. ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ▣ አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣ #ክፍል_2 ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ ... የዚህችን ሴት ምንነት ለመግለፅ ምን ይሆን የከበደው..? የሚለውን ጥያቄ ሲጮኽ የሰሙት ሰዎች በውስጣቸው ያለ ማቋረጥ እያሰቡት ነው ። አለሙ ማን ናት ህይወቱስ ማን ናት? ድቅደቁ ምሽት ተገፎ ወደ መነጋጋቱ ወስዶታል ። ብርሀን እየመጣ ነው ። ጨለማው ለውጦ ፀሀይ ቦታዉን ተረክባለች። ኮማ ውስጥ ያለችው ሴት ቀኑን እና ለሊቱን ያለ ልዩነት በስቃይ ውስጥ ነች። ማታ ሆስፒታሉን ሲቀውጠው ያደረው ያ ለግላጋ ስውም በእንባ እና በእንቅልፍ አብጦ አይኑን እያሻሽ ተነስቶ ኮማ ውስጥ ወዳለችው ሴት አመራ ። በጉጉት እና በናፍቆት ሲከንፍ ሄዶ አያት ። ምንም የተነቃነቀም ሆነ የተለወጠ ነገር የለም ። ዛሬ ከትላንት ለእሱ የተለየው መሽቶ መንጋቱ ብቻም አይደለም። የሚሳሳላት ሴት በህይወት መኖሯም ተመስገን አስኝቶታል ። ሰላም ስላሳደራት...ሰላም እንዲያውላት እና እንዲያኖራት ወደ ቤተ ክርስቲያን ፈጣሪዉን ሊያመስገን ፤ ሊማፀን ሄደ ። በሃሳብ ሩቅ ስለነጎደ ረዥሙ መንገድ አልታወቀውም ። በስተመጨርሻ እራሱን ቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ ላይ አገኘዉ። ሰማይ እና ምድርን..ሙት እና በህይወት ያሉትን ነገሮችን በሙሉ የማንቀሳቀስ እና የማዘዝ መብት ላለው ፈጣሪ ስላምታውን አቀርበ ። ወደ ግቢው ዘልቆ ገባና አንድ ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ። ግማሹ ቁሞ ሌላው ተቀምጦ ከፊሉ ደግሞ ተንበርክኮ ምልጃውን ያደርሳል ። በጉልበቱ ተንበርክኮ አለሙ የሆነችውን.. እስትንፋሱ የሆነችውን ሴት እንዳይወስድበት ተማፀነው ። ቀጥሎ ዝም ብሎ ቆየ ። ከራሱ ጋርም እንዲ ሲል ሙግት ገጠመ "ቆይ ፈጣሪ ቂም ያዉቃል እንዴ..? ለምንድነው አዳምና ሄዋንን ይቅር ያላላቸው። አይ..አይ ለነገሩ አታድርጉ የተባለውን ነገር ስላደረጉ ነው ። ቆይ ታድያ ፈጣሪ ሀጢያት እንደሚሰሩ ካወቀ ለምን አላስቆማቸውም..? ለነገሩ ማሰቢያ አእምሮ ሰጥቷቸዋል.. ማስብ የእነሱ ድርሻ ነው ። ልንሞት ነገርስ ለምን ተፈጠርን..? ምን ሆኜ ነው ...ፈጣሪ የፈጠርንኮ ለመግደል ብሎ አይደለም ። እሱማ ያረገው ነገር ቢኖር ነፃነትን ከእውቀት ጋር መስጠት ነው ። ፈጣሪን ከምወቅስ አታድርጉ ተብሎ ላረግነው እኛ ለምን ክስ አላቀርብም..? ምን እየሆንኩኝ ነዉ!! ፈጣሪ ፍቅር ነው ። ጥላቻን እንድናውቅ ያረገን የፍቅርን ሀያልነት ሊያሳየን ስለፈለገ ነው ። አዳም ብቻውን ቆዝሞ ከራሱ ጋር ያወጋል ። ስለማንም ግድ አልሰጠውም ። የእሱ ሄዋን አሁን አጠገቡ የለችም ። ወደ ራሱ ተመለሰ በሀዘኑ ምክንያት የተንጨበረረ ፀጉሩን እና ፂሙን በተራ እየዳበሰ ተንጠራርቶ ተነሳ ። ወደ ሀኪም ቤት ተመለሰ። በጣም ርቦታል መብላት ፍልጓል። ያለ እሷ መብላቱን ሊለምደው አልቻለም ። ከትላንት ጀምሮ ምግብ በአፉ አልዞረም ። ለመብላት በማስብ ወደ ሀኪም ቤቱ ካፌ ሄደና ተቀመጠ ። ቀጫጫ ረዘም ያለ አስተናጋጅ ቀልጠፍ ብሎ " ምን ይምጣ ወንድሜ " አለው "እእ ቀለል ያለ ቁርስ ባንተ ምርጫ ይሁንልኝ" አለው ። አስተናጋጁም ሲከንፍ ሄዶ ምርጥ ዱለት ከውሀ ጋር አመጣለትና መልካም ምግብ ብሎት ሄደ ። እጁን ታጥቦ ዱለቱን በፍጥነት በልቶ ጨርሰ ። የራሱን ሆድም በጣም ታዘበው ። "ለካስ ስጋና ነብስ የተለያዩ ናቸው ።" አለ በውስጡ "እሷ ተኝታ እኔ ግን በላሁ" አለ ምግብ መቅመሱ በትንሹ ያረጋጋው ይመስላል ። ከበላ በኋላ አረፍ ማለት ቢፈልግም አልቻለም ። ልቡ እና ሀሳቡ ሄዋኑ ጋር ነው ። እርሷ ጋር ሲደርስ ብቻዋን አልነበርችም ። አጭሯ ነርስም ነበረች ። በውስጡ "ይህቺ ነርስ ቀንና ለሊት ነው እንዴ የምትሰራው" ሲል እያሰበ ተጠጋት ። በስስ ፈገግታ ስላም ተባባሉ። ነርሷ አተኩራ እያየችው " ትላንት ግን" አለችና ፀጥ አለች "ትላንት ምን..?" አላት "አይይይ በጣም ጮኸክ በስላም ነው..?" አለችው የትላንቱ ትዕይንት በአይነ ህሊናዋ እየታያት ። "ልብሽን አሞሽ ወይም ልቡን የታመመ ሰው አጋጥሞሽ ያዉቃል ..?" አላት " ዉይ አዎ !! ይገርምሃል ጎረቤቴ ልቡን አሞት ነበር ። ማለቴ የልብ ድካም አለበትና በቃ ሊሞት ለጥቂት ነው የተረፈው " አለችው ። አዳም ትንሽ ሊስቅም ቃጣው ። ሌላ ጊዜ ቢሆን በደንብ ይስቅ ነበር ። አሁን ግን የሚስቅበት አንደበት የለውም ። ፈገግ ብሎ እያያት " እሱኛውን የልብ ህመም አደለም ያልኩሽ ። በፍቅር ምክንያት ሰለሚታመም ልብ ነው የጠየቅኩሽ ። ልክ እንደኔ በፍቅር መስቃየት የሚወዱትን.. የሚያፈቅሩትን ስው በቅርብ በአይን እያዩት በእጅ የማይነኩትን ነዉ የምልሽ..የሚወዱትን ሰው ትንፋሽ ካጠገቡ ሳትርቂም እስትንፋሱን አለመስማት... ድምፁን መራብ በጣም ያማል ። ቅስምን ይስብራል ። ይህንን ህመም . .. ይህንን ስቃይ ነው ያልኩሽ" አላት አሳዘናት... ያላትን ነገር ተረደተዋለች። እጇን ወደእሱ ሽቅብ እየዘረጋች "እንተዋወቅ ዲና እባላለው... ቅር ካላለህ የሁለታችሁንም ስም ብትነግርኝ " አለችው ። ዳግመኛ ስለ ስሟ ስጠይቀው እንደ ማታው እንዳይጮኽ በመፍራት... የጨበጣትን እጁን ከእጇ አላቀቀና " እኔ አዳም እባላለሁ። እሷ ደግሞ" አለ አልጋዉ ላይ ዟ ብላ ወደተኛችው ልጅ እየጠቆመ "ሄዋን ትባላለች" ብሎ ሌላ ወሬ ሊያወራ ሲል ተናዳ "አትቀልድ ባክህ ትክክለኛ ስማችሁን ንገረኝ" አለችው ... "ማለት?" አላት "ማለትማ ስማችሁን በስርአት ንገረኝ" " ነገርኩሽኮ" እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ አንድ ጠና ያለ ዶክተር ሄዋን ክፍል ገብቶ ካያት በኋላ ወደ አዳም ዞረና "አቶ አዳም ለወይዘሪት ሄዋን መድሃኒት ያስፍልጋታል ። ነገ ማታ ትነቃለች የሚል ግምት አለኝ "ብሎት ሄደ ... ነርስ ዲናም እንዳልቀለደ ገባት ። አዳም እና ሄዋን መገጣጠም ነው ወይስ ለእራሳቸው አውጥተውት ነው..? ብላ ተገረመች ። አዳም በደስታ ጮቤ ረገጠ ። መቼም የሚያየው ያልመስለውን አይን ሊያይ ቀጠሮ ተስጥቶታል ። ሮጥ ሮጥ እያለ መራመድ ጀመረ... ዲና "የት ልትሄድ ነው አለችው" "መድሃኒቱን ልገዛ ነዋ " ፊቱ ላይ ደስታ ይነበባል ። "አብርን እንሂድ " አለችው ፈገግ ብላ ... "ስራሽስ? " "ፈረቃዬን ጨርሻለው። ከመውጣቴ በፊት ላያችሁ ነበር የመጣሁት ። "እሺ እንሂድ" አላት አዳም እየተጣደፈ እስታፍ ልብሷን ቀይራ መጥታ መንገድ ጀመሩ ። መንገድ ላይ "አለሜ ልትነቃ ነው። አዎ ልትነቃ ነው ። እናትዬ ልትነቃ ነው " አለ ጮኽ ብሎ... ዲና ግራ ገባት ። እንደመሳቅም እየቃጣት " አረ ባክህ ዝም በል..ቆይ ይህቺ ሴት ምን አይነት እድለኛ ብትሆን ነው እንዲህ ያለ አፍቃሪ የሰጣት። ... አይ ሄዋን " አለች በውስጧ ስለሁለቱ ታሪክ ለመስማት እየጓጓች.... ይቀጥላል... @ethio_leboled 1.3K views16:01