Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_leboled — ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_leboled — ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_leboled
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.77K
የሰርጥ መግለጫ

🖇✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️🖇
📚 💥 ማምበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️
📚 💥 እውቀት ሃይል ነው‼️ 📚
📚 ለ እውቀት ትክክለኛው ቦታ✅ 📚
📚 በ ቆይታዎ ዘና ይበሉ ለማንኛውም አስተያየት በ 👉@ethioleboledbotላይ ያድርሱን እናመሰግናለን።
Group- https://t.me/ethio_leboled2

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 19:01:18 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_8


ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ



... የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወርቀቱ እንዲህ ይላል
ሰላም ላንተ ይሁን ጠበቃ አዳም የጠበቃ እስማኤል ወዳጅ ነኝ
ወዳጅ ብቻ አይደለሁም መከታዬ ነው ወንድሜም ጓደኛዬም ሁሉም
ነገሬ ነው ለፍትህ ዘብ የቆመክ ለእውነት የምታድር ሰው
መሆንህን አውቃለው እስማኤል ፍትህ ለተራበ የሚያጠግብ
ለጎደለበት የሚሞላ ነው እስከኖረበት ጊዜ ለእውነት ኖሯል
በመጨረሻም ግን ለአንድ አውሬ ሰው ተበገረ ይህ አውሬ የወዳጄ
እስማኤልን ህይወት ቀጥፎብኛል አንተም እንደሱ ነህ ባንተ በኩል
ፍትህ ያገኙት ስላንተ አውርተው አይጠግቡም እጅግ የጠበቀን
ወዳጄን ህልም እንደምታስጨርስው እርግጠኛ ነኝ ትወጣዋለክ
እንደምትወጣው አምናለው አንብቦ እንደጨርሰ ያን በተለያዩ ልኮች የተፃፈውን እና አርንጎዴ ክር የተያዘውን ደብተር ከፍተው ውስጡ በሉኮቹ ላይ የሰፈሩትን
ተመለከተ ፅሁፎቹ እጅግ የተዋቡ ናቸው በሰማያዊ እና በጥቁር
እስኪብርቶ የተፃፈ ነው የታሪኩ ርእስ መንገደኛው ሎሌ ይሰኛል መንገደኛው ሎሌ መሄድ የለመደው አንድ ቀን ተነስቶ መጓዝ የጀመርው በሄደበት ሁሉ ብዙ ይታዘባል
ተመልካች ታዛቢ ሁሉንም ይሆናል ዛሬ ከቆመበት መንገዱን ጀምሮል
ብሎ አጠር ባለ መልኩ መንገደኛው ሎሌን ገልፇታል መንገደኛ
ስሙን ደሞ በሎሌ ቀይሮ የእዛን አውሬ ስራ አስፍሮታል።
አዳም መፅሀፍን ማንበብ ቀጠለ መፅሀፉም እንዲህ ይላል።
ይገርማችዋል ዛሬ መንገዱኛው ሎሌ እንደለመደው ጉዞውን
ቀጥሏል እየሄደ በመንገዱ ያጋጠሙት ደሀ እናት እና ልጅ ን አየ
እስከሚችለው ሊከተላቸው ወስኖ ሳይሆን እግር መንገዱን
እያያቸው መጓዝ ጀመር እናትና ልጅ በፀጥታ ከተጓዙ በኋላ
ልጅየው እናቷን ሽቅብ አንጋጣ እያየች እናቴ አለቻች እናት
የስማቻት አትመስልም የእኔ እናት እናትዬ እማ እያለች
ስትጎቶጉታት ሀሳቧን እና መንገዷን ገታ አድርጋ ወዬ የእኔ ልጅ
አለች በጣም በደከመና ትንፋሽ በተቀላቀለበት መለኩ እማ እስቲ
አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ እሽ እሺ ልጄ ጠይቂኝ ፍቅር እና መውደድ
ልዩነት አላቸው እንዴ እንዴ እናትም ልጄ በጣም እንጂ በጣም
ልዩነት አላቸው ልጅየው እንዴት አለቻት እናት ልጆ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ልጄ አለቻት ልጅም እሺ እማ አለቻት ጥንድ ጥንድ የሆኑ አካላቶችሽን ንገሪኝ ብላ እናት
ከመናገሯ ልጅት ጥንድ ጥንድ የሆኑት ለምሳሌ አይናችን ሁለት
ነው አለች እናት እሺ ሌላስ አለቻት ሌላ ደሞ እጃችን እግራችን
ሌላስ አለች እናት ልጅቱ ሌላ ጆሮአችን ሌላ ግን የለም አለቻት
እናት ፈገግ ብላ ተሳስተሻል የእኔ ውድ ልጅ አለቻት ልጅም እኔ
የምልሽ እማ ይህ አሁን ከጠየቅሽኝ ጥያቄ ጋር ምን አገናኘው
ያገናኘዋል እንጂ ልጄ እይውልሽ እንዳልሽው እጃችን እግራችን
አይናችን እና ጆሮችን ብቻ ሳይሆን ከልባችን በቀር ሁሉም አጋዥ
አለው ልጅየው ግራ ገባትና እንዴት እናቴ አለቻት ለምሳሌ ጣትሽ
ስንት ነው 10 እሺ ጨንጓራችንንስ እኔጃ እማ እሱም ትንሹ እና
ትልቁ አንጀት የሚባሉ አጋዦች አሉት ፀጉሯችንንም ብዙ አሉት
ከንፍራችን ደሞ ከላይና ከታች አለ ጥርሳችንን ተመልከች ብዙ
ናቸው ሊላም ብዙ ጥንድ ነገሮች አሉ ሁለም አጋዥ የላችውም
ልባችን ግን ብቸኛ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ደሞ ሊ ሌላኛው
ልባችን ጋር ሌላ ሰው ጋረ ስለሆነ ነው አለች እናት ልጅቱ እየተገረመች ማን ጋር? ብላ ጠየቀቻት እናትም የወደፊት የህይወትሽ አጋር ጋር እሱ ጋር ነው ለዛም ነው ፍቅር ሲይዘን ሁሉም ነገራችንን የሚቆጣጠርን ፍቅር ሲይዘን ሁሉም አካላታችን
ስራውን አቁሞ ልባችን የሚስራው ፍቅር ሲይዘን ልባችንን የሚስማን ፍቅር ሲይዝሽ በ ፍቅር ካፍቀሩት ጋር መኖር እድለኝነት ነው። አዳም ንባብን በእዚህ ገታ እና
ወርቀቱን ከደነው።
የማያልፍ ቀናት የለም አለፈ ዛሬ ሄዋን ከጥቄት ሰአታት በኋላ
ትነቃለች አዳም ውስጡ ደስ አለው ቀጥሎ የሚፈጠረው ነገር
መልካም እንደሚሆን አሰበ ስትነቃስ አለ በልቡ ስትነቃስ እንዴት
ነው የምቀርባት ሁሉንም ነገር እኮ እረስታለች ድጋሚ እንድትወደኝ
ላረግ ነው ስቀርባት ማነህ ብትለኝስ ልቡ ፈራ ውዴ እረሳሽኝ ወይ እስቲ መልሽለኝ
ምነው ቢሆን ለእኔ ሁሉን ባርገልኝ ብዬ ለመንኩትኝ ሀሳቤን ቢስማኝ
ብዬ በመጠበቅ ይህው ወራት ሞላኝ ለእሱ ብዙ ነገሩ ናት የሄዋን እጃች
በትንሹ መንቀሳቀስ ጀመሩ አላመነም ዶክተሩ ትነቃለች ቢለውም
የሚንቀሳቀስ እጇን ሲያስ አዳም ደስስስ አለው ዶክተሩን
ለመጣራት ከነፈ አጠገቡ ማንም አልነበርም ዲና በጠዋት ቤቷ
ፍቅድ ጠይቃ ሄዳለች ዲና በመንገድ ላይ እና ቤቷም ከገባች
በኋላ ሰለ አዳም ያለ ማቆርጥ ታስባለች ዲና ስልኳ ጠራ አዳም
ነበር ሄሎ አለችው በተርጋጋ ድምፅ...

ይቀጥላል...
@ethio_leboled
408 views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:00:28 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_7


ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ



... አዳም ድካም እየተስማው ሲመጣ ሌላኛው አግዳሚ ወንበር ላይ
ሄዶ ጋደም አለ ግን ነገ ሄዋን ስለምትነቃ በጉጉት ሊሞት ነው
ሄዋን ከነቃች በኋላ ለሚፈጠርው ነገር እራሱን አእምሮውን አዘጋጀ
ሄዋን ነገ ከኮማ ስትነቃ ልክ እንደማታቀኝ ልታስመስል ነው ወይ
ብሎ እራሱን ከጠየቀ በኋላ መልሶ ለእራሱ አይ አይ ሄዋኔ ወዳ
አደለም የረሳችኝ እንደዚህ መሆኗስ ለእኔ ስትል አደል አለና
እራሱን አፅናና እንዲ ከራሱ ጋር በሀሳብ ሲሞገት ሳያስበው
እንቅልፍ አሽለበው።

የሆነ የሚያስፍራ ኮቴ ሰማ በቀስታ የሚጓዝ ማን እንደሆነ ለማየት
ቀና አለ ምንም አይነት ሰው አልታየውም መልሶ ተኛ አሁን
የሚንሾካሾክ ድምፅ ሰማ ቀና ሲል ከእሱ ትይዩ የተኛችው ዲና
የለችም የት እንደሄደች ግራ በመጋባት እና በፍርሀት ስሜት ወደ
ሄዋን ክፍል እያመራ ሳለ ዲና በ2 ትልልቅ አቅም ባላቸው ስዎች
ተይዛ በጥቁር ፕላስተር እጇ አፏ እና እግሯ ተይዟል በአስተማሚ
ወንበር ላይ ጥብቅ አድርገው አስርዋታል ። አዳምን ስታየው
በተቀመጠችበት ወንበር ላይ መወዛወዝ ጀመርች አዳም
ከታስረችው ዲና ትይዩ ኮማ ውስጥ ያለችውን ሄዋንን አንድ
ጭንብል ያርገ ሰው በህይወት እና በሞት መካከል እስትንፋሷ
የሆነውን ማሽን አዳምን ፍገግ ብሎ በ ሰራውልክ አይነት
አስተያየት እያየው ነቀለው አጭር ጩሀት ሰማ ዞር ሲል ዲናን
ድምፅ በሌለው መሳሪያ አናቷን በታተኑት አዳም
አይይይይይሆሆሆሆንንምምምምምምም ብሎ ጮከ ኧረ ድረሱልኝ
ሰው የለም እንዴ እያለ ቢጮክም ምንም አይነት ሰው ሊደርስለት
አልቻለም አዳምን የሆነ ባትሪ መሰል መብራት ነገር ስውነቱ ላይ
ጭንብል ከለበሱት ውስጥ አበራበት አዳም አቅም አጠርው
መንቀሳቀስም አልቻለም ከቆይታ በኋላ የአንድ ሰው ኮቴ ተሰማው
ይህንን ኮቴ ያውቀዋል ሁለት እግር አንድ ከዘራ ባለ ከዘራው እና
ባለ ብዙ ሀጢያቶች ባለቤት ይህ ሰው ሄዋን ለእዚህ ችግር
እንድትጋለጥ ያረገው ሰው ነው ፈገግ እያለ ወደ አዳም ቀረበው
አዳምም አይሆንምም ብሎ ከህልሙ ነቃ ዲና ደንግጣ በርግጋ
ተነሳች ምንነው ችግር አለ አዳም አለችው እሱም የለም ተኚ
ብሏት በጥድፊያ ሄዋን ጋር ሄዶ በመስታወቱ ያያት ጀመር።
እውነት ቢሆንስ ቆይ ህልሜ ካንቺ ተለይቼ እንዴት እኖራለው ብሎ
ተንስቀሰቀ።

ይህ ሰው ጌዲዬን ይባላል በወንጀል የታወቀ ነገር ግን መፍትሄ
ያልተገኘለት ሰው ለብዙ ህፃናት ደሀዎች እና ፍትህ ፍላጊዎች
እልቂት ተጠያቂ እጁ እስከ ከፍተኛ የወንጀልም ሆነ የቢዝነስ ነክ
ጉዳዎች ላይ የሚረዝም ከፈለገ ምንም ማድርግ የማያቅተው
ህይወት ያለው ሰው የሚታዘዘው ነው። ታዲያ ለእሱ አለታዘዝ ያለ
ስው በህይወቱ ፈርዶ ነው ባአስቃቂ እና በሚዘገንን መልኩ
ያስቃየዋል በቁሙ በህይወት እንዳለ ያለ በለዚያ ፈፅሞ አይርካም
አንድን ሰው ገደለ ማለት በጣም ጥሩ ስራ እንደስራ ነው
የሚስማው ሰውን በቁሙ ማስቃየት በአለም ላይ ለእሱ ትልቅ
ፌሽታ ነው ሁሉም ሰው የእዚህ ስው ስም ሲነሳ ይንቀጠቀጣል።
አዳም በጥብቅና ሙያው ማንም የማይስተካከለው እልልልል
የተባለለት ጠበቃ ነው ስራ የጀመርው ከአመት በፊት ቢሆንም
ባጭር ጊዜ ባጭር የፍርድ ቀጠሮ ብዙ አልበገር ባይ እና ወንጀል
ስርተው የሚሸሽጉ ስዎችን አጋፍጦ ለፍርድ ልኳል ወደ ሚገባቸው
አስናብቶቸዋል ።ጠበቃ አዳም ማለት ለወንጀለኖች ስይጣን ፍትህ
ለተነፈጉ ደሞ መላክ ነው።

ጌዲዮን የአዳምን የጥብቅና ችሎታ እና ዝናውን ሰምቶ በቢዝነስ
ይሁን በማንኛቸውም አይነት ጉዳዮችን አብሮት እንዲሆን በረብጣ
ገንዘብ ድርድር ያቀርብለታል ጊዲዮን በዙሪያው ሌሎች የእራሱ
ጠበቆች ቢኖሩትም የአዳምን ጥብቅና ግን አብዝቶ ፈልጎታል
አዳም ግን የጊዲዮን ድርድር ሆነ ገንዘብ አላማለለውም ጠበቃ
አዳም ለህሊናው የተገዛ ለፍትህ ጥብቅና የቆመ ለእውነት
የሚኖር ሰው ነው ።

ልክ እንደ አዳም በጊዲዮን አልመራ ያለ እና ጊዲዮን በቁሙ
አስቃይቶ የገደለው እስማኤል የተባለ እሳት የላስ ጠበቃ ነበር
እስማኤል የጊድዮንን ትእዛዝ አለመቀበል ብቻ ሳይሆን
ሊያስፈርድበት ሂደት ጀምሮ ነበር በጊዲዮን ሴራነት ሰውን ያለ
ምክንያት በሀሰት በመፍርድ ተብሎ ተከሶ ለእርዥም አመት ታስሮ
የታሰርበት እስር ቤት ውስጥ በጊዲዮን ትዛዝ መሰርት የታሳሪያን
ሻውር ቤት ውስጥ ሞቶ ነበር የተገኘው ይህንን ጠበቃ መጀመሪያ
የሚወዳቸውን ስዎች በመግደል ነበር አይምሮውን የገደለው
ጌዲዮን ይህ ነው ቁመቱ እጅግ የረዘመ የአይኑ ብሌንን ትኩር
ብሎ ለተመለከተው ልክ እንደ በርበሬ የቀላ መልኩም ወደ ጥቁር
ያደላ ሰው ነው።

ጋሞ ጎፋ እንደሆነና ይህንን ፀባዩን ከአባቱ እስከ ሰውነት አቆሙ
እንደወርሰው ይወራል ብዙ ሴቶችን አስርግዞ አረገዝኩ ብለው
ሲነግሩት የፀነሱትን ፇታ ካወቀ በኋላ ሴት ከሆነች ከእነ እናትየው
ይገላታል የተረገዘው ወንድ ከሆነ ግን እስኪወለድ ጠብቆ እሱን
ካልመስለ ይገለዋል ከመሰለ ግን አሳድጎ ገረዱ ያርገዋል
ይህንን ታሪኩን መንጉደኛው ሎሌ በሚል ርእስ ያ እሳት የላስ
ጠበቃው እስማኤል ፅፎታል እንዲፅፍ የረዳው ደሞ የጌዲዮን
አሽከር ነበር፡፡

አዳም ጠረፔዛው ላይ ፒያሳ አራዳ ጋር 9ስአት ጠብቀኝ የሚል
አጠር ያለ ፅሁፍ አገኘ አዳም የሰውየውን ማንነት ሳያውቅ
የተባለበት ቦታደረሰ ምናልባት ፍትህ የተነፈገ ሰው ስለሱ ሰምቶ
ሊያገኘው እንደፈለገ አልተጠራጠረም
ፒያሳ ጋር እንደደረሰ የሆነ ኩትት ያለ ልብስ የለበሰ ሰው ላዳ ይዞ
ና ግባ እኔ ነኝ የጠራውክ ብሎ ካስገባው በኋላ ጭር ያለ ቦታ
ወሰደው ሲደርሱ የተቀመጥከበትን ወንበር ግለጠው እና እየው
ብቻህን ሆነክ ክፈተው ተጠንቀቅ ማንም እንዳያይክ እዚህ ውስጥ
ስለከተትኩህ ይቅር በለኝ ግን እንደምታስተካክለው አውቃለው
አለውና ቤቱን ሳይነግርው ወደ ቤቱ አደርሰው አዳም ቤቴን እና
መስሪያ ቤቴን እንዴት አወቀ ብሎ ለእራሱ ጠይቆ ለስውየው
ሳይጠይቅ ወረደ ቤቱ በጥድፊያ እንደገባ ቦርሳውን ከፈተው ቦርሳ
ውስጥ በብዙ የተለያዩ ልሙጥ እና ባለ መስመር ሉክ ለሁለት
ታጥፈው በእስቴፕራል ሳይሆን በአርንጓዴ ክር የተሰፋ ደብተር አለ
ሳያነበው እየገላለለጠ ማየት ጀመር የብዙ ስው ፎቶዎች እና
ከፎቶዎች ስር ማብራሪያ ተፅፏል ደብተሩን ከደነው እና ቦርሳ
ውስጥ አንድ ተለቅ ያለ ስአት አገኘ በድጋሜ እጁን ሰደደው
የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወረቀቱ እንዲህ ይላል...

ይቀጥላል...

@ethio_leboled
463 views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:01:59 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_6


ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ(የሽዋ ልጅ)



... ይኸውልሽ ከሳመችኝ በኋላ ምንም ያልኳት ነገር የለም ፈዝዤ ነበር
የሳመችውን ጉንጬን ይዤ የቀረውት እሷ ፊት ላይ ግን ስስመኝ
በመፍዘዜ ምክንያት ሳቅ ይታይባታል ደግማ ጠጋ ብላ "ምነው
ችግር አለ?" አለችኝ አይ ስላት እና "ፈዘካል እኮ
እሺ በቃ ቻው እንገናኛለን በቀጣይ ለእኔም ግጥም ገጥመክ ይዘክ
ና እሺ" ስትለኝ "እሺ መቼ አልኳት".... "ነገ ማታ 12 ስአት ላይ እዚህ
አለችኝና አትፍዘዝ ስስምክ ስትፈዝ እኮ ሳቄም መጥቶ ድንጋጤም
ያዘኝ" ብላ በድጋሚ ግንባሬን ግጥም አድርጋ ስማኝ ሄደች ከሄደች
በሆላ ድንጋጤዬ አለቀቀኝም ዲና በወሬው መሀል ገባችና እንዴት
ግን" አለች ምን እንዴት አለው ያኔ ጓደኛዬ የለከፋት ለት ገና ሳያት
እኮ ነው ልቤን የስርቀችው ኡፍፍፍፍፍፍ በጣም ደስስስስ እሚል
ስሜት ነበር የተሰማኝ የምር ከሳመችኝ በኋላ ያለውን ጊዜ ዝም
ብዬ ስስቅ አሳለፍኩት ነገ በድጋሜ ተገናኝተን ግንባሬን እና
ጉንጭኤን በደንብ እንድትስመኝ ምርጥ ግጥም ልገጥምላት ወስኩኝ
ዲና አፉ ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም እሱም በጣም
በተመስጦ ነበር ሲነግራት የነበርው ጉሮሮውን ጠራርጎ ሊያወራ
ሲል "ንገረኛ" አለችው እሱም ልነግሽ እኮ ነው ከዛ ማታ ለእሷ
ግጥም ስፅፍ አመሸው ዲናም ፈጠን ብላ ምን የሚል እስቲ
በልልኝ ስትል ኧረ ተረጋጊ አላትና ወደወሬው ተመለሰ ማታ
ግጥም ገጥሜላት ግጥሙን12 ሰአት ደርሶ እስከማነብላት
ቸኮልኩኝ በጣምም ጓጓውኝ
ሰአተለ እንደምንም ደረሰልኝ እና 11:40 ላይ የግራሩ ዛፍ
ስር ቁጭ ብዬ
ጠበኳት 11:50 ሆነ ሰአቱ አልሄድ አለ በመከራ 12 ስአት ሞላልኝ
አልመጣችም ባትመጭም ቅጠሪኝ አለ ገጣሚው ባትመጣም ስለ
ቀጠርችኝ ደስስ
ብሎኝ ነበር ከባትመጭም ቅጠሪኝ ግጥም ውስጥ
የነፍስ ጥርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
በቆመ አውሎ ንፍስ ተመቶ እንደመውደቅ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የሚያሳቅቅ ነበር እንደሌለ የገጠመው ግጥም ውል አለብኝ
ትዝዝም አለኝ 12:15ሲል ሄዋኔ ጥቁር የቱታ ሱሪ ሌዘር ጃኬት
አድርጋ እስኒከር ጫማ ተጫምታ ስትመጣ አየዋት ልቤ እሷ
በቀረበችኝ ቁጥር እርምጃዋን ባፈጠነችው ቁጥር የእኔም የልብ
ምት ይፈጥን ጀመር በስተመጨርሻ እኔ ካለሁበት ደረሰች እና
ጉንጬን ስማኝ ቀልጠፍ ብል ተቀመጠች እንደተቀመጠች እጇን
ወደፊቴ ዘርጋችው አፍጠጠች አፈጠጥኩባት እ ምን ታፈጥብኛለክ
ልትለኝ ነው እንዴ በል
ግጥሜን ስጠኝ እንደውም አንተ እራስክ አንብብልኝ አለችኝ ከዛ
እኔም ድምፄን ለሰለስ አርጌ ግጥሙን ማንበብ ጀመርኩ ግጥሙ
እንዲህ ይላል ዲና በጣምም ተመስጣ እሺ በልልኝ አለችው
ከግራሩ ዛፍ ስር
ከግራሩ ዛፍ ስር ልክ እንደለመድኩት
እያነበብኩ ሳለ ግጥም የገጠምኩት
በጩከት ውስጥ እና በመመስጥ ውስጥ
አንድ ድምፅ ተስማኝ የሚመስጥ
ድንገት ከየት መጣ ብዬ ደነገጥኩኝ
አንድ ልጅ ነበርች ግጥሜን ስቀኝ
ከተመጥኩበት ከግራሩ ዛፍስር
ከጀመርዬ ሆና ቃላቶችን ሳስር
ልጅት ብቃቴ እጅክ ተደምማ
ጉንጭና ግንባሬን በአድናቆት ስማ
ለኔም ግጠምኝ ብላ ብጠይቀኝ
12 ሰአት ላይ ልጅት ቀጠርችኝ
ትእዛዝንን አክብሬ ይህው ግጥም ገጠምኩኝ
የሚል ነበር እና ልክ ግጥሙን አንብቤ ሰጨርስ አመሰግናለው የኔ
ውድ ብላ ሁለቱን ጉንጮቼን እና ግንባሬን ሳመችኝ ዲናም ወሬውን
እኔ እምለው ሄዋን ግን እንደተርዳዋት በጣም ሰውን መሳም
ትወዳለች አለች አዳምም ቀጠል አድርጓ ሄዋኔ መሳም ትወዳለች
አዎ መሳም ትወዳለች አለ እና ዝም አለ ዲና እሺ ቀጥላ አለችው
አዳምም ወሬውን ቀጠለ ከዛ በነጋታው ጠዋት ክላስ ልገባ ሰል
ሄዋንን ከብዙ ወንዶች ጋር ቆማ ስትሳሳቅ አየዋት ቅናት ቢጤ
ጫር አረገኝ ቆሜ የሚሆነውን ማየት
ጀመርኩ ትንሽ ካወሩ በኋላ ሄዋኔ ሁሉንም እየዞረች ግንባራቸውን
ሰማቸው ሄደች እራቅ ካለች በኋላም እጆን እያውለበለበች
ተሰናብታቸው ወጣች ልከተላት ስለፈለኩኝ
መከተል ጀመርኩኝ። አዳም ዲናን እንደደከማት እያስተዋለ ውይ
በጣም ደከመሽ አይደል እንቅልፍሽ መጥቷል ታስታውቄያለሽ በቃ
ተኚ ነገ እነግርሻለው አላት አይ ንገርኝ አለችና ድርቅ አለች ግን
ደሞ እሱም ድርቅ ብሎ እንድትተኛ ነገራት እሺ ብላ ካመጣችው
አነስተኛ ኩኪስ ውሀ እና ጋቢ ሰጠችው እሱም ወደ ሄዋን ሄዶ
ሄዋንን በተመስጦ እና በፍቅር አይን ማየት ጀመር...


ይቀጥላል...
@ethio_leboled
425 views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:00:09 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

▣ አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣

#ክፍል_5


ደራሲ:- ቤዛዊት ፋንታዬ(የሸዋ ልጅ)



... ተንስቀስቀ ዶክተሩ ከተቀመጠበት እየተነሳ አዳም ላንተ ከባድ
እንደሚሆን አውቃለው ግን ቆፍጠን ማለት አለብክ አለው አዳምም
እንዴት እንዴትትትት አለ በመከራ ዶክተሩ አዳምን አረጋጋው
ከረዳሃት ወደ ድሮ አቆሟ እንደምትመስል ነገረው እና ነገ ማታ
ስትነቃ ቁጥብነት እና ስርአት ባለው መልኩ እንዲያናግራት
አስጠነቀቀው አዳም ምድር የተደፍበት መሰለው ከዶክተሩ ቢሮ
ውልቅ ብሎ ወጣ
ቤተ ክርስቲያን ሄደ እና ሄዋንን ትውስታዋን እንዲመልስ
የሚያደርግ ትግስት እንዲስጠው እና እሷንም እንዲያኖርለት
ለመነው ተማፀነውም ፀሎቱን ሲጨርስ
ወደ ሄዋን ሄደ አያት ከዛም ኮሊደሩ ጥግ ባለ አግዳሚ ወንበር ላይ
ተኝቶ እንቅልፍ ጣለው የነቃው ዲና መጥታ ስትቀስቅስው ነው
ማታ 2 ስአት ላይ በርግጎ ሲነሳ ዲና ፈገግ ብላ አይዞን አለችው
ካጠገብ ተቀመጠች እና ዛሬ እዚህ ነው የማድርው ተረኛ ነሽ
እንዴ አይ አይ እያየከኝ በልብስ ነኝ እኮ እና አላት እናማ
በመጀመሪያ ዛሬ አምሮቦካል መቼም ለሄዋን ነው እንዲ መዋብክ
ሁለተኛ ደሞ በጣም አዝነካል ከቅድሙ ምን ሆነክ ነው ሶስተኛ
ደሞ ከሄዋን ጋር እንዴት እንደተዋወቃቹ ንገርኝ እሱም ቀጠለ
በመጀመሪያ አመስግናለው ሁለተኛ የከፋኝ ደሞ ብሎ እንባውን
አረገፍው ዲና ደነገጠች ምምምምም ምን ሆነክ ነው አለችው
ሁለተኛው ደሞ እናትዬ የኔ ህይወት ቢደርስባት አደጋ ምክንያት
ከአደጋው በኋላም ሆነ በፊት ያለውን ነገር አታስታውስም አለኝ
ዶክተሩ ሶስተኛው ጥያቄሽ ምን ነበር አዎ ትዝ አለኝ ከሄዋኔ ጋር
በደንብ የተዋወቅነው ዩንቨርስቲ ጊቢ ውስጥ ያሉ ልጆች ከጊቢ
ውጪ ድግስ ቢጤ አዘጋጅተው ነበር እና ጓደኛቼን እኔ
እንደማልሄድ ነግሬያቸው ጊቢ ቀረው ግጥም መፃፍ በጣም እወድ
ስለነበር ወደ ማታ 1 ስአት ላይ ከምወደው ዛፍ ስር ተቀምጬ ግጥሜን ገጥሜ ስጨርስ ጮክ ብዬ የማንብ
ልምድ ነበርኝ አንብቤ ስጨርስ ዋው በጣምምምም አሪፍ ነው
ብርቮ የሚል ድምፅ ከኋላዬ ከጭብጨባ ጋር ሰማው የስማውት
ደምፅ በጣምምም ጮክ ያለ እና ጆሮ የሚበሳ ነበር ያቺ ሴት
ሄዋን ነበርች ለካ ከምቀመጥበት ዛፍ ጀርባ ሄዋኔ ነበረች ዛፉ
በጣም ሰፊ ግንድ ስላለው አላየዋትም ነበር ጎበዝ ነክ ብላ ሞቅ
ባለ ድምፅ ግንባሬን እና ጉንጬን ሳመችኝ ዲና በመገርም እንዴ
ሳታቅክ አለችው አዳምም ፍገግ ብሎ አዎ ሳታቀኝ ዲናም ፈገግ
ብላ እና አንተ ምን አለካት እኔ እኔማ እኔማ ስስመኝ ዲና አታጓጓኛ
በእናትክ ንገርኝ እሺ...

ይቀጥላል...
@ethio_leboled
830 views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:00:21 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_4


ደራሲ:-ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ


... አዳም ዶክተሩ ጋር ከመሄዱ በፊት ሄዋን ስትነቃ አበባ መስሎ እሷ
ፊት ለመቅርብ በማስብ እንዳልተጨፈጨፈ ደን የተጠቀጠቀውን
ፂሙን ሊስተካከለው ፀጉሩንም በወጉ ለማድርግ በማስብ ሄዋንን
አይቶ ባይጠግባትም ብዙ ደቂቃ አይቷት ወደ ፀጉር ቤት ከነፈ
በደስታ በሳቂታ ፊት እየተራመደ ከሆስፒታሉ ትንሽ እራቅ ብሎ
ወደሚገኘው ፀጉር ቤት ገባ እና ቁጭ አለ ወረፋው እስኪደርስ
የእሱን እና የሄዋንን
ፎቶዎች እያየ ውስጡ በሀሴት ሞላ ፀጉር ቤት የተከፈተው ሬዲዮ
ላይ አንድ ታዋቂ ዘፋኝ ቃለ ምልልስ እየተደርገለት ነው ስልኩን
በኪሱ ከቶ ቃለ ምልልሱን መስማት ጀመር ጠያቂው ለታዋቂው
ዘፋኝ የሚጠላው ነገርን ጠየቀው ያው ሁሉም የሚለው ግን
የሆነውን ውሽት እንደሚጠላ መለስለት በስተመጨሻ ማስተላለፍ
የምትፍልገው ነገር ካለክ እና አንድ ዘፈን ለአድማጮቻችን
ብታስማልን የማስተላልፈው ነገር እንኳን የለም ዘፈን ደሞ ከእኔ
ሳይሆን ከሌላ ሰው ዘፈን ላንጎራጉር
ታመሽ ታምሜያለው
ስደኝም እንደዛው
ስትሞች ግን አልሞትም
እኔ ምን በወጣኝ
ብሎ እንጉርጉሮውን ገታ። አዳም በጣምም ተናደደ ብሽቅ አለ በገነ... ምክንያቱ ግልፅ ነው የመጀመሪያው ሰው እንዴት
የሚያስተላልፈው መልክት አይኖርም በሚለው ሲሆን ሌላው እና
ዋነኛው ደሞ ለእሱ አይነት አፍቃሪ ልብ ለሚያፈቅራት ሴት
ላበደው ለአዳም
ታመሽ ታምሜያለው
ስድኝም እንደዛው
ስትሞች ግን አልሞትም
እኔ ምን በወጣኝ
የሚለውን ቃል መስማት ያማል አይምሮን አልፎ ውስጥ ድረስ
ልብ ድረስ ገብቶ ያደማል። ፕሮግራም አቅራቢዋም ለመስናበቻ
የሚሆን ዘፈን ብላ
አሜን አሜን አሜንንንን
ልበል እስቲ አሜንንን
የሚለውን የኑዋይ ደበበን ዘፈን የፕሮግራሙ መዝጊያ አረገችው
ቢያንስ ጋባዥዋ በጋበዘችው ዘፍን ንዴቱ ጠፋ ወደ ኋላ ከሄዋን ጋር
ወዳሳለፈው የፍቅር ጊዜ ማስብ ጀመር ከ አመት በፊት ዩንቨርሲቲ
እያሉ ልደቷን ስታከብር ይህንን ዘፈን በማራኪ ድምፁ በ ዩንቨርስቲ
የሙዚቃ ባንድ አጋዥነት በምርጥ እና ጊቢውን ባነጋገረ እና
ባስደመመ መልኩ ዘፍኖ ሰርፕራይዝ አርጓት ነበር
ከዛም ልደቷን ግቢ አክብረው ወጣ ብለው ሲዝናኑ በድንገት
ተንበርክኮ በደስታ የታገቢኛለሽ ጥያቄ አቅርቦላት እሷም ተንበርክካ ተያይዘው
ተላቅስው ጥያቄውን የተቀበለችበትን ጊዜ ከዛ ደሞ እሷም
በተራዋ
አንነጋገርም ጨዋታው ይቅርብኝ
ቁጭ በል ከጎኔ ያይን እራብ አለብኝ
የሚለውን የኩኩ ሰብስቤ ዘፈን ከዘፈኑ ጋር አብራ እየዘፈነች
በፍቅር አይን እንዴት ታየው እንደነበር አስታወስ እና ፍገግም ሳቅ
ሳቅ እያለ ከዋዠቀበት ሀሳብ ነቃ ያነቃው የፀጉር ቆራጩ ድምፅ
ነበር አዳም ደነገጠ ብዙ ጊዜ ጠርቶት እንዳልስማው ተርዳ
እንደማፈር ብሎ ቀና ሲል ና ወርፋክ ደርሷል ብሎ ፀጉር
መታጠቢያ መቀመጫው ላይ እንዲቁመጥ ጋበዘው አዳምም
ቀልጠፍ ብሎ ተቀመጠ ለ2 ወራት ውሀ ያልነካውን ፀጉሩን
አጠበው ለእሱ ፊት የሚሆን ቁርጥ አስመርጦ ተቆርጦ ለ ፁጉር
ቆራጩ ከምስጋና ጋር ክፍያውን እስከ ጉርሻው ሞላ አድርጎ ሰጠብ
ፀጉር ቆራጩም ጎንበስ ቀና ብሎ አመስግኖ አዳምም
በአቆራርጡ ቆራጩም በጉርሻው ተደስተው ተመሰጋግነው ተለያዩ
አዳም
በጣም ሽበላ ሆኖል ያው ከ አንገቱ በላይ ቢሆንም ። አንድ ነገር
እንደሚቀርው አሰበ ልብስ እና ጫማ ልግዛ ወይስ ሄዋኔ
የምትወዳቸውን ልብስ እና ጫማ ላድርግ ብሎ ከራሱ ጋር ትንሽ
ግብግብ ከፈጠር በኋላ በስተመጨርሻ ሄዋኑ የእሱ ውድ
የምትወዳቸውን ለማድርግ ወሰነ ይህን እያስበ ሆስቲታል ደርሰ
ዶክተሩ
ና ያሉበት ስአት ስለደርስ ወደ ዶክተሩ ቢሮ አመራ ሲደርስ አንኳኳ
ኳኳኳኳኳኳኳኳ
ዶክተር "ማነው? ይግብ" አለ "እኔ ነኝ" አለ አዳም ዳክተሩም "ኦኦኦኦኦኦ አዳም ና
ግባ እባክህ
ቁጭ በል አዳም በጣም አምሮብካል ደሞ ዛሬ አሉ አዳምም ያው
ለእሷ ብዬ ነው አለ አዳም ልብ እንደ ከበሮ ለጉድ መምታት ጀመር
አዳም ጉሮሮውን ጠራርጎ
ለምን ነበር የፈለጉኝ ዶክተሩ ርዥምምምም ትንፋሽ ተንፍሰው
ትንፍሻቸውን መልስው ከስበሰብ በኋላ ንግግራቸው እንዲ ሲሉ
ጀመሩ እየውልክ አዳም አሁን በምነግርክ
ነገር በጭራሽ እንዳታዝን እንደውም ጠንካራ ሁን የአዳም የልብ
ምት በጣምም ፍጠነ ልብ በአፉ ሊወጣ ደርሰ እሺ ዶክተር ቀጥሉ
እኛ ሄዋን ብለው አሁንም ረጅም
ትንፋሽ ወስዱ አዳም ሊያብድ ምንም አለቀርውም እና ምን ዶክተር
ንገሩኛ እእእእ
ዶክተር ወሬያቸውን ቀጠሉ ሄዋንንንን አዳም ሰፍ ብሎ ሄዋን ምን
ብሎ አፈጠጠባቸው ሄዋን በደርስባት የመኪና አደጋ ምክንያት
ብለው አሁንም ዝም አሉ
አዳም እራሱን መቆጣጠር አቃተው እኔ ላብድ ነው በሉ ይናገሩ
ምንድነው መሄድ አችልም ሊሉኝ ነው ወይስ ጭንቅላቷ ውስጥ
ደም ፈሷል ስለዚህ አተርፍም የምታያት ዛሬ ማታ ብቻ ነው ልትሉኝ
ነው አለ ዶክተር አይ እሱ አደለም እንደዛ አደለም ሄዋንንን
የምታያት ነገ ነው መዳኒቷን አስተካክዬላት ነገ እንድነቃ
አርጊዋለው ግን ሄዋን ጭንቅላቷ በሀይል ስለተመታ ብሎ ዶክተሩ
ወሬውን ሳይጨርሱ ይህው ብያለው በቃ ትሞታለች ልትለኝ ነው
አደል አለ በለሆሳስ ዶክተርም አይ አይ ሄዋን አልዛይመር ወይም
የመርሳት በሽታ ይዞታል ሰለዚህ
አንተንም ሆነ በዙሪያዋ ያሉትን ነገሮች አታስታውስም አለው አዳም
ስቅስቅ ብሎ አለቀስ እናትዬ መከራሽ በዛ የኔ ህይወት አያለ...

ይቀጥላል...
@ethio_leboled
1.0K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:02:05 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

▣ አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣


#ክፍል_3



ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ( የሸዋ ልጅ)




... ጩኸቱን ሲጨርስ ረዥም ሳቅ ሳቀ። በረዥሙ ተንፍሶ ወደ ቀልቡ ተመለሰ ። ዲና አሁን ላይ ይህቺ ሴት ማን እንደሆነች ልትጠይቀው ወሰነች ። ጉሮሮዋን
ከጠራረገች በኋላ" እእእእእ እስቲ ስለ ሄዋን ንገረኝ አዳም" አለችው
" ምን ልንገርሽ" አላት
"ማለቴ ያው እንዴት እንደተዋወቃችሁ... ፍቅር እንዴት
እንደጀመራችሁ እና እንዴት እንደዚህ ልታፈቅራት እንደቻልክ" ዲና ይህንን ብላ
ቁልቁል አዳምን አየችው ።
ፊቱ በፈገግታ በርቷል ። ልክ እንደ ነፀብራቅ ፈክቷል ።
ባለፈው ፈገግ ካለው ይልቅ ሲስቅ በጣም
እንደሚያምር አወቀች ።
" ኡፍፍፍፍ እሷን ያወቅኩበትን ቀን ላንዴም
አልዘነጋውም ። ከ5 አመት በፊት የካምፓስ ተማሪ ነበርኩ ። 6 ጓደኞች ነበሩኝ ። ከእኔ
ጋር 7 ማለት ነው ። የሁለተኛ አመት ተማሪ ነበርን ። ከእነሱ በጣም የተለየ ፀባይ ነበረኝ ። ማለቴ እነሱ ሴት ማተራመስ እና መላከፍ በጣም ይወዳሉ ። ወሬያቸው ሁሉ
ሰለ ሴት ነው ። እኔ ደግሞ ሀሳቤ ሁሉ መፅሀፎቼ ላይ ነው ። ፀጥ ያለ ቦታ ይመቸኛል ። ግን ጓደኞቼ አብሬያቸው እንድሆን ሲጠይቁኝ እንቢ ማለት አልችልም ። ሄዋኔን
ያየኋት የሁለተኛ አመት ትምህርት ለመጀመር ተማሪው ከቤቱ ወደግቢ
የሚጎርፍበት ሰአት ላይ ነበር ። ጓደኞቼ እንደለመዱት ለመላከፍ ወደሚመቻቸው
ቦታ ሄደው ተደላድለው ተቀምጠው ነበር ። ያኔ እኔም ነበርኩኝ ። አንድ መካከለኛ
ቁመት ያላት በጣም ቀይ እና ፀጉሯ በጀርባዋ የወርደ ግን በቅጡ ያልተያዘ ፀጉር ያላት...የወንድ የሚመስል አለባበስ ለብሳ በአጠገባችን ልታልፍ
ስትል አንዱ ጓደኛዬ "ኧረ ይቺ ልጅ ፍሬሽ ናት መስለኝ አይቼያት አላዉቅም ። እስቲ
ላስደስታት" አለና ድምፁን ሰልከክ አርጎ "እሙዬ ሻንጣውን ላግዝሽ " አላት
እሷም ፈገግ ብላ "አመሰግናለው ወንድሜ አጋዥ አያስፍልግም" አለችው ቀጠል አድርጎ "ወይም አንቺን ተሽክሜሽ ልግባ " አላት...
ጥቂት ሄድ ካለች በኋላ ፊቷን
ፍክት አድርጋ ፈገግ እያለች "አንዴ እስኪ ና " አለችው...
ደስ እያለዉ ወደ እሷ
ቀረበ ። ሌላኛው ጓደኛችን "ኧረ ንቀት እራስሽ አትመጪም እንዴ..ምንሼ ነው" አላት...
እሷም ዝም ብላ ያኛውን ጎደኛችንን በአይኖቾ አታላ አጠገቧ አመጣችው ። ከዛም
በጥፊ ጭንቅላቱን አዞረችበት ። ሁሉም ደነገጡ ። እኔ እራሴም ደነገጥኩ ። 'ትስማኛለህ '
አለች እየጮኸች...
" አንተ ከንቱ.. የማትርባ አፍክህ በከፈትክ ቁጥር ባዶነትህን
ነው የሚያሳየው ። ዳግም እንዲህ ብታደርግ አንላቀቅም ።" ብላው ሄደች... ስታወራ...ጩከቷ አለም ላይ ያለ ሰዉ ድምፅ አዋጥቶ ለእሷ የተሰጣት ይመስላል ።
በጣም በጩከት ነው የምታወራው ። ልጅቷ ከሄደች በኋላ ጓደኛችን በድንጋጤ
ደርቆ ጉንጩን እየሸፈነ መጣ ።
ምን ብለሃት ነው ስንለው...' ለምንድነው
ወንድሜ የምትይኝ ..ይልቅ ማታ አልጋ ይዘን ለምን አናወራም ' ነበር ያልኳት አለ ።
ሁላችንም በጣም ሳቅንበት ። ይቺ ሴት ሄዋን ነበረች ። ሁሉም ሴት
ሲለከፉ እያፈሩ እና እየተሽኮርመሙ ሲሄዱ እራስዋን ያላስበገርችው ሄዋን ናት ።
ሄዋን ልጁን መታው ከመሄዷ በፊት አንድ ቃል ተናግራለች ። "እኔ ሄዋን ነኝ እሺ
የምሽኮርመምልህ ወይም የምፈራህ እንዳይመስልህ ። በጭራሽ እንዳትሳሳት.. ቀና ብለህ እንዳታየኝ ። ተግባባን !! ብላ አስጠንቅቃዉ ነበር ።
በጣም ገርመችኝ... ወኔዋ በእራስ
መተማመኗ እና ሁሉ ነገሯ አስገረመኝ ። ለፍቅር ያጨኋት ማለቴ
በአይነ ህሊናዬ የሳልኳት አይነት ሰው ሳትሆን ግን ልቤን እና ሁሉ ነገሬን በአንድ
ጊዜ ተቆጣጠረችው ።" አለ አዳም ። ፈገግ እያለ ነበር የሚያወራው ።
" በቃ የቀረውን ደግሞ
ሌላ ጊዜ" አላት የእጅ ሰአቱን እየተመለከተ ።
" ኧር አለስማህም... ልቤን
እንደዚህ አንጠልጥለኸዉ ወልፈት የለም ። በቃ እንደውም ዛሬ ሆስፒታል ነው የማድርው።" አለችው ።
አዳም በአግራሞት እያያት "ዛሬ እረፍት አደለሽ እንዴ " አላት
"አዎ ነኝ ግን የእረፍት ጊዜዬን ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ በመስማት ላሳልፍው
ወስኛለሁ" አለችው ።
የመድሀኒት መደብሩ ጋር ደርሱና መድሀኒቱን ገዙ ። መድሀኒቱ በጣም ውድ ነው ። ቢሆንም ግን የገንዘብ ችግር የለበትም ። ገዛና ወደ ሀኪም ቤቱ ተመለሱ ።
ከመድሀኒት ቤቱ እስከ ሆስፒታሉ ምንም ነገር አላወሩም ነበር ። ሆስፒታሉ በር
ላይ ሲደርሱ
ዲና "በቃ አሁን ቤቴ ሄጄ እርፍት ላድርግ..አመሻሹ ላይ መጥቼ
የጀመርክልኝን ትጨርስዋለህ። እንገናኛለን" ብላዉ ተሰናበተችዉ ። ባይኑ ሽኛትና ሄዋን ወደተኛችበት ክፍል አመራ ። ሄዋን አሁንም ኮማ ውስጥ ናት ። ግን ደግሞ
ልትነቃ ትንሽ ለሊት ማታ እና ቀን ወይም ሰአት ነው የቀረው ።
"ሄዋኔ " አለ በለሆሳስ
ደምፅ ...
"አንቺን አለማፍቀር ይቻላል...? እእ አንቺን አለመውደድስ ...? አይ በጭራሽ
አይቻልም ። አዎ አይቻልም.. የኔ አስተዋይ .. የእኔ ጩኸታም.. የኔ አኩራፊ ንቂ ...ንቂልኝ ።
ሄዋኔ ሄዋኔ አንቺ ነሽ ሰላሜ
እናቴ ልበልሽ በቃ ነሽ አለሜ
የፍቅርሽ ወላፈን ከአድማስ ባሻገር
ልቤን አሳመመሙ ለኔ ሳይናገር ።
ኮማ ውስጥ ያለሽው ፍቅሬ ተይ ንቂልኝ
ጨርቄን ጥዬ ሳላብድ ባክሽ ድርሽልኝ ።
እያለ አጠር ያለችውን የግሉን ግጥም በውስጡ አዥጎረጎርው ።
በተመስጦ
እሷን በማየት ግጥሙን ቀጠለዉ...

ትነቂያለሽ ብዬ በተስፋ ልጠብቅ
አትነቂም ብሎ ውስጤ እንዳይጨነቅ።
እያለ በሀዘን ፊት ያያት ጀመር ።
"ትነቂያለሽ ውዴ" አለ በለሆሳስ....
እዚህ ሀስብ ውስጥ ሆኖ ጠና ያለው ዶክተር ትካሻውን ለመጣራት እና
ለማፅናናት ያክል መታ አደረገው።
"ከአንድ ሰአት በኋላ ቢሮ ና" ብለውት ሄዱ...
"ምን ሊሉኝ ነው...? አትተርፍም ትሞታለች ሊሉኝ ነው...? ለምን እንዲህ አዘኑ..? እእእ "

ይቀጥላል...
@ethio_leboled
1.1K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:01:28 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

▣ አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣

#ክፍል_2


ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ



... የዚህችን ሴት ምንነት ለመግለፅ ምን ይሆን የከበደው..? የሚለውን ጥያቄ ሲጮኽ
የሰሙት ሰዎች በውስጣቸው ያለ ማቋረጥ እያሰቡት ነው ። አለሙ ማን ናት
ህይወቱስ ማን ናት?
ድቅደቁ ምሽት ተገፎ ወደ መነጋጋቱ ወስዶታል ። ብርሀን እየመጣ ነው ።
ጨለማው ለውጦ ፀሀይ ቦታዉን ተረክባለች። ኮማ ውስጥ ያለችው
ሴት ቀኑን እና ለሊቱን ያለ ልዩነት በስቃይ ውስጥ ነች።
ማታ ሆስፒታሉን ሲቀውጠው ያደረው ያ ለግላጋ ስውም በእንባ እና በእንቅልፍ
አብጦ አይኑን እያሻሽ ተነስቶ ኮማ ውስጥ ወዳለችው ሴት አመራ ።
በጉጉት እና በናፍቆት ሲከንፍ ሄዶ አያት ። ምንም የተነቃነቀም ሆነ የተለወጠ ነገር
የለም ። ዛሬ ከትላንት ለእሱ የተለየው መሽቶ መንጋቱ ብቻም አይደለም። የሚሳሳላት ሴት በህይወት መኖሯም ተመስገን አስኝቶታል ።
ሰላም ስላሳደራት...ሰላም እንዲያውላት እና እንዲያኖራት ወደ ቤተ ክርስቲያን ፈጣሪዉን ሊያመስገን ፤ ሊማፀን ሄደ ። በሃሳብ ሩቅ ስለነጎደ ረዥሙ መንገድ አልታወቀውም ። በስተመጨርሻ
እራሱን ቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ ላይ አገኘዉ። ሰማይ እና ምድርን..ሙት
እና በህይወት ያሉትን ነገሮችን በሙሉ የማንቀሳቀስ እና የማዘዝ መብት ላለው
ፈጣሪ ስላምታውን አቀርበ ። ወደ ግቢው ዘልቆ ገባና አንድ ድንጋይ
ላይ ቁጭ አለ።

ግማሹ ቁሞ ሌላው ተቀምጦ ከፊሉ ደግሞ ተንበርክኮ ምልጃውን ያደርሳል ። በጉልበቱ ተንበርክኮ አለሙ የሆነችውን.. እስትንፋሱ የሆነችውን ሴት እንዳይወስድበት
ተማፀነው ። ቀጥሎ ዝም ብሎ ቆየ ። ከራሱ ጋርም እንዲ ሲል ሙግት ገጠመ
"ቆይ ፈጣሪ ቂም ያዉቃል እንዴ..? ለምንድነው አዳምና ሄዋንን ይቅር ያላላቸው። አይ..አይ ለነገሩ
አታድርጉ የተባለውን ነገር ስላደረጉ ነው ። ቆይ ታድያ ፈጣሪ ሀጢያት እንደሚሰሩ
ካወቀ ለምን አላስቆማቸውም..? ለነገሩ ማሰቢያ አእምሮ ሰጥቷቸዋል.. ማስብ የእነሱ ድርሻ ነው ። ልንሞት ነገርስ ለምን ተፈጠርን..? ምን ሆኜ ነው ...ፈጣሪ
የፈጠርንኮ ለመግደል ብሎ አይደለም ። እሱማ ያረገው ነገር ቢኖር ነፃነትን
ከእውቀት ጋር መስጠት ነው ። ፈጣሪን ከምወቅስ አታድርጉ ተብሎ ላረግነው እኛ
ለምን ክስ አላቀርብም..? ምን እየሆንኩኝ ነዉ!! ፈጣሪ ፍቅር ነው ።
ጥላቻን እንድናውቅ ያረገን የፍቅርን ሀያልነት ሊያሳየን ስለፈለገ ነው ። አዳም
ብቻውን ቆዝሞ ከራሱ ጋር ያወጋል ። ስለማንም ግድ አልሰጠውም ። የእሱ ሄዋን አሁን አጠገቡ የለችም ።
ወደ ራሱ ተመለሰ በሀዘኑ ምክንያት የተንጨበረረ ፀጉሩን እና ፂሙን በተራ እየዳበሰ ተንጠራርቶ ተነሳ ። ወደ ሀኪም ቤት ተመለሰ።

በጣም ርቦታል መብላት ፍልጓል። ያለ እሷ መብላቱን ሊለምደው አልቻለም ።
ከትላንት ጀምሮ ምግብ በአፉ አልዞረም ። ለመብላት በማስብ ወደ ሀኪም ቤቱ ካፌ ሄደና ተቀመጠ ።

ቀጫጫ ረዘም ያለ አስተናጋጅ ቀልጠፍ ብሎ " ምን ይምጣ ወንድሜ " አለው
"እእ ቀለል ያለ ቁርስ ባንተ ምርጫ ይሁንልኝ" አለው ።
አስተናጋጁም ሲከንፍ ሄዶ ምርጥ ዱለት ከውሀ ጋር አመጣለትና መልካም ምግብ ብሎት ሄደ ። እጁን ታጥቦ ዱለቱን
በፍጥነት በልቶ ጨርሰ ። የራሱን ሆድም በጣም ታዘበው ። "ለካስ ስጋና ነብስ የተለያዩ ናቸው ።" አለ በውስጡ
"እሷ ተኝታ እኔ ግን በላሁ" አለ
ምግብ መቅመሱ በትንሹ ያረጋጋው ይመስላል ። ከበላ በኋላ አረፍ ማለት ቢፈልግም አልቻለም ። ልቡ እና ሀሳቡ ሄዋኑ ጋር ነው ። እርሷ ጋር ሲደርስ ብቻዋን አልነበርችም ። አጭሯ ነርስም
ነበረች ። በውስጡ "ይህቺ ነርስ ቀንና ለሊት ነው እንዴ የምትሰራው" ሲል እያሰበ ተጠጋት ።
በስስ ፈገግታ ስላም ተባባሉ።
ነርሷ አተኩራ እያየችው " ትላንት ግን" አለችና ፀጥ አለች
"ትላንት ምን..?" አላት
"አይይይ በጣም ጮኸክ በስላም ነው..?" አለችው
የትላንቱ ትዕይንት በአይነ ህሊናዋ እየታያት ።
"ልብሽን አሞሽ ወይም ልቡን የታመመ ሰው አጋጥሞሽ ያዉቃል ..?" አላት
" ዉይ አዎ !! ይገርምሃል ጎረቤቴ ልቡን አሞት ነበር ። ማለቴ የልብ ድካም
አለበትና በቃ ሊሞት ለጥቂት ነው የተረፈው " አለችው ።
አዳም ትንሽ ሊስቅም
ቃጣው ። ሌላ ጊዜ ቢሆን በደንብ ይስቅ ነበር ። አሁን ግን የሚስቅበት አንደበት የለውም ።
ፈገግ ብሎ እያያት
" እሱኛውን የልብ ህመም አደለም ያልኩሽ ። በፍቅር ምክንያት ሰለሚታመም
ልብ ነው የጠየቅኩሽ ። ልክ እንደኔ በፍቅር መስቃየት የሚወዱትን.. የሚያፈቅሩትን ስው በቅርብ በአይን እያዩት በእጅ የማይነኩትን ነዉ የምልሽ..የሚወዱትን ሰው ትንፋሽ
ካጠገቡ ሳትርቂም እስትንፋሱን አለመስማት... ድምፁን መራብ በጣም ያማል ። ቅስምን ይስብራል ። ይህንን ህመም . ..
ይህንን ስቃይ ነው ያልኩሽ" አላት
አሳዘናት... ያላትን ነገር
ተረደተዋለች። እጇን ወደእሱ ሽቅብ እየዘረጋች "እንተዋወቅ ዲና እባላለው... ቅር ካላለህ የሁለታችሁንም ስም ብትነግርኝ " አለችው ። ዳግመኛ ስለ ስሟ ስጠይቀው እንደ ማታው እንዳይጮኽ በመፍራት...
የጨበጣትን እጁን ከእጇ አላቀቀና " እኔ
አዳም እባላለሁ። እሷ ደግሞ" አለ አልጋዉ ላይ ዟ ብላ ወደተኛችው ልጅ እየጠቆመ "ሄዋን ትባላለች" ብሎ ሌላ ወሬ ሊያወራ ሲል ተናዳ "አትቀልድ
ባክህ ትክክለኛ ስማችሁን ንገረኝ" አለችው ...
"ማለት?" አላት
"ማለትማ ስማችሁን በስርአት ንገረኝ"
" ነገርኩሽኮ" እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ አንድ ጠና ያለ ዶክተር ሄዋን ክፍል
ገብቶ ካያት በኋላ ወደ አዳም ዞረና "አቶ አዳም ለወይዘሪት ሄዋን መድሃኒት
ያስፍልጋታል ። ነገ ማታ ትነቃለች የሚል ግምት አለኝ "ብሎት ሄደ ...
ነርስ ዲናም እንዳልቀለደ ገባት ። አዳም እና ሄዋን መገጣጠም ነው ወይስ
ለእራሳቸው አውጥተውት ነው..? ብላ ተገረመች ። አዳም በደስታ ጮቤ ረገጠ ። መቼም የሚያየው ያልመስለውን አይን ሊያይ ቀጠሮ ተስጥቶታል ። ሮጥ ሮጥ እያለ መራመድ ጀመረ... ዲና "የት ልትሄድ ነው
አለችው"
"መድሃኒቱን ልገዛ ነዋ " ፊቱ ላይ ደስታ ይነበባል ።
"አብርን እንሂድ " አለችው
ፈገግ ብላ ...
"ስራሽስ? "
"ፈረቃዬን ጨርሻለው። ከመውጣቴ በፊት ላያችሁ ነበር የመጣሁት ።
"እሺ እንሂድ" አላት አዳም እየተጣደፈ
እስታፍ ልብሷን ቀይራ መጥታ መንገድ ጀመሩ ።
መንገድ ላይ "አለሜ ልትነቃ ነው። አዎ ልትነቃ ነው ። እናትዬ ልትነቃ ነው " አለ ጮኽ ብሎ...
ዲና ግራ ገባት ። እንደመሳቅም እየቃጣት
" አረ ባክህ ዝም በል..ቆይ ይህቺ
ሴት ምን አይነት እድለኛ ብትሆን ነው እንዲህ ያለ አፍቃሪ የሰጣት። ...
አይ ሄዋን " አለች በውስጧ ስለሁለቱ ታሪክ ለመስማት እየጓጓች....

ይቀጥላል...

@ethio_leboled
1.3K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:00:37 ​​​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

▣ አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣


#ክፍል_1



ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ
.
.
.
ዛሬ አንድ ግሩም ለግላጋ ስው ኮማ ውስጥ ያለችውን ሴት በክፍሉ ማሳያ በኩል በሀዘን እና በጭንቀት በፍቅር አይን አትኩሮ እያያት ነው ። በጣም
ተመስጧል ። በእርግጠኝነት ይህ ስው የሴቲቱን መንቃት እንደሚጠባበቅ በህይወቱ ምንም ተጠባብቆ
የሚያዉቅ አይመስልም ። አንድ አጠር መጠን ያለች ቀልቃላ ነርስ መጣችና ደንደን ያለውን ትከሻውን መታ አድርጋዉ ከሃሳቡ አነቃችው ። ይህ ስው ከሃሳቡ ቢነቃም የነቃ
አይመስልም ። ይህች ጀርባ መቺ ከማጠሯ የተነሳ ያቀረቀረው አንገቱን ቀና አርጎ መመልከት አልተጠበቀበትም ። ባይኑ ስላምታ ስጥቷት.. ልብ
ሰራቂ የሆነውን ፈገግታዉን በትንሹ የግዱን አሳያት።
" እኔ እምልህ" አለችው አጭሯ ነርስ እሱም ቀጥይ ወሬሽን የሚል በሚመስል
መልኩ አያት "ይህቺ ሴት ምንህ እንደሆነች እስቲ ንገርኝ አለችው "
ረዥም ዝምታ በመካከላቸው ሰፍነ ። ትግስት ያጣችው አጭሯ ነርስ "ምነው ዝም አልክ ...? መቼም ምንህ እንደሆነች ጠፍታብህ እንዳልሆነ ተስፋ አረጋለው ። በቃ ልገምት እእእእ
እህትህ ናት" አለችው...
"አይደለችም" አለ እንባው መተናነቅ የጀመረው ይመስላል...
"እና መቼም ልጅህ አትሆንም" አለችና ፈገግ አለች ። እሱ ግን ስምቶት
ወይስ ችላ ብሎት ፈገግም አላለ...
ፊቱን በአተክሮት አየችው እንደተከዘ ነው ። " እሺ እና ፍቅርኛህ ናት..?" አለችው
"አይ እሷ" አላስጨረሰችውም "እእእ መቼም እናትህ አደለችም ..ወልዳ አንተን
አታደርስ" አሁን የሰማት ይመስላል ፈገግ አለ ።
እሷም "እና ቆይ ሚስትህ ነች ማለት ነዉ ። አለችው...
ዝምም አለ በድጋሜ ። ረዥም ዝምታ
በመሀከላቸው ስፈነ ። አጭሯ ነርስ ግራ ገባት ። ከፊቱ የተኛችውን እንስት ማንነት
ለማወቅ ከፊቷ ከቆመው ሚስኪን ሰው ብጠይቅም መልስ አልሰጣትም ።
" እና ምንህም ካልሆነች እዚህ ምን ትስራለህ...? ወይስ" ስትለው "እንዳጨርሽው በቃ "
አላት እየጮኸ
"እሷ ማለት ለእኔ አለሜ ናት ። ምንህ ነች ስትይኝ ምኔ ነች ልበልሽ...? ሁሉ ነገሬ
ናታ !" የተናነቁት እንባዎች በትንሹ ተከታትሉ። ብዙም ሳይቆዩ እየተሽቀዳደሙ ይፈሱ ጀመር ።
አጭሯ ነርስ በጩኸቱ ተደናገጠች ። በቃላቱም ተገርዠረመች " አለሜ ናት ፤ ህይወቴ ናት ፤ ደስታዬ ናት ፤
ፍቅሬ ናት በቃ ሁሉ ነገሬ ናት ። " አለ መልሶ...
አጭሯ ነርስ አሁን ምኗ እንደሆነ የገባት
ይመስላል ። እየደጋገመ አለሜ ነሽ ፤ አለሜ ነሽ ..አለሜ ናት.. አልተዋትም
አፍቅራታለሁ ። ህይወቴ ናት ።" እንደ መፍክር እየጮኸ መናገር ጀመረ ።
ጭኸቱ በረታ ። ክፍሉን አናወጠው በእዚህ መሀል አጭሯ ነርስ ፈዛ
ደንዝዛ ቀረች ። ጩኸቱ ያስደነገጣት መልሱም ያልጠበቀችው ትመስላለች ። ለቀናት በሀዘን ተክዞ የሷን መንቃት የሚጠባበቀውን ሰው የሀኪም ቤቱ ዘበኞች እና ሁኔታውን እያዩ ሲያዝኑ የነበሩት ሰዎች እያዋከቡ አስወጥተው የሀኪም ቤቱ ግቢ ማረፊያ ወንበር ላይ አስቀመጡት ።
ወደራሱ የተመለስ አይመስልም ። አሁንም አለሜ ነች ፤ ሁሉ ነገሬ !!
ምንህ ናት አትበሉኝ። ሁሉ ነገሬ ናት.. ምንህ ናት እያላቹህ አታስጨንቁኝ ። ስንቴ ነው የምትደጋግሙብኝ ።" ቀስ በቀስ ድምፁ ሰለለ...ድካም ተስማውና ባለበት አግዳሚ ወንበር ላይ ጋደም አለ።
"ዘመድ የለኝም ዘመድ የላትም ። ምንህ ነች አትበሉኝ ..ሁሉ ነገሬ ናት። ይላል አሁንም አልፎ አልፎ ።
ድምፁን እየቀነስ እየቀነሰ በስተመጨረሻ ዝምምም አለ ። ዘበኞችም ፎጣ
ፈላልገው አልብስውት እዛው እንቅልፍ ወሰደው ። ሁሉም በውስጡ ይህቺ ሴት
ማናት ይላል.. እውነትም ይህቺ ሴት ማናት?...

ይቀጥላል...


@ethio_leboled
1.5K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:46:58 ከስር ከተዘረዘሩት ልቦለዶች ብዙ vote ያገኘዉ ማታ ይጀመራል
anonymous poll

አለሜ ነሽ – 86
60%

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ ! – 35
24%

✿የማይፋቅ ስህተት✿ – 22
15%

143 people voted so far.
1.4K views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 07:56:19 Meteken ena nafiban yemetsefut lijoch metsaf selakomu nw betchalen fetenet tolo lemakerb enmokeraln
Eskeza lela arif arif yaleku leboledochn enlekalen
Hasabachun comment lay adersun
1.3K viewsedited  04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ