Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ #ክፍል_10 #ደራሲ_Hila ከመኪና ወርዶ እኔም እንድወርድ ነገረኝ ቤቱ እጅግ ያማረ ነበረ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

#ምትኬ
#ክፍል_10
#ደራሲ_Hila
ከመኪና ወርዶ እኔም እንድወርድ ነገረኝ ቤቱ እጅግ ያማረ ነበረ አነስ ያለ የመኖሪያ ቪላ ነው ጊቢው ከግራና ከቀኝ በተለያዩ አበቦች ያጌጠነው የመኪና ማቆሚያ ገራዝም አለው ቤቱየተቀባው ቀለም ከሩቅ ይስባል ብቻ ምን አለፋችሁ የናጠጠ ሀብታም መኖሪያ መሆኑ ገና ሳይጠየቅ ግኡዙ ቤት ይናገራል ይህን በአይምሮዬ እያደነኩ ወደ ሰፊው ሳሎን ስገባ ተከትዬው ስገባ ባየሁት ነገር ደርቄ ቀረሁ
"ብሌን ተዋወቂያት እናቴ ናት ?"
"እማ የነገርኩሽ ልጅ እሷ ነች ልቤን የወሰደችው "
በጣም የደከሙ እርጅና እና ማጣት የተጫናቸው ግን በዘመናቸው ቆንጆ እንደሆኑ የሚያሳብቅ መልክ አላቸው፡፡ በድንጋጤ ቆሜ ቀረሁ ማውራትም መንቀሳቀስም አቃተኝ ለጊዜውም ቢሆን በድን ሆንኩ
"ነይ እስኪ የኔ መልአክ ደግሞ እንዴት ታምራለች"
ይህን ግዜ ብሩክ መደንገጤን ሲያይ እጄን እንደመያዝ ብሎ ከድንጋጤ መለሰኝ አጠገባቸው ሄጄ አጎንብሼ ጉልበታቸውን ሳምኩ ቀና እያረጉኝ
" ተባረኪ ተባረኪ የኔ ልጅ ነይ ከጎኔ ቁጭ በይ" ብለው ከጎናቸው ሶፋው ላይ እንድቀመጥ ጋበዙኝአጠገባቸው ተቀመጥኩ አሁንም እንደ ደነዘዝኩ ነው አሁን ሰራተኛዋ ጠረጴዛውን በምግብ እየሞላችው ነው
"ልጄ ስምሽን ማን አልሽኝ"
"ብሌን... ብሌን ተመስገን "
"እውነትም ብሌን ስምን መልአክ ያወጣዋል አይደል እሚባለው ፈጣሪ ነው ለኔ ብሌን አርጎ የላከሽ አንቺን ባያገኝ ልጄ መች ያስታውሰኝ ነበር"
"እማማ እኔ ምንም እኮ አላረኩም ፈጣሪ ነው የመለሰሎት"
"አይ ልጄ እንደው እረፊ ቢለኝ አይደል አንቺን መልአክ አርጎ የላከልኝ"
በዚሁ መሀል ሰራተኛዋ ምግብ መቅረቡን ነገረችን እና ወደ ጠረጴዛው አመራን፡፡ የቀረበውን የምግብ ብዛት ስመለከት ሌላ የተጠራ ሰው ያለ መስሎኝ ነበር፡፡ ምግቡን ተመግበን ከጨረስን በኋላ ለመጨዋወት ተብሎ ቡና ተፈላ፡፡
አሁን ነበር ጉድ የሰማሁት ነገሮች ከሳቅ ጨዋታ ወደ ለቅሶ የተቀየሩት፡፡ የብሩክ እናት እኔን በግራ እሱን በቀኝ አስቀምጠው ታሪካቸውን ማውራት ጀመሩ፡፡
"እየውላችሁ ልጆቼ ሂወት ነገ ላይ ምን እንደምታስቀምጥ አይታወቅም ብቻ እኛ የመሰለንን እንጓዛለን፡፡ እንግዲ ብሩኬ አልነግርህም ያልኩህን ታሪክ ዛሬ ከብሌን ጋር ልንገርህ አንተን ዳግም የወለደችልኝ እሷ ስለሆነች፡፡
ብለው ፊታቸው ላይ በጣም ከባድ ሀዘን አየሁ ከረጅም ዝምታ በኋላ ንግግራቸውን ጀመሩ
"የብሩክ አባት ሳገኘው እንዴት ጥሩ ሰው ነበር መሰለሽ ያው ከቤተሰብ ኮብልዬ ነው ያገባሁት አባቴ እንድማር ነበር ፍላጎቱ እኔ ፍቅር አይኔንም ጆሮዬንም ደፈነውና ከሱ ኮበለልኩ ከቤተሰብም ተቆራረጥኩ ለ6ወር የነበር ፍቅር ሀገር ያስቀና ነበር እኔም ብሩክን አረገዝኩ ነገሮች ተገለበጡ ፍቅሩ ጥላቻን ሰላሙ ፀብን ተካ መጠጣት ማጨስ ጀመረ እንደምንም ወለድኩ ልጁን ሲያይ ይመለሳል ብዬ ነበር እርሱ ጭራሽ ከቤት አባረረኝ ጎዳና የምሄድበት ስላልነበረኝ ጎዳና ወጣሁ ሰው ቤት ልብስ እያጠብኩ ያገኘውትን እየሰራው ለኔና ለልጄ የምንቀምሰው አገኝ ነበር፡፡ ታዲያ ብሩኬ አንድ አመት ሲሞላው ቤተሰቦቼ አፈላልገው አገኙኚ ለነሱ አንድ ስለነበርኩ አባቴ መሞቱን ስሰማ እናቴም በድንጋጤ ሞተች ያኔ የነበራቸው ሀብት በሙሉ በስሜ ዞረ ያኔ የብሩክ አባት እኔን ፈልጎ የይቅርታ መአት አውርዶ ታረቀኝበሰአቱ የቤተሰቤ ሀዘንም ነበር፡፡ ብቸኝነቱንም ለመተው ስል ይቅርታውን ተቀብዬ አብሬው ሆንኩ ፍቅራችን ተመለሰ ደስታ በደስታ ሆንን አሁን ሁሉም ነገር እንደምፈልገው መሄድ ጀመረ በህግ ተፈራረምን ያኔ ሀብቱን እንዴት አርጎ እንደሆነ ባላቅም በስሙ አዞረው፡፡ ከአንድ አመት በኋላ የድሮ በሀሪው ተመለሰበት ጭራሽ መማታትም ጀመረ ፍቺ ጠየኩ ከዛም በባዶ አባረረኝ 3 አመት ታገልኩ ግን በፍቅር አስክሮ ንብረቱን እንደማልጋራውና የልጄ ማሳደጊያ ይሁን ብዬ እንድፈርም አርጎ ነበር፡፡በቃ ሁሉን ትቼ ጎዳና ገባሁ
ልጄን እንዲያሳየኝ ብለምነውም ዛተብኝ አቅም ስላልነበረኝ ብሩኬን እየተደበኩ ሳየው ለነገሩ በገንዘቤ ልጄን ነበር ያንደላቀቀው ብዙም አልከፋኝም፡፡ መቼም ሙት አይከሰስም አይወቀስም አይደል እሚባለው፡፡ ያው በስቃይ ነው የኖርኩት፡፡ እሱ በኔ ሀብት ሲደላቀቅ እኔ ግን የለት ጉርስ አጥቼ በርሀብ ስንደፋደፍ መኖር እንደሬት ሲመረኝ ሞትን ስናፍቅ ተደብቄ የልጄን ሳቅ ሳይ ተስፋ ይሰጠኛል ዳግም በጠወለገው ልቤ ውስጥ የመኖርን ዘይት አፍስሶ ያለመልመዋል ፈጣሪ ልጄን እንዲጠብቅልኝ እየተማፀንኩ የድህነት ሂወቴን ተያያዝኩት፡፡ አምላክ ይሰማ የለ እኔን ከልጄ ሊያገናኝ አንቺን ላከልኝ ፈጣሪ ይባርክሽ ከላስቲክ ቤት ወደዚህ ቪላ የጨመረኝ አምላክ በሂወትሽ በዘመንሽ ፍቅር ይሙላልሽ ፈጣሪ ወኪል ይዘዝልሽ ደስታን ብቻ ያጋጥምሽ ፈጣሪ ላንቺም አሳቢ ባል የተባረኩ ልጆች ይስጥሽ""
"አሜን አሜን እማማ"
በዚሁ ብዙ ነገር አወራን ሰአቱ መሸ ልሂድ ብዬ ተነሳሁ ሊሸኘኝ ተነሳ እናቱን ተሰናብቼ ወደቤት ሄድኩ የነገሩኝ ታሪክ በጣም ውስጤን ነክቶታል ለብሩክ አዘንኩለት ይበልጥ አፈቀርኩት በልቤ ፍቅሩን እነደተሸከምኩ በሀሳብ እየናወዝኩ ምንም ሳናወራ ሰፈር ደረስን ቤቴ አጠገብ መኪናውን አቁሞ፡፡
"ብሌን አመሰግናለሁ ማወቅ የነበረብኝ ነገር አንቺን ካገኘው ተገለጠልኝ እባክሽ ይቺን ስጦታ ተቀበይኝ "
ብሎ በስጦታ የተጠቀለለ ትንሽዬ ነገር ሰጠኝ ምንም ሳልለው ተቀብዬው መኪናውን ከፍቼ ወረድኩ ልዘጋው ስል
"ብሌን አፈቅርሻለሁ "
ሲለኝ ደነግጬ በሩን ዘግቼ ገባሁ፡፡

#ክፍል_11_ይቀጥላል
@mastaweshaye