር መቅረቡን ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
2.0K viewsAYY, 10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 13:55:16 #ExitExam

ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫው ፈተና ይወስዳሉ ?

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦

" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።

ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።

አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።

ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ Sociologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።

ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "

የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?

" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።

ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.6K viewsAYY, 10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 12:02:14
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  ለቅድመ ዩኒቨርሲቲ  አቅም ማሻሻያ የተመደቡ ተማሪዎችን ውጤታማ ለማዲረግ እየሰራ  ነው፡፡
          
ትምህርት ሚኒስቴር  የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተለያዩ ሪፎረሞችን  አውጥቶ እየሰራ ይገኛል  ፡፡ የዚሁ አካል የሆነው የ12ኛክፍልን ሀገር አቀፍ ፈተና  ኩረጃን በመከላከል በሚያስችችል በጠበቀ ድሲፕሊን   የ2014ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን  በዩኒቨርቲዎች እንድፈተኑ ተደርጓል ፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ  ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎችን  በቅድመ ዩኒቨርሲቲ የ4 ወር ያቅም ማሻሻያ እንድወስዱ በተደረገው  መሰረት  በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  ለተመደቡ አቅም ማሻሻያ ለሚውስዱ ተማሪዎች  ውጤታማ  ይሆኑ ዘንድ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዙሪያው ከሚገኙ  2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ9-12ኛ ክፍል ያሉ  መማሪያ መጽሃፍትን በማሰባሰብና  በየትምህርት አይነቱ ከ9-12ኛክፍል  የሚያገለግሉ መረጃ መጽሀፍትን በመግዛት  አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡
የ24 ሰዓት የቤተ-መፅሀፍት አገልግሎት መስጠት ከ9-12ኛ ክፍል በየትምህርት አይነቱ አጋዥ መፅሀፍትን በቤተመጽሃፍት በማስቀመጥ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት  የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ  የተጣለበትን አደራ  እየተወጣ ይገኛል ፡፡
ለዚህ ተግባር የተመደቡ የግቢው መምህራን የተፈቀደላቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም በልዩ ሁኔታ ለተምህርት  ጥራት የድርሻቸውን  እየተወጡ ያገኛሉ።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_Acadmy
1.7K viewsAYY, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 11:57:49 #NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
#NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY
1.5K viewsAYY, 08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ