Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ ክፍል11 #ደራሲ_Hila 'ብሌን አፈቅርሻለሁ ' ሲለኝ ደነግጬ በሩን ዘግቼ ገባሁ። መ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

#ምትኬ
ክፍል11

#ደራሲ_Hila

"ብሌን አፈቅርሻለሁ "
ሲለኝ ደነግጬ በሩን ዘግቼ ገባሁ። መምጣቴን የተመለከተችው እናቴ
"ምትኬ መጣሽ የኔ ልጅ ቀንሽ እንዴት ነበር?"
"ደና እማ ጥሩ ነበር ደክሞኛል ልተኛ ነው እናቴ ደና እደሪ"
ብያት ቶሎ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡ እናቴ ምንም አላለችኝም አልተከተለችኝም
ክፍሌ ገብቼ የሰጠኝን ስጦታ መክፈት ጀመርኩ ምን ይሆን ብዬ እየጓጓሁ ነበር
ስጦታውን ስከፍት ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ AFEKRSHALHU የሚል የወርቅ አንገት ሀብል ነበር በጣም ያምራል እንባዬ በጉንጮቼ ኮለል ብሎ ሲፈስ ታወቀኝ በዛው ቅፅበት የመኝታ ቤቴ በር ተከፍቶ እናቴ ገባች በእጄ የያዝኩትን ሀብል እያየች
"ምትክ ምንድነው የያሽው እስቲ አምጪ ?"
"እማ ብሩክ ነው የሰጠኝ እናቴ ምክርሽን ፈልጋለሁ ያሳለፍኩት ቀን ከባድ ነው እማ" እናቴን እያወራሁ እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ አጠገቤ ቁጭ ስትል ጭኗ ላይ ጭንቅላቴን አስደግፌ ከመጀሪያው ጀምሮ ሁሉንም ነገርኳት፡፡ ታቀዋለች ግን እንዲቀለኝ ነበር ደግሜ የነገርኳት እስክጨርስ ምንም አላለችም ነበር፡፡ ጨርሼ ዝም ስል
"ምትክዬ"
"ወዬ እናቴ "
"አየሽ ፍቅር አስበነው ፈልገነው አይመጣም ደግሞም ገፍተነው አይሄድም አንቺ ለብሩክ የጎደለ ማንነቱን የጠፋ እሱነቱን ሰጠችው በሀብት በዝና የማይገኝ ጎዶሎነቱን ሞላሽለት፡፡ እናቱ ያጣችው የመሰላትን ልጇን የተነጠቀችውን ደሟን በፍቅር አስመለሽላት በመዘናጋት ለነሱ የሰጠሻቸውን ደስታ አንቺ እንዳታጪው ውለታና ፍቅር ለየ ቅል ናቸው አይገናኙም ኧረ እንደውም አንዱ አንዱን ያጠፋዋል ብቻ ግን ልጄ ቆም ብለሽ አስቢ ከራስሽ ተማከሪ ያንቺ ህይወት ነው"
ብላኝ ከተኛሁበት ቀና አርጋ ግንባሬን ሳመችኝ
"ምትክ የኔ ልጅ ጠንካራ ናት በራሷ የምትተማመን ጭምር"
ብላኝ ጥላኝ ወጣች
ትራሴን ታቅፌ ጋደም አልኩ አይምሮዬም ልቤም አንድ መስመር ላይ ተገናኙ ሁለቱም ብሩክን ያስባሉ ያፈቅራሉ ያለምንም ማመንታት ያንገት ሀብሉን ለበስኩት ፍቅሩን ተቀበልኩት

***
"እናቴ በጣም አፈቅርሻለሁ መቼም አልተውሽም አላስከፋሽም ሁሌም ባርያሽ ሆናለሁ"
"ብሩኬ እኔም አፈቅርሀለሁ ይሄ ቦታ ያምራል አይደል"
"በጣም እናቴ አረንጓዴ እኮ ነው በዛላይ የወፎቹ ዜሜ "
" ብሩኬ ፏፏቴዎቹ ድምፃቸው የልጅነት ህልሜ ይህ ቦታ ነበር "
"ብሌን ብሌን ወዴት ሄድሽ እናቴ የትነሽ እባክሽ ነይ ብሌ........ን" ብሩክ ብሌን ከአጠገቡ ምን እንደወሰደበት አጣት ቢጣራ ቢጮህ ቢሮጥ ብሌን ጠፋች "ብሌ.....ን ፍቅሬ ብሌ......ን" ከብዙ ሩጫና ጥሪ በኋላ ራቅ ያለ ቦታ ላይ ከአንድ እድሜያቸው ከገፋ ነጭ በነጭ ከለበሱ የመልአክ አይነት መልክ ካላቸው እናት ጋር በደስታ እየተፍለቀለቀች ታወራለች አጠገብዋ ሲደርስ
"ቆይ ብሌን የት ሄድሽ ይህን ገነት የመሰለ ስፍራ ብቻዬን አስጠላኝ አስደነገጭሺኝ የማጣሽ መሰለኝ እኮ"
"እንዴ ብሩክዬ ስጠራኝ ሰምቼሀለሁ እኮ ደሞ እያወራውህ ስለሆነ ነው"
በዚ መሀል አብረዋት የነበሩት እናት ደስ በሚል አንደበት በሚገርም ቅላፄ በሚጣፍጥ ንግግር
"ልጄ አይዞህ እናቷ ጋር መታ ነው አደንግጥ ደግሞ አትለይህም ተንከባከባት ይቺን እንቡጥ አበባ ሳትፈነዳ እንዳታደርቃት ወፏ በነፃነት እንድትበር ተዋት ያንተ ልብ ጎጆዋ ነው ብትበርም ጎጆዋን ትታ አትሄድም ካላፈረስከው በስተቀር ልጄ እጅህን ስጠኝ.... አንቺም የኔ ልጅ እጅሽን ስጪኝ"
ከዛ የሁለታችንንም እጅ ይዘው አንድላይ አጨባበጡን
"ልጆቼ አትለያዩም በአንድ ታስራችኀል በሉ ሂዱ ብረሩ ሂዱ"
የነበሩበት ቦታ ገደል ሆነ ወደታች ተምዘግዝገው መውረድ ጀመሩ፡፡
ብሩክ ላበላብ ሆኖ ከተኛበት ደንግጦ ተነሳ፡፡ ሰአቱን ሲመለከት ከለሊቱ 9:45 ሆኑዋል ወርዶ ውሀ ጠጥቶ ተመልሶ ተኛ አንዳች ነገር ልቡን ደስ አለው

#ክፍል_12_ይቀጥላል
@mastaweshaye