Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_leboled — ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_leboled — ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_leboled
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.77K
የሰርጥ መግለጫ

🖇✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️🖇
📚 💥 ማምበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️
📚 💥 እውቀት ሃይል ነው‼️ 📚
📚 ለ እውቀት ትክክለኛው ቦታ✅ 📚
📚 በ ቆይታዎ ዘና ይበሉ ለማንኛውም አስተያየት በ 👉@ethioleboledbotላይ ያድርሱን እናመሰግናለን።
Group- https://t.me/ethio_leboled2

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-03 21:46:34 #ምትኬ

ክፍል-12
#ደራሲ_Hila

ብሩክ ላበላብ ሆኖ ከተኛበት ደንግጦ ተነሳ፡፡ ሰአቱን ሲመለከት ከለሊቱ 9:45 ሆኑዋል ወርዶ ውሀ ጠጥቶ ተመልሶ ተኛ አንዳች ነገር ልቡን ደስ አለው፡፡
* * *
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ አንዳች የተለየ ቀለል ያለ ስሜት ነበር ሲሰማኝ የነበረው ብሩኬን መናፈቄ እጅግ በረታ ቢሆንም እንደማገኘው አውቃለሁ ስወጣ በር ላይ እንደሚጠብቀኝ አቅፎ እንደሚስመኝ ከምንም በላይ ሀብሉን በአንገቴ ሲያየው የተሰበረ ልቡን እንደምጠግንለት አቃለው፡፡ ቁርስ ከእናቴ ጋር ተመግቤ እናቴን ተሰናብቼ ስወጣ ብሩኬን በአይኔ ፈለኩት ከበሬ ባሻገር ከሚቆምበት ስፍራ መኪናውን በአየኔ ፈለኩ ግን አልነበረም ልቤ ተጨነቀ ለምን አልመጣም? ማታ አስከፍቼው ይሆን ወይስ ምንድነው የተፈጠረው? በር ላይ የተወሰነ ደቂቃ በሀሳብ እየባከንኩ ቆምኩ ግን የለም በዝግታ መንገዴን ቀጠልኩ የሰፈራችንን መታጠፊያ ጨርሼ ወደ አስፓልት ስወጣ ልቤ በድን ሆነ አይምሮዬ ማሰብ አቃተው የሆነ የሰው ብዛት ብቻ ይታየኛል ቀስ እያልኩ ስጠጋ የብሩኬ መኪና ነበረች ከዛ መላ አካላቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ ላብ በጀርባዬ ኮለል ብሎ መፍሰስ ጀመረ
* * *
"የኔ ልጅ ብሩክ እስቲ ና ተቀመጥ"
"ወዬ እማዬ ቁርስ በልቼ ወጣለሁ ብሌን ላይ መድረስ አለብኝ በጠዋት ላገኛት ፈልጋለሁ"
"እሺ ልጄ እሱን እረዳለሁ ግን ይቺን ልጅ አደራ ፍቅርህ እንደ ጉም እንዳይሆን በነፋስ የሚበተን አደራ ልጄ ከጅህ እንዳታመልጥህ ጠበቅ አርጋት ፍቅርህን በልቧ ላይ በእምነት ስራው ዙፋንህ እንዲሆን እምነትን ሰላምን ፍቅርን አፅንተህ ኑር አደራ"
"እሺ እማዬ በጣም አስፈራራሽኝ ደሞ አንቺ ከጎኔ ካለሽ ሁሉም ይስተካከላል...... በይ እማ ልሂድ እንዳታመልጠኝ ደና ዋይ"
* * *
እያዘገምኩ ሰው አጠገብ ስደርስ ሁሉም ያወራል ግማሹ የራሱን ግምት ይሰጣል አንዱን ጠጋ ብዬ "ይቅርታ አባት ምን ተፈጥሮ ነው ?" አልኩት በልቤ ክፋ እንዳያሰማኝ እየተማፀንኩ
" ምን አውቄ ሚስቱ ናት መሰለኝ መንገድ ምጧ መቶ ነው አሉ? ወይ የዘንድሮ ወንድ በቃ መላ ቅጡ የጠፋበት......." ከዛ በኋላ ሰውየው ያለውን አልሰማሁም በሰው ውስጥ እየተጋፋው ወደ ብሩክ መኪና ተጠጋሁ በዚሁ መሀል አንዱ ከመሀል " እስቲ ገለል በሉ መኪናውን አሳልፉት ነፍሰጡሯን ሆስፒታል ያድርስበት ሆሆሆሆ ዞር በሉ" ሲል ለመኪናው መንገድ ከፈቱለት አጠገቡ ደርሼ መስታወቱን አንኳኳው ቀና ሲል እኔ ነኝ
"ምንድነው?"
"ውይ እናቴ በነብሴ ደረሽ የሆነውን በኋላ ላስረዳሽ አሁን ጊቢና ይቺን ሴት ሆስፒታል እናድርስ"
"እሺ" አልኩት አንዴ እሱን አንዴ እሷን እያየሁ ወደ መኪናው ገባሁ አንድ ሌላ ሰው ጨምረን በአቅራቢያ ወዳለ የግል ሆስፒታል ገባን፡፡
ሆስፒታል ደርሰን አስፈላጊውን ሁሉ አሟላ፡፡ ግራ ቢገባኝም ለመጠየቅ ጊዜ አላገኘሁም ነበር እሷን ማዋለጃ ሲያስገቧት አብራን የነበረችውን ልጅ ዞር ብሎ " ብቻዋን ነው እንዴ የምትኖረው? ማለቴ የልጇ አባት የለም?"
" አለ ለማለት አያስደፍርም ለነገሩ በቁሙ የሞተ ነው እሷን ያሰቃያል እንጂ"
"ማለት አልገባኝም በሽተኛ ነው ወይስ በሀገር የለም"
"ኧረ ሙሉ ጤነኛ ነው በሀገርም አለ ግን ምን መሰለህ ሚስትና ልጆች አሉት በፍቅር አበድኩ ካለና ቅምጡ ካረጋት በኋላ ስታረግዝ ውሻ አረጋት ለምን እንደጠላት ስታጣራ ጉዱን ሰማች ያኔ አለም ጨለመችባት ስራም የላት ብቻ ታሳዝናለች"
አሁን ነገሩ ገባኝ ብሩኬ አያቃትም ግን እንዴት እሱ መኪና ገባች፡፡ እሱን እያሰብኩ ከውስጥ የህፃን ድምፅ ተሰማ ዶክተሩ ወደኛ በመምጣት
እንኳን ደስ አለህ የሴት ልጅ አባት ሆነሀል " አለው ቅናት ተሰማኝ ዞሬ ብሩክን ሳየው "ይቅርታ አባቱ አይደለውም እሷግን ደህናት ?"
"በጣም ይቅርታ አባቷ መስለከኝ ነው....."
"ምንም አይደል ያጋጥማል ዶ/ር"
"አሁን እሷ እና ልጇ ሙሉ ጤነኛ ናቸው ግን ድካም እና የአቅም ማነስ እናትየው ላይ ይታያል በእርግዝና ወቅት ጉዳት ነበረባት ለዛሬ እዚህ አድራ ነገ ትወጣለች መልካም ቀን"
"በጣም እናመሰግና"
በዚህ መሀል አብራን የመጣችው ልጅ ልታያት ወደ ውስጥ ስትገባ ትንሽ የማወራበት ጊዜ አገኘሁ
"ብሩኬ ምንድነው የተፈጠረው ?"
"ይኸውልሽ እናት ወደአንቺ እየመጣሁ መሀል አስፓልት ላይ ሲጯጯሁ አየሁ ለማረጋገጥ ስጠጋ እርዳታ ፈላጊ ሴት ናት በሂወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ልቤ አዘነ መርዳት እንዳለብኝ አሰብኩ ከዛ አንቺ መጣሽ በቃ ይሄነው የተፈጠረው"
"እኔ ደሞ አንተ የሆነ ነገር የሆንክ ነበር የመሰለኝ ከዛ አንዱን ስጠይቀው ምን እንዳለኝ ....." ያለኘኝን ሳላወራ ሳቅ ቀደመኝ በዚህ መሀል ብሩኬ የአንገት ሀብሉን አየው
1.8K viewsedited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:47:00 #ምትኬ
ክፍል11

#ደራሲ_Hila

"ብሌን አፈቅርሻለሁ "
ሲለኝ ደነግጬ በሩን ዘግቼ ገባሁ። መምጣቴን የተመለከተችው እናቴ
"ምትኬ መጣሽ የኔ ልጅ ቀንሽ እንዴት ነበር?"
"ደና እማ ጥሩ ነበር ደክሞኛል ልተኛ ነው እናቴ ደና እደሪ"
ብያት ቶሎ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡ እናቴ ምንም አላለችኝም አልተከተለችኝም
ክፍሌ ገብቼ የሰጠኝን ስጦታ መክፈት ጀመርኩ ምን ይሆን ብዬ እየጓጓሁ ነበር
ስጦታውን ስከፍት ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ AFEKRSHALHU የሚል የወርቅ አንገት ሀብል ነበር በጣም ያምራል እንባዬ በጉንጮቼ ኮለል ብሎ ሲፈስ ታወቀኝ በዛው ቅፅበት የመኝታ ቤቴ በር ተከፍቶ እናቴ ገባች በእጄ የያዝኩትን ሀብል እያየች
"ምትክ ምንድነው የያሽው እስቲ አምጪ ?"
"እማ ብሩክ ነው የሰጠኝ እናቴ ምክርሽን ፈልጋለሁ ያሳለፍኩት ቀን ከባድ ነው እማ" እናቴን እያወራሁ እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ አጠገቤ ቁጭ ስትል ጭኗ ላይ ጭንቅላቴን አስደግፌ ከመጀሪያው ጀምሮ ሁሉንም ነገርኳት፡፡ ታቀዋለች ግን እንዲቀለኝ ነበር ደግሜ የነገርኳት እስክጨርስ ምንም አላለችም ነበር፡፡ ጨርሼ ዝም ስል
"ምትክዬ"
"ወዬ እናቴ "
"አየሽ ፍቅር አስበነው ፈልገነው አይመጣም ደግሞም ገፍተነው አይሄድም አንቺ ለብሩክ የጎደለ ማንነቱን የጠፋ እሱነቱን ሰጠችው በሀብት በዝና የማይገኝ ጎዶሎነቱን ሞላሽለት፡፡ እናቱ ያጣችው የመሰላትን ልጇን የተነጠቀችውን ደሟን በፍቅር አስመለሽላት በመዘናጋት ለነሱ የሰጠሻቸውን ደስታ አንቺ እንዳታጪው ውለታና ፍቅር ለየ ቅል ናቸው አይገናኙም ኧረ እንደውም አንዱ አንዱን ያጠፋዋል ብቻ ግን ልጄ ቆም ብለሽ አስቢ ከራስሽ ተማከሪ ያንቺ ህይወት ነው"
ብላኝ ከተኛሁበት ቀና አርጋ ግንባሬን ሳመችኝ
"ምትክ የኔ ልጅ ጠንካራ ናት በራሷ የምትተማመን ጭምር"
ብላኝ ጥላኝ ወጣች
ትራሴን ታቅፌ ጋደም አልኩ አይምሮዬም ልቤም አንድ መስመር ላይ ተገናኙ ሁለቱም ብሩክን ያስባሉ ያፈቅራሉ ያለምንም ማመንታት ያንገት ሀብሉን ለበስኩት ፍቅሩን ተቀበልኩት

***
"እናቴ በጣም አፈቅርሻለሁ መቼም አልተውሽም አላስከፋሽም ሁሌም ባርያሽ ሆናለሁ"
"ብሩኬ እኔም አፈቅርሀለሁ ይሄ ቦታ ያምራል አይደል"
"በጣም እናቴ አረንጓዴ እኮ ነው በዛላይ የወፎቹ ዜሜ "
" ብሩኬ ፏፏቴዎቹ ድምፃቸው የልጅነት ህልሜ ይህ ቦታ ነበር "
"ብሌን ብሌን ወዴት ሄድሽ እናቴ የትነሽ እባክሽ ነይ ብሌ........ን" ብሩክ ብሌን ከአጠገቡ ምን እንደወሰደበት አጣት ቢጣራ ቢጮህ ቢሮጥ ብሌን ጠፋች "ብሌ.....ን ፍቅሬ ብሌ......ን" ከብዙ ሩጫና ጥሪ በኋላ ራቅ ያለ ቦታ ላይ ከአንድ እድሜያቸው ከገፋ ነጭ በነጭ ከለበሱ የመልአክ አይነት መልክ ካላቸው እናት ጋር በደስታ እየተፍለቀለቀች ታወራለች አጠገብዋ ሲደርስ
"ቆይ ብሌን የት ሄድሽ ይህን ገነት የመሰለ ስፍራ ብቻዬን አስጠላኝ አስደነገጭሺኝ የማጣሽ መሰለኝ እኮ"
"እንዴ ብሩክዬ ስጠራኝ ሰምቼሀለሁ እኮ ደሞ እያወራውህ ስለሆነ ነው"
በዚ መሀል አብረዋት የነበሩት እናት ደስ በሚል አንደበት በሚገርም ቅላፄ በሚጣፍጥ ንግግር
"ልጄ አይዞህ እናቷ ጋር መታ ነው አደንግጥ ደግሞ አትለይህም ተንከባከባት ይቺን እንቡጥ አበባ ሳትፈነዳ እንዳታደርቃት ወፏ በነፃነት እንድትበር ተዋት ያንተ ልብ ጎጆዋ ነው ብትበርም ጎጆዋን ትታ አትሄድም ካላፈረስከው በስተቀር ልጄ እጅህን ስጠኝ.... አንቺም የኔ ልጅ እጅሽን ስጪኝ"
ከዛ የሁለታችንንም እጅ ይዘው አንድላይ አጨባበጡን
"ልጆቼ አትለያዩም በአንድ ታስራችኀል በሉ ሂዱ ብረሩ ሂዱ"
የነበሩበት ቦታ ገደል ሆነ ወደታች ተምዘግዝገው መውረድ ጀመሩ፡፡
ብሩክ ላበላብ ሆኖ ከተኛበት ደንግጦ ተነሳ፡፡ ሰአቱን ሲመለከት ከለሊቱ 9:45 ሆኑዋል ወርዶ ውሀ ጠጥቶ ተመልሶ ተኛ አንዳች ነገር ልቡን ደስ አለው

#ክፍል_12_ይቀጥላል
@mastaweshaye
1.6K views20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:45:53 #ምትኬ
#ክፍል_10
#ደራሲ_Hila
ከመኪና ወርዶ እኔም እንድወርድ ነገረኝ ቤቱ እጅግ ያማረ ነበረ አነስ ያለ የመኖሪያ ቪላ ነው ጊቢው ከግራና ከቀኝ በተለያዩ አበቦች ያጌጠነው የመኪና ማቆሚያ ገራዝም አለው ቤቱየተቀባው ቀለም ከሩቅ ይስባል ብቻ ምን አለፋችሁ የናጠጠ ሀብታም መኖሪያ መሆኑ ገና ሳይጠየቅ ግኡዙ ቤት ይናገራል ይህን በአይምሮዬ እያደነኩ ወደ ሰፊው ሳሎን ስገባ ተከትዬው ስገባ ባየሁት ነገር ደርቄ ቀረሁ
"ብሌን ተዋወቂያት እናቴ ናት ?"
"እማ የነገርኩሽ ልጅ እሷ ነች ልቤን የወሰደችው "
በጣም የደከሙ እርጅና እና ማጣት የተጫናቸው ግን በዘመናቸው ቆንጆ እንደሆኑ የሚያሳብቅ መልክ አላቸው፡፡ በድንጋጤ ቆሜ ቀረሁ ማውራትም መንቀሳቀስም አቃተኝ ለጊዜውም ቢሆን በድን ሆንኩ
"ነይ እስኪ የኔ መልአክ ደግሞ እንዴት ታምራለች"
ይህን ግዜ ብሩክ መደንገጤን ሲያይ እጄን እንደመያዝ ብሎ ከድንጋጤ መለሰኝ አጠገባቸው ሄጄ አጎንብሼ ጉልበታቸውን ሳምኩ ቀና እያረጉኝ
" ተባረኪ ተባረኪ የኔ ልጅ ነይ ከጎኔ ቁጭ በይ" ብለው ከጎናቸው ሶፋው ላይ እንድቀመጥ ጋበዙኝአጠገባቸው ተቀመጥኩ አሁንም እንደ ደነዘዝኩ ነው አሁን ሰራተኛዋ ጠረጴዛውን በምግብ እየሞላችው ነው
"ልጄ ስምሽን ማን አልሽኝ"
"ብሌን... ብሌን ተመስገን "
"እውነትም ብሌን ስምን መልአክ ያወጣዋል አይደል እሚባለው ፈጣሪ ነው ለኔ ብሌን አርጎ የላከሽ አንቺን ባያገኝ ልጄ መች ያስታውሰኝ ነበር"
"እማማ እኔ ምንም እኮ አላረኩም ፈጣሪ ነው የመለሰሎት"
"አይ ልጄ እንደው እረፊ ቢለኝ አይደል አንቺን መልአክ አርጎ የላከልኝ"
በዚሁ መሀል ሰራተኛዋ ምግብ መቅረቡን ነገረችን እና ወደ ጠረጴዛው አመራን፡፡ የቀረበውን የምግብ ብዛት ስመለከት ሌላ የተጠራ ሰው ያለ መስሎኝ ነበር፡፡ ምግቡን ተመግበን ከጨረስን በኋላ ለመጨዋወት ተብሎ ቡና ተፈላ፡፡
አሁን ነበር ጉድ የሰማሁት ነገሮች ከሳቅ ጨዋታ ወደ ለቅሶ የተቀየሩት፡፡ የብሩክ እናት እኔን በግራ እሱን በቀኝ አስቀምጠው ታሪካቸውን ማውራት ጀመሩ፡፡
"እየውላችሁ ልጆቼ ሂወት ነገ ላይ ምን እንደምታስቀምጥ አይታወቅም ብቻ እኛ የመሰለንን እንጓዛለን፡፡ እንግዲ ብሩኬ አልነግርህም ያልኩህን ታሪክ ዛሬ ከብሌን ጋር ልንገርህ አንተን ዳግም የወለደችልኝ እሷ ስለሆነች፡፡
ብለው ፊታቸው ላይ በጣም ከባድ ሀዘን አየሁ ከረጅም ዝምታ በኋላ ንግግራቸውን ጀመሩ
"የብሩክ አባት ሳገኘው እንዴት ጥሩ ሰው ነበር መሰለሽ ያው ከቤተሰብ ኮብልዬ ነው ያገባሁት አባቴ እንድማር ነበር ፍላጎቱ እኔ ፍቅር አይኔንም ጆሮዬንም ደፈነውና ከሱ ኮበለልኩ ከቤተሰብም ተቆራረጥኩ ለ6ወር የነበር ፍቅር ሀገር ያስቀና ነበር እኔም ብሩክን አረገዝኩ ነገሮች ተገለበጡ ፍቅሩ ጥላቻን ሰላሙ ፀብን ተካ መጠጣት ማጨስ ጀመረ እንደምንም ወለድኩ ልጁን ሲያይ ይመለሳል ብዬ ነበር እርሱ ጭራሽ ከቤት አባረረኝ ጎዳና የምሄድበት ስላልነበረኝ ጎዳና ወጣሁ ሰው ቤት ልብስ እያጠብኩ ያገኘውትን እየሰራው ለኔና ለልጄ የምንቀምሰው አገኝ ነበር፡፡ ታዲያ ብሩኬ አንድ አመት ሲሞላው ቤተሰቦቼ አፈላልገው አገኙኚ ለነሱ አንድ ስለነበርኩ አባቴ መሞቱን ስሰማ እናቴም በድንጋጤ ሞተች ያኔ የነበራቸው ሀብት በሙሉ በስሜ ዞረ ያኔ የብሩክ አባት እኔን ፈልጎ የይቅርታ መአት አውርዶ ታረቀኝበሰአቱ የቤተሰቤ ሀዘንም ነበር፡፡ ብቸኝነቱንም ለመተው ስል ይቅርታውን ተቀብዬ አብሬው ሆንኩ ፍቅራችን ተመለሰ ደስታ በደስታ ሆንን አሁን ሁሉም ነገር እንደምፈልገው መሄድ ጀመረ በህግ ተፈራረምን ያኔ ሀብቱን እንዴት አርጎ እንደሆነ ባላቅም በስሙ አዞረው፡፡ ከአንድ አመት በኋላ የድሮ በሀሪው ተመለሰበት ጭራሽ መማታትም ጀመረ ፍቺ ጠየኩ ከዛም በባዶ አባረረኝ 3 አመት ታገልኩ ግን በፍቅር አስክሮ ንብረቱን እንደማልጋራውና የልጄ ማሳደጊያ ይሁን ብዬ እንድፈርም አርጎ ነበር፡፡በቃ ሁሉን ትቼ ጎዳና ገባሁ
ልጄን እንዲያሳየኝ ብለምነውም ዛተብኝ አቅም ስላልነበረኝ ብሩኬን እየተደበኩ ሳየው ለነገሩ በገንዘቤ ልጄን ነበር ያንደላቀቀው ብዙም አልከፋኝም፡፡ መቼም ሙት አይከሰስም አይወቀስም አይደል እሚባለው፡፡ ያው በስቃይ ነው የኖርኩት፡፡ እሱ በኔ ሀብት ሲደላቀቅ እኔ ግን የለት ጉርስ አጥቼ በርሀብ ስንደፋደፍ መኖር እንደሬት ሲመረኝ ሞትን ስናፍቅ ተደብቄ የልጄን ሳቅ ሳይ ተስፋ ይሰጠኛል ዳግም በጠወለገው ልቤ ውስጥ የመኖርን ዘይት አፍስሶ ያለመልመዋል ፈጣሪ ልጄን እንዲጠብቅልኝ እየተማፀንኩ የድህነት ሂወቴን ተያያዝኩት፡፡ አምላክ ይሰማ የለ እኔን ከልጄ ሊያገናኝ አንቺን ላከልኝ ፈጣሪ ይባርክሽ ከላስቲክ ቤት ወደዚህ ቪላ የጨመረኝ አምላክ በሂወትሽ በዘመንሽ ፍቅር ይሙላልሽ ፈጣሪ ወኪል ይዘዝልሽ ደስታን ብቻ ያጋጥምሽ ፈጣሪ ላንቺም አሳቢ ባል የተባረኩ ልጆች ይስጥሽ""
"አሜን አሜን እማማ"
በዚሁ ብዙ ነገር አወራን ሰአቱ መሸ ልሂድ ብዬ ተነሳሁ ሊሸኘኝ ተነሳ እናቱን ተሰናብቼ ወደቤት ሄድኩ የነገሩኝ ታሪክ በጣም ውስጤን ነክቶታል ለብሩክ አዘንኩለት ይበልጥ አፈቀርኩት በልቤ ፍቅሩን እነደተሸከምኩ በሀሳብ እየናወዝኩ ምንም ሳናወራ ሰፈር ደረስን ቤቴ አጠገብ መኪናውን አቁሞ፡፡
"ብሌን አመሰግናለሁ ማወቅ የነበረብኝ ነገር አንቺን ካገኘው ተገለጠልኝ እባክሽ ይቺን ስጦታ ተቀበይኝ "
ብሎ በስጦታ የተጠቀለለ ትንሽዬ ነገር ሰጠኝ ምንም ሳልለው ተቀብዬው መኪናውን ከፍቼ ወረድኩ ልዘጋው ስል
"ብሌን አፈቅርሻለሁ "
ሲለኝ ደነግጬ በሩን ዘግቼ ገባሁ፡፡

#ክፍል_11_ይቀጥላል
@mastaweshaye
1.5K views20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 06:04:36 https://spinformoney.com/8980697759148634
1.5K views03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 06:25:15 #ምትኬ
#ክፍል_10
#ደራሲ_Hila
ከመኪና ወርዶ እኔም እንድወርድ ነገረኝ ቤቱ እጅግ ያማረ ነበረ አነስ ያለ የመኖሪያ ቪላ ነው ጊቢው ከግራና ከቀኝ በተለያዩ አበቦች ያጌጠነው የመኪና ማቆሚያ ገራዝም አለው ቤቱየተቀባው ቀለም ከሩቅ ይስባል ብቻ ምን አለፋችሁ የናጠጠ ሀብታም መኖሪያ መሆኑ ገና ሳይጠየቅ ግኡዙ ቤት ይናገራል ይህን በአይምሮዬ እያደነኩ ወደ ሰፊው ሳሎን ስገባ ተከትዬው ስገባ ባየሁት ነገር ደርቄ ቀረሁ
"ብሌን ተዋወቂያት እናቴ ናት ?"
"እማ የነገርኩሽ ልጅ እሷ ነች ልቤን የወሰደችው "
በጣም የደከሙ እርጅና እና ማጣት የተጫናቸው ግን በዘመናቸው ቆንጆ እንደሆኑ የሚያሳብቅ መልክ አላቸው፡፡ በድንጋጤ ቆሜ ቀረሁ ማውራትም መንቀሳቀስም አቃተኝ ለጊዜውም ቢሆን በድን ሆንኩ
"ነይ እስኪ የኔ መልአክ ደግሞ እንዴት ታምራለች"
ይህን ግዜ ብሩክ መደንገጤን ሲያይ እጄን እንደመያዝ ብሎ ከድንጋጤ መለሰኝ አጠገባቸው ሄጄ አጎንብሼ ጉልበታቸውን ሳምኩ ቀና እያረጉኝ
" ተባረኪ ተባረኪ የኔ ልጅ ነይ ከጎኔ ቁጭ በይ" ብለው ከጎናቸው ሶፋው ላይ እንድቀመጥ ጋበዙኝአጠገባቸው ተቀመጥኩ አሁንም እንደ ደነዘዝኩ ነው አሁን ሰራተኛዋ ጠረጴዛውን በምግብ እየሞላችው ነው
"ልጄ ስምሽን ማን አልሽኝ"
"ብሌን... ብሌን ተመስገን "
"እውነትም ብሌን ስምን መልአክ ያወጣዋል አይደል እሚባለው ፈጣሪ ነው ለኔ ብሌን አርጎ የላከሽ አንቺን ባያገኝ ልጄ መች ያስታውሰኝ ነበር"
"እማማ እኔ ምንም እኮ አላረኩም ፈጣሪ ነው የመለሰሎት"
"አይ ልጄ እንደው እረፊ ቢለኝ አይደል አንቺን መልአክ አርጎ የላከልኝ"
በዚሁ መሀል ሰራተኛዋ ምግብ መቅረቡን ነገረችን እና ወደ ጠረጴዛው አመራን፡፡ የቀረበውን የምግብ ብዛት ስመለከት ሌላ የተጠራ ሰው ያለ መስሎኝ ነበር፡፡ ምግቡን ተመግበን ከጨረስን በኋላ ለመጨዋወት ተብሎ ቡና ተፈላ፡፡
አሁን ነበር ጉድ የሰማሁት ነገሮች ከሳቅ ጨዋታ ወደ ለቅሶ የተቀየሩት፡፡ የብሩክ እናት እኔን በግራ እሱን በቀኝ አስቀምጠው ታሪካቸውን ማውራት ጀመሩ፡፡
"እየውላችሁ ልጆቼ ሂወት ነገ ላይ ምን እንደምታስቀምጥ አይታወቅም ብቻ እኛ የመሰለንን እንጓዛለን፡፡ እንግዲ ብሩኬ አልነግርህም ያልኩህን ታሪክ ዛሬ ከብሌን ጋር ልንገርህ አንተን ዳግም የወለደችልኝ እሷ ስለሆነች፡፡
ብለው ፊታቸው ላይ በጣም ከባድ ሀዘን አየሁ ከረጅም ዝምታ በኋላ ንግግራቸውን ጀመሩ
"የብሩክ አባት ሳገኘው እንዴት ጥሩ ሰው ነበር መሰለሽ ያው ከቤተሰብ ኮብልዬ ነው ያገባሁት አባቴ እንድማር ነበር ፍላጎቱ እኔ ፍቅር አይኔንም ጆሮዬንም ደፈነውና ከሱ ኮበለልኩ ከቤተሰብም ተቆራረጥኩ ለ6ወር የነበር ፍቅር ሀገር ያስቀና ነበር እኔም ብሩክን አረገዝኩ ነገሮች ተገለበጡ ፍቅሩ ጥላቻን ሰላሙ ፀብን ተካ መጠጣት ማጨስ ጀመረ እንደምንም ወለድኩ ልጁን ሲያይ ይመለሳል ብዬ ነበር እርሱ ጭራሽ ከቤት አባረረኝ ጎዳና የምሄድበት ስላልነበረኝ ጎዳና ወጣሁ ሰው ቤት ልብስ እያጠብኩ ያገኘውትን እየሰራው ለኔና ለልጄ የምንቀምሰው አገኝ ነበር፡፡ ታዲያ ብሩኬ አንድ አመት ሲሞላው ቤተሰቦቼ አፈላልገው አገኙኚ ለነሱ አንድ ስለነበርኩ አባቴ መሞቱን ስሰማ እናቴም በድንጋጤ ሞተች ያኔ የነበራቸው ሀብት በሙሉ በስሜ ዞረ ያኔ የብሩክ አባት እኔን ፈልጎ የይቅርታ መአት አውርዶ ታረቀኝበሰአቱ የቤተሰቤ ሀዘንም ነበር፡፡ ብቸኝነቱንም ለመተው ስል ይቅርታውን ተቀብዬ አብሬው ሆንኩ ፍቅራችን ተመለሰ ደስታ በደስታ ሆንን አሁን ሁሉም ነገር እንደምፈልገው መሄድ ጀመረ በህግ ተፈራረምን ያኔ ሀብቱን እንዴት አርጎ እንደሆነ ባላቅም በስሙ አዞረው፡፡ ከአንድ አመት በኋላ የድሮ በሀሪው ተመለሰበት ጭራሽ መማታትም ጀመረ ፍቺ ጠየኩ ከዛም በባዶ አባረረኝ 3 አመት ታገልኩ ግን በፍቅር አስክሮ ንብረቱን እንደማልጋራውና የልጄ ማሳደጊያ ይሁን ብዬ እንድፈርም አርጎ ነበር፡፡በቃ ሁሉን ትቼ ጎዳና ገባሁ
ልጄን እንዲያሳየኝ ብለምነውም ዛተብኝ አቅም ስላልነበረኝ ብሩኬን እየተደበኩ ሳየው ለነገሩ በገንዘቤ ልጄን ነበር ያንደላቀቀው ብዙም አልከፋኝም፡፡ መቼም ሙት አይከሰስም አይወቀስም አይደል እሚባለው፡፡ ያው በስቃይ ነው የኖርኩት፡፡ እሱ በኔ ሀብት ሲደላቀቅ እኔ ግን የለት ጉርስ አጥቼ በርሀብ ስንደፋደፍ መኖር እንደሬት ሲመረኝ ሞትን ስናፍቅ ተደብቄ የልጄን ሳቅ ሳይ ተስፋ ይሰጠኛል ዳግም በጠወለገው ልቤ ውስጥ የመኖርን ዘይት አፍስሶ ያለመልመዋል ፈጣሪ ልጄን እንዲጠብቅልኝ እየተማፀንኩ የድህነት ሂወቴን ተያያዝኩት፡፡ አምላክ ይሰማ የለ እኔን ከልጄ ሊያገናኝ አንቺን ላከልኝ ፈጣሪ ይባርክሽ ከላስቲክ ቤት ወደዚህ ቪላ የጨመረኝ አምላክ በሂወትሽ በዘመንሽ ፍቅር ይሙላልሽ ፈጣሪ ወኪል ይዘዝልሽ ደስታን ብቻ ያጋጥምሽ ፈጣሪ ላንቺም አሳቢ ባል የተባረኩ ልጆች ይስጥሽ""
"አሜን አሜን እማማ"
በዚሁ ብዙ ነገር አወራን ሰአቱ መሸ ልሂድ ብዬ ተነሳሁ ሊሸኘኝ ተነሳ እናቱን ተሰናብቼ ወደቤት ሄድኩ የነገሩኝ ታሪክ በጣም ውስጤን ነክቶታል ለብሩክ አዘንኩለት ይበልጥ አፈቀርኩት በልቤ ፍቅሩን እነደተሸከምኩ በሀሳብ እየናወዝኩ ምንም ሳናወራ ሰፈር ደረስን ቤቴ አጠገብ መኪናውን አቁሞ፡፡
"ብሌን አመሰግናለሁ ማወቅ የነበረብኝ ነገር አንቺን ካገኘው ተገለጠልኝ እባክሽ ይቺን ስጦታ ተቀበይኝ "
ብሎ በስጦታ የተጠቀለለ ትንሽዬ ነገር ሰጠኝ ምንም ሳልለው ተቀብዬው መኪናውን ከፍቼ ወረድኩ ልዘጋው ስል
"ብሌን አፈቅርሻለሁ "
ሲለኝ ደነግጬ በሩን ዘግቼ ገባሁ፡፡

#ክፍል_11_ይቀጥላ
1.7K viewsedited  03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:54:00 #ምትኬ
#ክፍል_9
#ደራሲ_Hila
ይዛው መነፅሯን ፍለጋ ወጣች መነፅሯን ይዛ ተመልሳ አጠገቤ ቁጭ አለች ድምፆን ከፍ አርጋ ማንበብ ጀመረች
"ሰላም ብሌን ለሴት ኧረ እንደውም ለሰው ደብዳቤ ስፅፍ ይህ የመጀመሪያዬ ነው እና ብሌንዬ ብዙም ነገር አላበዘም፡፡ የመጀመሪያ ቀን ሳይሽ በገንዘቤ የምገዛሽ እቃ ነበር የመሰለኝ ለዚህ አመለካከቴ ተጠያቂው አባቴ ነው ከሰው ይለቅ ገንዘብን እንዳከብር አርጎ ያሳደገኝ አንቺን የዛን ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ያልሽኝ ነገር ሂወቴን ቀየረው የሰውን ማንነት ተረድቼ ነው ዛሬ ይህንን ደብዳቤ የፃፍኩት፡፡
አየሽ ብሌን እኔ የተወለድኩት ከአንድ ብር አምላኪ አባትና ከየዋህ እናት ነው፡፡ አብረው ብዙም አልቆዩም የሁለት አመት ልጅ ሳለሁ ተለያዩ እናቴ ለአባቴ ብላ ከሁሉም ሰው ርቃ ስለነበር ከሱ ስትለያይ የምትሄድበት አልነበራትም እኔን በጉልበቱ ወስዶ አሳደገኝ ምንም ነገር ጎሎብኝ አያውቅም ከቀን ወደቀን ሀብታም እየሆነ መጣ እናቴን እንድጠላት የውሸት ታሪኮችን ነገረኝ እኔና አባቴን ለገንዘብ ብላ ጥላን እንደሄደች እኔን ማየት እንደማትፈልግ ለዛም በጥረቱ ሀብታም እንደሆነና ሴት የተባሉ ፍጥረት ሁሉ የብር ጥማት እንዳለባቸው ነገረኝ አምኜው እኔም ብርን ብቻ መከተል ጀመርኩ በብሬ ሁሉነገርን ገዛሁ ግን ሁሌ ጎዶሎ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር ከተወለድኩ በኋላ እናቴን አይቻት አላቅም ለመፈለግም አላስብም ነበር አባቴ ከሞተ በኋላ አንዲት ሚስኪን አሮጊት እናቴ እንደሆነች ነገረችኝ እኔ ግን በዘበኞች አባረርኳት ሁሌ ስትከታተለኝ እናት እንደሌለኝ ነግሬ ደግሜ ባያት እንደማሳስራት ነገሬ አባረርኳት ይህ ከሆነ ከ 6 ወር በኋላ በሂወቴ አንቺ ገባሽ ነገሮችን ቀየርሽ እና ብሌን የጎደለኝን ነገር ሞላሽልኝ ዳግም የወለድሽኝ እናቴ ሆንሽ ሁሉን ነገር ገለባበጥሽው ብርን ሳይሆን ሰውን እንዳከብር አረግሽኝ ብሌን እባክሽ ነገ ከስራ ስትወጪ አንድ ነገር ላሳይሽ ከዛም አጠገብሽ እንዳልደርስ ከፈለግሽ አልደርስም የነገን ብቻ በስተመጨረሻ ስላንቺ አንድ ነገር ተረዳሁ ልቤን እንደቀማሽኝ እወድሻለሁ""
እናቴ አንብባ ስጨርስ ወደኔ እያየች
"ምትኬ ምን እያሰብሽ ነው ልጄ ይሄ እኮ ደስ ይላል አንድ ሰው ባንቺ ምክንያት ተቀየረ፡፡ ታድያ ያስለቅሳል እንዴ"
"እማ ደስታ ነው ያስለቀሰኝ ደግሞም አሳዘነኝ"
"እና ነገ ታገኝዋለሽ የኔ ልጅ
"አዎ እማ አገኘዋለሁ የሚለውን ሰማዋለሁ"
"ጎሽ የኔ ልጅ በይ አሁን ተነሽ ተጣጠቢና አረፍ በይ"
"እሺ እማ ልተኛና ስነሳ እታጠባለሁ"
በይ ተኚ
ግንባሬን ስማኝ ወጣች ከዛ ግን ሀሳቤ ብሩክ ጋር ሄደ ስለ ነገው ማሰብ ጀመርኩ የመጀመሪያ ቀን ትዝ አለኝ የዛሬ ውሎዬም በመሀል እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
በሰመመን የቤቲ ድምፅ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ ረጅም ሰአትነበር የተኛሁት
"መጣሽ ቤቲዬ
"አዎ ተረጋጋሽ? ፊትሽም ደና ነው አሁን"
"አዎ ግን ስለሱ ማሰብ አላቆምኩም በጣም የተጎዳ ነው አባቱ ግን አይገርምም ቤቲዬ በጣም ጨካኝ ነው"
"አዎ ግን ደገሞ ምክንያት ይኖረው ይሆናል"
"ሆሆሆሆ ሰውን ለመጥላት የሚያደርስ የፈለገ ምክንያት ቢኖር ይህን ያህል ክፋ አይኮንም እኮ"
"ፈጣሪ ይቅር ይበለው፡፡ አንቺ ግን ምን አሰብሽ ብሌንዬ "
"አገኘሁና የሚፈጠረውን አያለሁ እንግዲ ነገ"
በዚሁ ብዙ አወራን ደብዳቤውን አብረን ደግመን አነበብነው፡፡ ቤቲም እዚሁ እኔጋ አደረች አይነጋ የለ እሱኑ እያሰብኩ ነጋ፡፡
ስራ ገባሁ እንጂ ሀሳቤ ብሩክ ጋር ነበረ ሰአቱም ከወትሮ በተለየ መልኩ ወደኃላ እንጂ ወደፊት አልሄድ አለ፡፡
መድረስ አይቀር ሰአቴ ደረሰ ቶሎ ቶሎ ብዬ ቤቲን ተሰናብቼ ወጣሁ፡፡ መኪናውን በአይኔ ፈለኩ አጣሁት ተንከራተትኩ አጣሁት ተስፋ ቆርጬ ወደ ቤት ሳመራ ከኋላዬ
"ብሌን" የሚል ድምፅ ተሰማኝ ስዞር ልቤ እኔጋር አልቆየም ዘሎ ወደ እርሱ የሄደ መሰለኝ
"ይቅርታ አረፈድኩ አይደል ስራ ነበረብኝ እንሂድ ፈቃደኛ ነሽ?"
"አዎ ግን የት ነው ምትወስደኝ?"
"እሱን እራስ ታይዋለሽ ከዛ የፈለግሽውን ትወስኛለሽ"
"እሺ እንሂድ ግን አልቆይም እወቅ"
"ችግር የለውም በጊዜ ትመለሻለሽ"
ብሎኝ መኪና ከፍቶ አስገባኝ ናፍቆቴ ደስታዬ ሀዘኔ ፊቴላይ እንዳይታወቅ እየጣርኩ ነው ያለኝ ቦታ እስክንደርስ ብዙ ነገር አወራን አስተዳደጋችንን ስለ ስራው እያወራን የሆነ ቦታ ስንደርስ አቆመው
ከመኪና ወርዶ እኔም እንድወርድ ነገረኝ ቤቱ እጅግ ያማረ ነበረ አነስ ያለ የመኖሪያ ቪላ ነው ጊቢው ከግራና ከቀኝ በተለያዩ አበቦች ያጌጠነው የመኪና ማቆሚያ ገራዝም አለው ቤቱየተቀባው ቀለም ከሩቅ ይስባል ብቻ ምን አለፋችሁ የናጠጠ ሀብታም መኖሪያ መሆኑ ገና ሳይጠየቅ ግኡዙ ቤት ይናገራል ይህን በአይምሮዬ እያደነኩ ወደ ሰፊው ሳሎን ስገባ ተከትዬው ስገባ ባየሁት ነገር ደርቄ ቀረሁ
#ክፍል_10_ይቀጥላል
1.8K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 01:19:58 #ምትኬ

#ደራሲ_HiLa
ክፍል-8
ወደ መፀዳጃ ስገባ በጣም ደንግጬ እግሬ እየተሳሰረ አላስኬድ አለኝ እንደምንም እግሬን ተቆጣጥሬው ደረስኩ ድንጋጤዬን መቆጣጠር አቅቶኝ ሰውነቴ ሁሉ ይንቀጠቀጣል ፊቴን እና እጄን በውሀ አራስኩት በዚ መሀል ቤቲ ከሁዋላዬ መጣች፡፡
"ብሌን በሰላም ነው ስትሄጂ እያየሁሽ ነበር"
"እእእእ ብ..ሩ..ክ.. ብሩክ መጣ አየሁት"
"አይቼዋለሁ ደግሞ አሁን ሄዷል ተረጋጊ በቃ"
"ሄደ? የት? ለምን ሄደ? እንዴት ሳያናግረኝ ይሄዳል?"
"ብሌን ተረጋጊ እንጂምንም ሳታናግሪው የሄድሽው አንቺ እሱ ምን ያርግሽ ቆይ ?"
"አይደለም እኮ ቤቲዬ ድንጋጤዬ እኮ ነው ያስሮጠኝ እሺ ሄደ አሁን?"
"አዎ ውጪ በቃ ወደ ስራሽ ተመለሺ "
መሄዱ በጣም ከፋኝ በራሴም በጣም ተበሳጨሁ እንደምንም ወደ ስራዬ ተመለስኩ
"ብሌን የቅድሙ ልጅ ይህን ወረቀት እንድሰጥሽ ነግሮኝ ነበር አሁኑኑ አንብቢው ብሎሻል"
"የቱ ብሩክ ነው አምጣው"
የልጁን መልስ ሳልጠብቅ ነበር ወረቀቱን ከእጁ ነጥቄ ማንበብ ጀመርኩ ሳላስበው እንባዬ መፍሰስ ጀመረ ይህን ያየችው ቤቲ አጠገቤ መታ ቆማለች አንብቤ እስክጨርስ ጠበቀችኝ ከዛም ከእጄ ነጥቃ ማንበብ ጀመረች ፊቷ ላይ የሀዘን ስሜት እያየሁ ነበር አንብባ ስጨርስ ቀና አለችና
"ብሌንዬ ወደቤት ሂጂ እና እረፊ ስወጣ መጥቼ እንነጋገርበታለን"
ልክ ነሽ መሄዴ ይሻላል
ከዛም አስፈቅጄ ወደቤት ሄድኩ በመንገዴ ላይ ወደኃላ ማየቴ አልቀረም የፃፈው ደብዳቤ ትዝ እያለኝ እንባ አይኔን እየሞላ አስቸገረኝ መሄድ ስላቃተኝ ታክሲ ኮንትራት ይዤ ቤት ደረስኩ ያለወትሮዬ በጊዜ መምጣቴን ያየችው እናቴ
"ምትኬ ምን ሆንሽብኝ አመመሽ የኔ ልጅ?"
እናቴን ሳይ ሆድ ባሰኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ
"ምንድነው ጉዱ ምን ተፈጠረ ልጄን ምን ነካብኝ ማናባቱ ነው ያስከፋሽ?"
"እ...ማ" ሲቃው አላሶራ አለኝ ትቻት ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡ ከሁዋላዬ እየተከተለች
"አንቺ ምትክ ምን ሆንሽብኝ? ማን ተናገረሽ? ምንድነው የሆንሽው? አትናገሪም ዛሬ ደሞ ገንዘብ ጎደለ? ከስራ ተባርሽ ?"
መጨረሻ ደብዳቤውን ሰጠኋት እናቴ እስከ 10 ስለተማረች ማንበብ ትችላለች ተቀብላኝ
"ይሄ ምንድነው ደግሞ?"
"እማ ታስታውሻለሽ እንደውም እዚ ሰፈር ድረስ ተከትሎኝ ድንጋይ ያነሳሁበት ልጅ"
"አዎ ያ እንደውም በመኪና የመጣው ቆንጆ ወጣት ምን ሆነ አሁንም ተናገረሽ ምን አባቱ ነው ሚፈልግብሽ"
አልተናገረኝም እማ ይህን አንብቢና ትረጂዋለሽ ምን እንደሆንኩ"
ይዛው መነፅሯን ፍለጋ ወጣች መነፅሯን ይዛ ተመልሳ አጠገቤ ቁጭ አለች ድምፆን ከፍ አርጋ ማንበብ ጀመረች.......
#ክፍል_9_ይቀጥላል
1.7K viewsedited  22:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 01:19:29 #ምትኬ

#ደራሲ_HiLa

በጣም ተናደድኩ መሳቋ አናደደኝ፡፡ መናገሬ ደግሞ አሳፈረኝ
"ቤቲ ተይው በቃ መናገር አልነበረብኝም እርሽው"
ሳቋን መግታት እያቃታት "ይቅርታ ብሌንዬ በሱ መሸነፍሽ ገርሞኝ እኮ ነው"
አሁንም ንዴቴ መቆጣጠር አቃተኝ መልስ ሳልሰጣት ፊቴን ከስክሼ ቁጭ አልኩ
"በእውነት ይቅርታ ብሌንዬ ንገሪኝ ታቂኝ የለ ሳቅ ይቀድመኝ የለ"
"ተይው በቃ ዝም ብሎ ነገረ ነው ብለሽ አስቢው"
"ውይ በጌታ ይቅርታ ይህን ያህል የተበሳጨሽ አልመሰለኝም"
"እሺ ተቀብያለሁ ግን በቃ ስለ ብሩክ እርሺው ድንገት አስቤው የናፈቀኝ መስሎኝ ነው"
"አይ እንግዲ ብሌን ንገሪኝ አታናጂኝ የምሬን ነው መስማት ፈልጋለሁ"
"እሺ በቃ ሰሞኑን ሙሉ እያሰብኩት ነው አይኑ ራሱ ናፈቀኝ ቤቲዬ ሲከታተለኝ ሊያናግረኝ ሲመጣ ፊቱ ላይ ንቀት አንብቤ አላቅም ቤቲ ስሰድበው እኮ እራሱ ይስቅ ነበር"
"ግን እኮ ብሌን ብሩክ እንኳን ሴት ተናግራው ወንድ ራሱ ቀና ብሎ ካየው ነብር ነበር ሚሆነው በዛላይ ለሰው ልጅ ክብር የለውም እንደውም የሰማሁተን ልንገርሽ 'አንዴ መንገድ ላይ መኪና እየነዳ አንድ ውሻ እና አንዲት እናት ቆመው ያያል ከዛም ዞር ብሎ ምግብ ቤት ፈልጎ ምግብ ገዝቶ ንፅሁን ምግብ ለውሻው ሰታ ሴትየዋን ደግሞ ከሱ የተረፈውን እንድትበላ ነግሯት ሄደ' ሲሉ ሰማሁ እና ብሌንዬ የብሩክ መጥፋት ለበጎ ይሆናል"
"የምር ይህን ያህል የሰውን ልጅ ለምንድነው ሚንቀው"
"እኔጃ ሰው ሰውን ለመናቅ ምክንያት አያስፈልገውም እኮ ብሌንዬ"
"ለሱ እየተከራከርኩ ሳይሆን ክፋ ሰው አይመስልም የተደበቀ ማንነቱ ጥሩ ሰው ይመስላል እውነት"
"ኧረ ጠበቃ መሆን ብሌን ስለማታቂው ሰው እኮ ነው? ለማንኛውም ከመጣ በሀሪውን ታቂዋለሽ ካልመጣ ደግሞ እርሽው"
"ዝም ብዬ ነው ለነገሩ ድንገት ትዝ ብሎኝ ነው"
በዚው ስለ ብሩክ ማውራት አቆሙ፡፡ የብሌን ልብ ግን እዛው ወሬ ላይ ቆመ እቤት ሄዳም ከናቷ ጋር ስትጫወት ከልቧ አልነበረም ደክሟት ይሆናል ብለው አሰቡ፡፡ ግን ቀን ቀንን ሲተካ ልትመለስ አልቻለችም፡፡ ግራ አጋባቸው የልጃቸው ሁኔታ ነገሩ ቢብስባቸው እራት እየበሉ
"ምትኬ ምን ሆነሽ ነው ሰሞኑን ሀሳብ ገብቶሻል እኮ ስራ ቦታ ችግር ገጠመሽ እንዴ ልጄ"
"አይ እማ ስራ በዝቶብኝ ነው ምንም አልሆንኩም አትጨነቂ "
"ከሆነ ጥሩ እራስሽን ጠብቂ ታድያ ገንዘብ እንዳትሳሳቺ"
"እሺ እማ በቃ ልተኛ ደና እደሪ"
"እሺ ደና እደሪ"
ገብቼ ጋደም አልኩ እንጂ ስለዛን ቀን ብሩክን ስለተናገርኩት ነገር ማሰብ አላቆምኩም ምን አልባት ባልናገረው ከአይኔ አይጠፋ ይሆን? ለምን ወደኔ መጣ? ግን ሆንብሎ ቢሆንስ የጠፋው
ብቻ እኔንጃ ይህን እያሰብኩ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ የልብ ምቴ እንደ ድሮ አልሆን አለኝ በጣም ፈራሁ ያለ ወትሮዬ በጠዋት ሻወር ገባሁ አሁንም ግን ያው ነኝ ቁርስ መብላት አቃተኝ ትቼው እናቴን ስሜ ወደስራ ሄድኩ ቢሆንም ግን ልቤ መፍራቱን አልተወም ልብ ምቴ ለራሴ አስፈራኝ
ስራ ገባሁ ቢሆንም የዛሬውን ቀን ተኝቼ ባለፍኩት ብዬ እያሰብኩ ነው እናቴን ምንም ባልነካብኝ ብዬ ፀሎት እያረኩ ነው ስራዬን መስራት አቃተኝ አስፈቅጄ መሄድ እያሰብኩ ነው መልሼ ደግሞ ደንበኞቼን ጨርሼ ወጣለሁ ብዬ አሰብኩ የተሰለፋትን የባንክ ደብተሮች እያየሁ ከዚ በላይ ደንበኛ ባልመጣ ብዬ ፀለይኩ ፍጥነቴ ለራሴ እየገረመኝ ነው ቶሎ አስፈቅጄ መሄድ ስላሰብኩ ቶሎ መጨረስ ፈልጌያለሁ አሁን የመጨረሻውን ደብተር ሳነሳ ገንዘብ ወጪ ማድረጊያ ነው የልቤ ምት ከበፊቱ ጨመረ ስሙን ሳላስተውል ስም ተጣራሁ አጠገቤ መቶ ሲቆም ፎቶውን ለማረጋገጥ ቀና ስል እራሴን ማረጋጋት አቃተኝ ብሩክ ነበር አጠገቤ የነበረውን የስራ ባልደረባዬን ጠርቼ እንዲጨርስ ነግሬው ወደ መፀዳጃ ሄድኩ

ክፍል 8 ይቀጥላል ከተመቻችሁ
#join #share
1.6K views22:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 12:19:15 #ምትኬ
#ደራሲ_HiLa
ክፍል 6
ከዛ ቀን በኋላ ግን በሄድኩበት ብሩክ አለ ከጀርባዬ እንደጥላ ይከታተለኛል እንዳናግረው ይጠይቀኛል ጭራሽ ባንክ ቤቱን እንደ ቤተክርስቲያን በየቀኑ ይመላለስበት ጀመር፡፡ ይግረምሽ ብሎ ጭራሽ ጠዋት ወደስራ ስሄድ በሬ ላይ ቆሞ ይጠብቀኛል ከስራ ስመለስ ተከትሎ ሰፈር ድረስ ይመጣል፡፡ በዚ ነገሩ ቤቲ ቅፅል ስም ሰታዋለች ሁሌ ከሩቅ ስታየው
"ብሌን ጥላሽ መጣ " ትለኝና ያየሚያምር ፍልቅልቅ ሳቋን ትለቀዋለች
ዛሬ ደግሞ ይለይልሽ ብሎ ነው መሰለኝ ስራ ቦታ ቁጭ ብዬ
" ሰላም ብሌን
"ሰላም ምን ልርዳህ"
"ዛሬ ካላናገርሺኝ እመኚኝ ከዚጋር አልሄድም ያማለት ስራሽንም አሰሪም"
"ያምሀል እንዴ ሰውዬ አንተ ማለት የሰው ክብር ስለሌለህ ከአንተ ጋር ማውራት አልፈልግም"
"ቆይ ግን ማነኝ ብለሽ ነው ምታስቢው ሴት እኮ ነሽ"
"ማን መሆኔን ነገርከኝ እኮ እኔ ሴት ነኝ አዎ ሴት ያውም የናቴ ልጅ ለሌላወው መኖር ምክንያት የምትሆን ሴት ነኝ ሰውነት የገባኝ ለሌላው ክብር ያለኝ ንፁህ ሴት ነኝ ከተራ ነገር በላይ ውዱን የሰው ልጅ የማከብር የናቴ ልጅ ነኝ ገባህ ስለዚህ እኔን ለማዋራት በቂ ስብእና የለህም ከቻልክ ምናልባት የሰውን ነገር ስትረዳ እና ሰው ስትሆን አወራሀለሁ አሁን ግን ስራዬን ልስራበት" ብዬው ከወንበሬ ተነስቼ ወደውስጥ ገባሁ ለነገሩ ደንበኛ እስካሁን እኔጋ አልመጣም በዚ ተመስገን እያልኩ መፀዳጃ ቤት ቆይቼ ተመለስኩ ተመስገን የለም ፡፡ ወደቤትም ስንሄድ መንገድ ላይም የለም
"አንቺ ጥላሽ የት ሄደ?"
"አይገርምም ቤቲዬ ጠዋት ከተናገርኩት በኋላ እኮ ነው የጠፋው ኡፍ ቀለል አለኝ ነፃነት ነስቶኝ ነበር"
"ግን ለምን አቀርቢውም ቆንጆ ነው ሀብታምም ነው ሞክሪው"
"እንዴ ቤቲ የሰው ልጅ ሀብቱ ለሰው ያለው ክብሩ ነው እና እሱ ደሀ ነው ለኔ"
በዚሁ እያወራን ወደ ቤት ገባን እናቴን ስሜ እንደተለመደው የቀን ውሎዬን ዘግቤ የናቴን ምክር ተቀብዬ እራት በላንና ቤቲዬ ወደቤቷ ሄደች፡፡
ነግቶ ስራ ልሄድ ከቤት ስወጣ የብሩክ መኪና የለም ያው እፎይ ብዬ ወደስራ ገባሁ በቃ የብሩክ ነገር ከዛ ቀን በኋላ አከተመ፡፡
ቀናት ሳምንታት ወራትም አለፋ ጉረኛው ልኡል ጠፋ ጭራሽ ብር ገቢ የሚያረገው በሰው ነበር፡፡ በጠፋ በሁለት ሳምንቱ እንዲከታተለኝ ናፈኩ ስሄድ ወደኃላ አስሬ ዞራለሁ፡፡ ብቻ ስለሱ አስባለሁ፡፡
"ቤቲዬ ጥላዬ ጠፋኮ አይገርምም"
አዎ አንቺ ልጁ ምን በላው "
"እኔ እንጃለት ባክሽ ተይው እኔዴት ትዝ አለኝ" አልኳት እኔ እኮ ቆየሁ ከናፈኩት
"ናፈቀሽ እንዴ አንቺ ጉደኛ "
ኧረ ቤቲዬ አልናፈቀኝም ደግሞ ሰው መሰለሽ እሱ" ሌላ ጥያቄ እንዳታነሳ ከአጠገቧ ተነሳሁ
ብሩክን በአይኔ ካየሁ 2 ወር ሆነኝ፡፡ ስራዬን በደስታ እየሰራሁ ነው ግን ብሩክን በአይኔ እየፈለኩት ነው፡፡ የመጀመሪያ ቀን የነበረውን ሁኔታ በትዝታ ተመልሼ ለራሴ ፈገግ አልኩ ውበቱ ማንንም ሴት በፍቅር የሚያጠምድ ነበር በዛ ላይ ሀብታም ቆንጆ ነው አለባበሱ ምርጥ ነው፡፡ እሱን እያሰብኩ ፈገግ ስል የቤቲን አጠገቤ መቆም አላስተዋልኩም
"ሄይ ብሌኒዬ ከማ ጋር ነው እንዲህ በሀሳብ የከተምሽው"
"እእእእ መተሻል እንዴ ቤቲዬ ዝም ብዬ ነው ባክሽ"
"አይ ማነው እህቴን ደስተኛ ያረጋት"
"ማንም" አልኩ እንደማፈር ብዬ
"ብሌንዬ ተያ አትዋሺኝ ቤቲ እኮ ነኝ ተሽኮረመምሽ እኮ "
"አትስቂብኝም ልንገርሽ"
"እንዴ አዎ ለምን እስቃለሁ "
"እንትን ማለት በቃ ብሩ......ክ"
"ብሩክ ምን ሆነ የሰማሽው ነገር አለ"
"አይ የለመ በቃ ኡፍፍፍፍ ናፈቀኝ"
ምን ብላ ሳቋን ለቀቀችው፡፡ በጣም ተናደድኩ መሳቋ አናደደኝ፡፡ መናገሬ ደግሞ አሳፈረኝ

ክፍል 7 ይቀጥላል ከተመቻችሁ
#join #share
https://spinformoney.com/8980697759148634
2.0K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 12:18:43 #ምትኬ
#ደራሲ_HiLa
ክፍል 5
ትንሽ እንደተጓዝኩ ቀድሞኝ ከፊቴ መንገዴን ዘጋብኝ ወደኃላ መመለስ አስቤ ነበር ነገር ግን በተፈጥሮዬ መበለጠንም ሽንፈትንም አልወድም ልቤ እየፈራ ነው ግን መጋፈጥ እንዳለብኝ እያሰብኩ ወደፊት ተጠጋሁ፡፡ የመኪናዋ በር ተከፍቶ ከውስጡ የወጣውን ሰው ሳይ ግን እኔ ነብር ሆነኩ የምን ፍራቻ ሁሉ ነገር በአንዴ የተገላቢጦሽ ሆነ ብሩክ ነበር
"አንተ ወራዳ እንደውም በሰፈሬ እንኳን አገኘሁህ ደሞ አታፍርም......" እኔ እለፈልፋለሁ ከዛም ድንጋይ ፍለጋ እሽከረከር ጀመረ በዚህ መሀል
"ቆይ ተረጋጊ እንጂ የመጣሁት ይቅርታ ልልሽ ነው ብሌን አንዴ መረጋጋት ትችያለሽ"
"ትሰማለህ እኔ ያንተን ይቅርታ አልፈልግም ገደል ግባ ከዚህ ሂድ አለበለዚያ በዚህ ድንጋይ ፈነክትሀለሁ"
እየተጨቃጨቅን እናቴ ድምፄን ሰምታ ከቤት ወጥታ ስታየኝ እህል ውሀ የማያሰኝ ድንጋይ ይዣለሁ
"ምትኬ ልጄ ምንድነው ምን ተፈጠረ"
"ምንም እማ ዝም ብዬ ነው" በድነጋጤ ድንጋዩን ጣልኩት፡፡ ዞር ስትል ብሩክን አየችው
"ማነው ይሄ ደሞ ምን አርጎሽ ነው" ብላ ወደእሱ ስትዞር በፍጥነት እጇን ይዤ
"እማ ተረጋጊ ምንም አልተፈጠረም ቤት እንግባና ነግርሻለሁ"
"አትዋሽ ምትክ ምናባቱ አርጊ ብሎሽ ነው?"
"እማ ትሙት ምንም አላረገኝም"
"ከሆነ ማነው?"
"እንግባና ልንገርሽ"
ተያይዘን ገባን ወደ ቤት ብሩክ በድንጋጤ ቀጥ ብለው እንደቆመ ጥለነው ገባን
"በይ ንገሪኝ ማነው?" ያጋጠመኝን በሙሉ ዘርዝሬ ነገርኳትከዛ እናቴ ንዴቷ ጠፍቶ ትስቅ ጀመር
"እንዴ እማ ምን ያስቃል ያወራሁት ነገር አሁን""አይ ምትኬ እኔ ደሞ እኮ አፍኖ ሊወስድሽ መስሎኝ ነበር ከዛ ደግሞ ምንም አላረገኝም ስትይኝ ፍቅረኛሽም መሰለኝ"
"እና እማ ይሄ ነው ያሳቀሽ"
ቀላሉን ነገር አከበድሽው ምትኬ በሂወት እኮ ብዙ ፈተና አለ ትዕግስት ይኑርሽ እንጂ ማለፍንም እወቂ"
እማ በክብሬ እኮ ነው የመጣብኝ
በይ ተረጋጊ በቃ
ከዛ ግን የናቴ ንግግር ትክክል መሆኑን አሰብኩበት፡፡ከዛ ቀን በኋላ ግን በሄድኩበት ብሩክ አለ ከጀርባዬ እንደጥላ ይከታተለኛል እንዳናግረው ይጠይቀኛል ጭራሽ ባንክ ቤቱን እንደ ቤተክርስቲያን በየቀኑ ይመላለስበት ጀመር

ክፍል 6 ይቀጥላል ከተመቻችሁ
#join #share
1.6K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ