Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_leboled — ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_leboled — ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_leboled
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.77K
የሰርጥ መግለጫ

🖇✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️✏️🖇
📚 💥 ማምበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️
📚 💥 እውቀት ሃይል ነው‼️ 📚
📚 ለ እውቀት ትክክለኛው ቦታ✅ 📚
📚 በ ቆይታዎ ዘና ይበሉ ለማንኛውም አስተያየት በ 👉@ethioleboledbotላይ ያድርሱን እናመሰግናለን።
Group- https://t.me/ethio_leboled2

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-24 21:31:20 ​​​​ መልካሙ ዶክተር
┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉
የመጨረሻ ክፍል


እራሴን ለማጥፋት እቅድ ሳወጣ በአጋጣሚ እዩኤል የሰጠኝ የአደራው ነገር እና የደብዳቤው ነገር ትዝ አለኝ... በፍጥነት ደብዳቤውን ካስቀመጥኩበት ቦታ አውጥቼ ስከፍት ሁለት ወረቀቶች በውስጡ አሉ... ቶሎ ብዬ አንዱን ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩኝ ደብዳቤው እንዲህ ይላል፦
ደብዳቤውን ከማንበባችሁ በፊት እስቲ ቻናሉን አጋሩ አቤት እናንተ የሚያስከፍል ይመስል ትትስታላችሁ ለማነኛውም ደብዳቤው እንዲህ ይላል
በጣም የምወድህ ምርጥ ጓደኛዬ እንዴት ነህ? እግዚአብሔር ይመስገን እኔ ደህና ነኝ፣ በእርግጥ ስለ አንተ ማንነት ብዙም አላውቅም ግን በዚህች አብረን በሆንበት ጥቂት ወራቶች ውስጥ ከአንተ ብዙ ነገሮችን ተምሬያለሁ ግን አሁን ማውራት የፈለኩት ስለ መልካምነትህ አይደለም፣ ከአንተ ልርቅ መሆኔን ልነግርክ ነው እንጂ! በርግጥ አንተ ምናልባት አንድም ቀን ከእኔ ይርቃል ብለህ ላታስብ ትችላለህ ግን እኔም ግድ ሆኖብኝ ነው ለመራቅ የወሰንኩት ምክንያቱም በአንተ እና በሀረግ ፍቅር መሃል መግባት አልፈልግም ዝም ብዬ እንዳልቀመጥ ደግሞ አቅም አጣሁ፣ ሀረግን በጣም እወዳታለሁ ለሷ ግን ተመንገር የለብህም አንተም እንድታውቅ የፈለኩት ልርቅህ ስለሆነ ምክንያቱን እንድታውቅ ብዬ ነው ይላል ምን? ዶክተር ከእኔ ፍቅር? ቀልድ መሆን አለበት ብዬ በፍጥነት ሁለተኛውን ወረቀት ስከፍት.. እንዲህ ይላል፦ ሁሌም የምወድሽ በልቤ ዙፋን ላይ ለዘላለም ተቀምጠሽ የምትኖሪ የመጀመርያዬም የመጨረሻዬም የልቤ ንግስት የምወድሽ የማከብርሽ ሀረግ ሰላም ላንቺ ይሁን... አንቺን ለመግለጽ ብዙ ቃላቶች አይበቁም እነዚህ ጥቂት ወራቶች አንቺ ከጎኔ ባትሆኝ እንዴት ሆነው ያልቁ ነበረ ብዬ ሁሌም አስብ ነበረ አንቺ ከቨጎኔ ስለነበርሽ ግን ይሄው የመጨረሻው ቀን ደረሰ የኔ ፍቅር በውስጤ ይዤ ለመሞት ያሰብኩ አንድ ምስጢር ነበረ አሁን ግን ላንቺ ጠቃሚ ስለሆነ ለመንገር ወሰንኩኝ እኔ የካንሰር በሽተኛ ብቻ አይደለሁም ትዝ ይልሻል? የዚያን ቀን በጣም ስሜት ውስጥ ከገባን በኋላ ምክንያት ፈጥሬ ጥዬሽ የሄድኩትን ቀን? የዚያን ቀን ጥዬሽ የሄድኩት ስሜት ስለሌለኝ ሳይሆን በደሜ ውስጥ ኤች አይ ሺ ኤድስ ስለነበረብኝ ነው። ደሜ ውስጥ እሱን ተሸክሜ እስከዛሬ አብሬሽ በመኖሬ ራስ ወዳድ ነኝ አይደል? የኔ ፍቅር እውነታውን ያወኩት ፍቅር ውስጥ ከገባን በኋላ ነበረ.. ከዛም ምክንያት ፈጥሬ ካንቺ ለመራቅ አሰብኩኝ በዚህ መሃል ግን ዶክተሩ ይሄን ደብዳቤ ሰጠኝ እኔም ዶክተሩ መልካም ሰው ስለሆነ የሱን መልካምነት በእኔ ምክንያት አንቺም እንድታውቂ ብዬ ዝም አልኩኝ እውነታው ይሄ ነው ፈጣሪ ሁሉንም ነገር ቀድሞውኑ ያውቃል እኔ የምሞተው ብኖርም ተስፋ ስለሌለኝ ነው እራስሽን ጠብቂ የእናቴን ነገር ደግሞ አደራ ሁሌም የምወድሽ የሁልጊዜ አፍቃሪሽ እዬኤል ይላል። ከአይኔ እምባ መውረድ ጀመረ... ለካ ሰውን አውቃለሁ ማለት ውሸት ነው የሰውን ልብ የሚያውቀው አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው። ግን እሱንም መውቀስ አልችልም ምክንያቱም ለኔ ብሎ ያደረገው ነገር ነው የሚወዱትን አጥቶ መኖር በጣም ከባድ ቢሆንም ህይወት ግን ትቀጥላለች እሱ እንዳለውም ሁሉም ነገር ያለ ምክንያት አይሆንም!! እዩኤል ከሞተ ከሁለት ዓመት በኋላ ከዶክተሩ ጋር በፍቅር ማሳለፍ ጀመረን እኔም ቃሉን ጠብቄ ደስተኛ ሆኜ እናቱንም አቅሜ በቻለው መጠን ሁሉ እየረዳው እየኖርኩኝ ነው እናም የምትወዱትን ሰው በአጋጣሚ ብታጡ እንኩዋን ህልሙን ለመኖር ሞክሩ እንጂ ራሳችሁን ወደ መጥፎ ሱስ ወይንም እብደት አስገብታችሁ ነብሱን እረፍት አትንሱት እያልኩ ታሪኬን እዚሁ ልቋጭ።

The end
┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉
┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉
1.4K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:31:07 ​​ መልካሙ ዶክተር
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
ክፍል አስራአንድ


ፍቅር ምነው ደከምክ እንዴ አልከት.... መልስ የለም ፍቅር እናውራ እኔ እንደዚህ አይነት ቀልድ አልወድም አልኩት መልስ የለም... በድንጋጤ ጩኸት ለቀኩት... የሰፈር ሰዎች ሁሉ መምጣት ጀመሩ... ቀድሞ የመጡ ወንዶች እኔን ከእዩኤል አጠገብ አንስተው እነሱ ምን እንደሆነ ማድረግ ጀመሩ... ተውኝ እዩኤል ምንም አልሆነም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ አንዲት እናት ልጄ አሁን እዩኤል አልፏል ከእንግዲህ ተመልሶ መምጣት አይችልም ጠንከር በይ አሉኝ እራሴን ሰትኩኝ... ከዛ በኋላ የሆነውን ነገር ብዙም ማስታወስ አልችልም፣ ብቻ ምንም ስሜት የሌላኝ ኦና ሆንኩኝ ከአይኔ እምባ ይወርዳል አፌ ግን በዝምታ ተወጠ ትላንት በህመም ጊዜ በዶ የነበረው ቤት በሞቱ ቀን ሞላ ትላንት በህመሙ ጊዜ ቤት ውስጥ በሩን ዘግቶ ይኖር የነበረ ሰው ሁሉ ዛሬ በሞቱ ቀን መጥቶ ስራ መስራት ማልቀስ ጀመረ.... በህይወት እያለ ዞር ብሎ እንኩዋን አይቶ የማያውቁ ሰዎች ዛሬ ለሞተ ስጋው ይሁን ወደ አምላኩ ለሄደው ነብሱ እኔ አላውቅም ብቻ ሽር ጉድ ይላሉ ይሄ ባህል ግን ምን አለ ብለወጥ? ለነገሩ ይሄ ባህል ሳይሆን እርግማን ነው የሞተውን ሰው መቅበሩ ጥሩ ነገር ቢሆንም ከመቅበር ይልቅ ግን በህይወት እያለ መርዳት የተሸላ ነገር ነው። አበድኩኝ ወዲህ ወዲያ አልኩኝ... የኔ እምባ የኔ እብደት ግን አንዴ ለሄደው ሰው ምንም እርዳታ መስጠት አልቻለም እዩኤል ልቤን ተስፋዬን ሁሉንም ነገሬን ይዘው ማንም ወደ ማይቀርበት መቃብር ወረደ። እኔም ትዝታውን ፍቅሩን አደራውን ይዤ ብቻዬን ቀረሁ... ህይወት አንደወዛ ልክ እንደ ቀልድ በቀላሉ እንደዚህ መጨረሻውን አገኝቶ ይሄዳል ብሎ ማን አስቦ ያውቃል? ሁሉም በሀብት ላይ ሀብት በጥላቻ ላይ ጥላቻ ለመጨመር እንቅልፉን ትቶ ቀን ማታ ሳይል ይሮጣል እንጂ! ማን ጥላቻን በፍቅር ለማለውጥ ሮጦ ያውቃል? ለቅም በቀል ሲል እረፍት አጥቶ ይኖራል... ,ህይወት ግን እንደዚህ ናት በጣም በጣም አጭር! ሞት የሚባል ነገር አለ ከብዙ ህልም ከብዙ እቅድ ከብዙ ምቾት በአንዴ መጥቶ ሁሉንም ትተህ ና እንሂድ የሚል ጀግና ማንም እንቢ ማለት አይችልም ታድያ ለምንድነው ጥላቻው? ታድያ የምንድነው ጀግንነቱ? ታድያ የትኛው ነው ትልቁ ዘር? ታድያ የትኛው ነው የአንተ ጉልበት? ፍቅር ማሸነፍ የልቻለውን ሞት በዚህች ምድር ላይ ምንም ማሸነፍ አይችልም። ከአንድ ስምንት የሰዎች ጋጋታ በኋላ እኔ እና ሁለቱ እናቶቼ ብቻ ቀረን... ሰው ሁሉ አንድ በአንድ እያለ ከቤቱ ወጥቶ አለቀ። ህይወት አስጣለኝ መኖር ሰለቸኝ ለከ ተስፋ ከሌላት ህይወት መኖርን እንደዚህ ስልችት ትላለች እንደዚህ እያልኩ አንድ ወር ደረስኩኝ... ከአንድ ወር በኋላ ቆይ በምድር ላይ የኔ የሚለውን ነገሮች አጥቼ መኖር ምን የምሉት ነገር ነው የሚል ሃሳብ በተደጋጋሚ መምጣት ጀመረ እራሴን ለመጥፈት እቅድ ስያወጣ በድንገት አእምሮዬ ላይ የእዩኤል አደራው እና የደብዳቤው ነገር ትዝ አለኝ በፍጥነት ደብዳቤው ያስቀመጥኩበት ቦታ ሄድኩኝ
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
የመጨረሻ ክፍል ከ ነገ ማታ ┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
1.3K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:03:53 ​​ መልካሙ ዶክተር
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
ክፍል አስር

አሁን ቀኑ አልደረሰም አለኝ እኮ ቀኑ መቼ ነው አልኩት ቀኑ....በአንድ አጋጣሚ በጣም ከፍቶሽ መፍትሄ ስታጪ ደብዳቤውን ከማንበብሽ በፊት የትኛውም ውሳኔ ላይ አትድረሽ ቀድመሽ ደብዳቤውን ማንበብ አለብሽ አለኝ እሺ ፍቅር አንተው እንዳልከው አደርጋለሁ ብዬ ደብዳቤውን ተቀብዬ ቤት ሄድኩኝ.. .. ደብዳቤው ውስጥ ያለውን ነገር የማወቅ ጉጉት እረፍት ቢነሳኝም ቃል ግን ቃል ነውና በአንድ ጥሩ ቦታ ላይ አስቀመጥኩት ዶክተር አንድ ቀን ስልክ ደውሎ እዩኤል እንዴት ነው አለኝ ምንም አዲስ ነገር የለም ግን በድጋሚ ሆስፒታል መሄድ አለበት እናቴ ብሩን ለመስጠት ቃል ገብታለች አልኩት የግድ መሄድ አለበት ካልሽ ችግር የለም እኔም በቻልኩ መጠን ለመርዳት እሞክራለሁ እንደውም ነገ ጠዋት መኪና ይዤ እመጣለሁ ከዛም አንቺ የፈለግሽበት ሆስፒታል ሁሉ ይዘን እንሄዳለን አለኝ ዶክተር በጣም አመሰግናለሁ ብዬ ስልኩን ዘጋውት በልቤ ተመስገን አምላኬ ብሩ አሁን ተገኝቶዋል... እዩኤል መቼም አይሞትም ብዬ ተመልሼ ወደ እዩኤል ሄድኩኝ ዛሬ ከእሱ ጋር ብዙም ቁጭ አላልኩም.. ቤት ውስጥ የቆሸሸ እቃ ምናምን ሞልቶ ነበር እቃዎችን አጥቤ ቤቱን አስተካክዬ ወደ ቤት ተመልሼ ልመጣ ስል ፍቅር የሚል ድምፅ ሰማሁ... አቤት ብዬ ስሄድ.. ለምን ጥለሽኝ ትሄጃለሽ አለኝ አይይይ ፍቅር እናቴ ቤት ውስጥ ይጠብቁኛል ብዬ እኮ ነው አልኩት አይዞሽ አሁን ጥቂት ጊዜ ነው የቀረኝ ግን እኮ ፍቅር በጣም ነው የምወድሽ አለኝ የኔ ውድ እኔም በጣም እወድሃለሁ አልኩት እስኪ በተግባር አሳዪ ቢሉሽ ምን ታደርጊልኝ ነበረ ብሎ ጠየቀኝ የመጨረሻ ምንያህል እንደምወድህ ለማሳየት ሞት እንኳን ቢሆን እሞትልህ ነበረ አልኩት በጣም ደንግጦ.... ፍቅር ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትዪ አለኝ የምትወጅኝ ከሆነ እኔ በሌለውበት እኔ ለምወደው ነገር ጥንቃቄ ማድረግ ነው ሞትሽ ማለት እኮ እኔን አትወጅኝም ማለት አይደል አለኝ እኮ አንተ ምንድነው የምትወደው አልኩት እናቴን ነዋ! እኔ በሌለውበት እሷን መንከባከብ የሚችል ሰው የእውነት ይወደኛል ማለት ነው ጥሏት የሞተ ሰው ግን እኔንም አይወደኝም ማለት ነው አለኝ ስለ ምን ሞት የምታወራው አሁን ስለ ሌላ ነገር እናውራ አልኩት እናትህማ ለኔም እናቴ ናት ግን አደራ ስለ ሞት አታውራ አልኩት በጣም ደስ አለው ፍቅር ብሎ እጄን ያዘኝ.... እጁ በጣም ቀዝቅዞ ነበረ... ፍቅር ለምንድነው እጅህ እንደዚህ ቀዝቃዛ የሆነው አልኩት መልስ የለም.... ፍቅር ምነው ደከምክ እንዴ አልኩት... መልስ የለም... ፍቅር አውራ እንጂ እኔ እንደዚህ አይነት ቀልድ አልወድም አልኩት.... መልስ የለም... በድንጋጤ ጩኸቴን ለቀቅኩት
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
ይቀጥላል.. አሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ።
1.4K views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:02:54 ​​ መልካሙ ዶክተር
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
ክፍል ዘጠኝ


ዋውውውው በጣም ደስ አለኝ በልቤ ዶክተሩ ውሸታም ነው አልኩት ትንሽ አብረን ከተጫወታን በኋላ እዩኤል በአፉ ደም መትፈት ጀመረ... ፍቅር ፍቅር ደም እኮ ነው የተፈው አልኩት ታድያ ምነው አዲስ ሆነብሽ አለኝ ማለት እንዴት አይሆንብኝም አልኩት አይይይይ የተመመ ሰው ብዙም ጊዜ ደም ይታፍል አለኝ እዩኤል ከዚህ በፊትም ደም እየታፍ መሆኑን ነገር ግን ከእኔ ደብቆ እንደነበረ አሁን ገና ገባኝ የኔ ፍቅር ሃኪም ቤት እንሂድ አልኩት አይይይ አሁን እኮ ደህና ነኝ ደግሞ ምንም ለውጥ እንደሆነ የለም መሄዱስ ምን ያደርጋል ብለሽ ነው ባይሆን አንቺ ሁለም ደስተኛ ሁኝልኝ ደስ ስልሽ ደስ ይለኛል ብሎ እምባ ማፍሰስ ጀመረ ፍቅር እያለቀስክ እኮ ነው አልኩት የደስታ እምባ እኮ ነው አለኝ ስለ የትኛው ደስታ ነው የምታወራው አልኩት ፍቅር አንቺን አፍቅሮ ይሄን ሁሉ ወረቶችን በፍቅር አሰልፈን መሞት በራሱ ለኔ ትልቅ ደስታ ነው ብዙዎች እኮ ናቸው ይሄን እድል ማግኘት ያልቻሉት ብዙ ዘመናትን ኖረው ግን ፍቅር የሚባል ነገር በጭራሽ አያውቁም እኔ እድለኛ ነኝ፣ ፍቅር ግን ምንም ነገር ብመጣ ሀዘንተኛ እንድትሆኝ አልፈልግም ሁለም ደስተኛ ሁኝልኝ እሽ አለኝ ውዴ ስለ ምን ሞት ነው የምታወራው በእናትህ ሁለተኛ ስለ ሞት አታውራ አሁን እኮ ደህና ነህ ከዚህ በኋላ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል አልኩት እኔ ግን አይመስለኝም ልቤን ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ነበረ አሁን ግን መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ያለውት ይመስለኛል፣ ግን ፍቅር ዶክተሩ በጣም መልካም ሰው ነው አለኝ ይሞታል የሚለውን ነገር ነግሮኝ ስለነበረ ባክህ እሱ አስጣልታ ነገር ነው እሱን ተው አልኩት ምነው ፍቅር በዚህ ዘመን እንደሱ ጊዜውን ገንዘቡን ሁሉንም ነገር አይቶ እንኩዋን ለማያውቅ ሰው አሰልፎ የሚሰጥ ሰው ማን ነው? እነዚህን ሁሉ ወረቶች የቆየውት ከፈጣሪ በታች በእሱ እርዳታ አይደል? እሱ ባይኖር ሌላ ቀርቶ ምግብ ራሱ አልነበርም እኮ አለኝ ለናገሩ እዩኤል ትክክል ነው ግን እኛ ሰዎች መቼም እውነት ተናግሮ ከሚጎዳ ሰው ይልቅ በውሸት የሚያጽናና ሰውን አብዝታን እንወዳለን የኔም ጥላቻ ከዚው የመጣ ነው። እሱማ ትክክል ነህ ግን ውሸታም ነው አልኩት ማን ዶክተር? ፍቅር እሱ በፍጹም ውሸታም አይደለም ባይሆን ይሄን ደብዳቤ ወስደሽ ቤትሽ አስቀምጪ አለኝ የምን ደብዳቤ ነው? ማነው የላከው? አልኩት ሁሉንም ነገር ደብዳቤ ላይ ታገኛለሽ ነገር ግን ደብዳቤውን አሁን መክፈት የለብሽም አለኝ እኔስ ድሮ በአንተ ፊት ምን ብዬ እከፍታለሁ ብለህ ነው አልኩት እንደዛ ማለቴ አይደለም.... ፍቅር ቤት ሄደሽም መክፈት የለብሽም አለኝ እኮ ለምን አልኩት መክፈት ያለብሽ ቀን ይመጣል አሁኑ ቀኑ አልደረሳም አለኝ እኮ ቀኑ መቼ ነው አልኩት ቀኑ
ይቀጥላል...
┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉
1.3K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:52:32 Join @ethio_leboled #Share @ethio_leboled
invite your friends

@ethio_leboled
║▌║█║▌║▌█║▌║█║▌▌█║▌
1.4K viewsedited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:50:41 ርዕስ :- ደህንነቱ
ደራሲ :- ይስማእከ ወርቁ
ዘውግ:- ልብ ወለድ
ዓ.ም:- 2011
ሙሉ ነው ይሄ! ደብዛዛ ነው :ሙሉ አይደለም ላላችሁኝ ይሄንን አውርዳችሁ አንብቡት!
Join @ethio_leboled #Share @ethio_leboled
invite your friends

@ethio_leboled
║▌║█║▌║▌█║▌║█║▌▌█║▌
1.5K viewsedited  04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:45:24 Join @ethio_leboled #Share @ethio_leboled
invite your friends

@ethio_leboled
║▌║█║▌║▌█║▌║█║▌▌█║▌
1.4K viewsedited  04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:41:37 #Share
@Ethio_Leboled
1.4K viewsedited  04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:41:24 #Share
@Ethio_Leboled
1.3K viewsedited  04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:41:09 #Share
@Ethio_Leboled
1.3K viewsedited  04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ