Get Mystery Box with random crypto!

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

▣ አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣


#ክፍል_3



ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ( የሸዋ ልጅ)




... ጩኸቱን ሲጨርስ ረዥም ሳቅ ሳቀ። በረዥሙ ተንፍሶ ወደ ቀልቡ ተመለሰ ። ዲና አሁን ላይ ይህቺ ሴት ማን እንደሆነች ልትጠይቀው ወሰነች ። ጉሮሮዋን
ከጠራረገች በኋላ" እእእእእ እስቲ ስለ ሄዋን ንገረኝ አዳም" አለችው
" ምን ልንገርሽ" አላት
"ማለቴ ያው እንዴት እንደተዋወቃችሁ... ፍቅር እንዴት
እንደጀመራችሁ እና እንዴት እንደዚህ ልታፈቅራት እንደቻልክ" ዲና ይህንን ብላ
ቁልቁል አዳምን አየችው ።
ፊቱ በፈገግታ በርቷል ። ልክ እንደ ነፀብራቅ ፈክቷል ።
ባለፈው ፈገግ ካለው ይልቅ ሲስቅ በጣም
እንደሚያምር አወቀች ።
" ኡፍፍፍፍ እሷን ያወቅኩበትን ቀን ላንዴም
አልዘነጋውም ። ከ5 አመት በፊት የካምፓስ ተማሪ ነበርኩ ። 6 ጓደኞች ነበሩኝ ። ከእኔ
ጋር 7 ማለት ነው ። የሁለተኛ አመት ተማሪ ነበርን ። ከእነሱ በጣም የተለየ ፀባይ ነበረኝ ። ማለቴ እነሱ ሴት ማተራመስ እና መላከፍ በጣም ይወዳሉ ። ወሬያቸው ሁሉ
ሰለ ሴት ነው ። እኔ ደግሞ ሀሳቤ ሁሉ መፅሀፎቼ ላይ ነው ። ፀጥ ያለ ቦታ ይመቸኛል ። ግን ጓደኞቼ አብሬያቸው እንድሆን ሲጠይቁኝ እንቢ ማለት አልችልም ። ሄዋኔን
ያየኋት የሁለተኛ አመት ትምህርት ለመጀመር ተማሪው ከቤቱ ወደግቢ
የሚጎርፍበት ሰአት ላይ ነበር ። ጓደኞቼ እንደለመዱት ለመላከፍ ወደሚመቻቸው
ቦታ ሄደው ተደላድለው ተቀምጠው ነበር ። ያኔ እኔም ነበርኩኝ ። አንድ መካከለኛ
ቁመት ያላት በጣም ቀይ እና ፀጉሯ በጀርባዋ የወርደ ግን በቅጡ ያልተያዘ ፀጉር ያላት...የወንድ የሚመስል አለባበስ ለብሳ በአጠገባችን ልታልፍ
ስትል አንዱ ጓደኛዬ "ኧረ ይቺ ልጅ ፍሬሽ ናት መስለኝ አይቼያት አላዉቅም ። እስቲ
ላስደስታት" አለና ድምፁን ሰልከክ አርጎ "እሙዬ ሻንጣውን ላግዝሽ " አላት
እሷም ፈገግ ብላ "አመሰግናለው ወንድሜ አጋዥ አያስፍልግም" አለችው ቀጠል አድርጎ "ወይም አንቺን ተሽክሜሽ ልግባ " አላት...
ጥቂት ሄድ ካለች በኋላ ፊቷን
ፍክት አድርጋ ፈገግ እያለች "አንዴ እስኪ ና " አለችው...
ደስ እያለዉ ወደ እሷ
ቀረበ ። ሌላኛው ጓደኛችን "ኧረ ንቀት እራስሽ አትመጪም እንዴ..ምንሼ ነው" አላት...
እሷም ዝም ብላ ያኛውን ጎደኛችንን በአይኖቾ አታላ አጠገቧ አመጣችው ። ከዛም
በጥፊ ጭንቅላቱን አዞረችበት ። ሁሉም ደነገጡ ። እኔ እራሴም ደነገጥኩ ። 'ትስማኛለህ '
አለች እየጮኸች...
" አንተ ከንቱ.. የማትርባ አፍክህ በከፈትክ ቁጥር ባዶነትህን
ነው የሚያሳየው ። ዳግም እንዲህ ብታደርግ አንላቀቅም ።" ብላው ሄደች... ስታወራ...ጩከቷ አለም ላይ ያለ ሰዉ ድምፅ አዋጥቶ ለእሷ የተሰጣት ይመስላል ።
በጣም በጩከት ነው የምታወራው ። ልጅቷ ከሄደች በኋላ ጓደኛችን በድንጋጤ
ደርቆ ጉንጩን እየሸፈነ መጣ ።
ምን ብለሃት ነው ስንለው...' ለምንድነው
ወንድሜ የምትይኝ ..ይልቅ ማታ አልጋ ይዘን ለምን አናወራም ' ነበር ያልኳት አለ ።
ሁላችንም በጣም ሳቅንበት ። ይቺ ሴት ሄዋን ነበረች ። ሁሉም ሴት
ሲለከፉ እያፈሩ እና እየተሽኮርመሙ ሲሄዱ እራስዋን ያላስበገርችው ሄዋን ናት ።
ሄዋን ልጁን መታው ከመሄዷ በፊት አንድ ቃል ተናግራለች ። "እኔ ሄዋን ነኝ እሺ
የምሽኮርመምልህ ወይም የምፈራህ እንዳይመስልህ ። በጭራሽ እንዳትሳሳት.. ቀና ብለህ እንዳታየኝ ። ተግባባን !! ብላ አስጠንቅቃዉ ነበር ።
በጣም ገርመችኝ... ወኔዋ በእራስ
መተማመኗ እና ሁሉ ነገሯ አስገረመኝ ። ለፍቅር ያጨኋት ማለቴ
በአይነ ህሊናዬ የሳልኳት አይነት ሰው ሳትሆን ግን ልቤን እና ሁሉ ነገሬን በአንድ
ጊዜ ተቆጣጠረችው ።" አለ አዳም ። ፈገግ እያለ ነበር የሚያወራው ።
" በቃ የቀረውን ደግሞ
ሌላ ጊዜ" አላት የእጅ ሰአቱን እየተመለከተ ።
" ኧር አለስማህም... ልቤን
እንደዚህ አንጠልጥለኸዉ ወልፈት የለም ። በቃ እንደውም ዛሬ ሆስፒታል ነው የማድርው።" አለችው ።
አዳም በአግራሞት እያያት "ዛሬ እረፍት አደለሽ እንዴ " አላት
"አዎ ነኝ ግን የእረፍት ጊዜዬን ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ በመስማት ላሳልፍው
ወስኛለሁ" አለችው ።
የመድሀኒት መደብሩ ጋር ደርሱና መድሀኒቱን ገዙ ። መድሀኒቱ በጣም ውድ ነው ። ቢሆንም ግን የገንዘብ ችግር የለበትም ። ገዛና ወደ ሀኪም ቤቱ ተመለሱ ።
ከመድሀኒት ቤቱ እስከ ሆስፒታሉ ምንም ነገር አላወሩም ነበር ። ሆስፒታሉ በር
ላይ ሲደርሱ
ዲና "በቃ አሁን ቤቴ ሄጄ እርፍት ላድርግ..አመሻሹ ላይ መጥቼ
የጀመርክልኝን ትጨርስዋለህ። እንገናኛለን" ብላዉ ተሰናበተችዉ ። ባይኑ ሽኛትና ሄዋን ወደተኛችበት ክፍል አመራ ። ሄዋን አሁንም ኮማ ውስጥ ናት ። ግን ደግሞ
ልትነቃ ትንሽ ለሊት ማታ እና ቀን ወይም ሰአት ነው የቀረው ።
"ሄዋኔ " አለ በለሆሳስ
ደምፅ ...
"አንቺን አለማፍቀር ይቻላል...? እእ አንቺን አለመውደድስ ...? አይ በጭራሽ
አይቻልም ። አዎ አይቻልም.. የኔ አስተዋይ .. የእኔ ጩኸታም.. የኔ አኩራፊ ንቂ ...ንቂልኝ ።
ሄዋኔ ሄዋኔ አንቺ ነሽ ሰላሜ
እናቴ ልበልሽ በቃ ነሽ አለሜ
የፍቅርሽ ወላፈን ከአድማስ ባሻገር
ልቤን አሳመመሙ ለኔ ሳይናገር ።
ኮማ ውስጥ ያለሽው ፍቅሬ ተይ ንቂልኝ
ጨርቄን ጥዬ ሳላብድ ባክሽ ድርሽልኝ ።
እያለ አጠር ያለችውን የግሉን ግጥም በውስጡ አዥጎረጎርው ።
በተመስጦ
እሷን በማየት ግጥሙን ቀጠለዉ...

ትነቂያለሽ ብዬ በተስፋ ልጠብቅ
አትነቂም ብሎ ውስጤ እንዳይጨነቅ።
እያለ በሀዘን ፊት ያያት ጀመር ።
"ትነቂያለሽ ውዴ" አለ በለሆሳስ....
እዚህ ሀስብ ውስጥ ሆኖ ጠና ያለው ዶክተር ትካሻውን ለመጣራት እና
ለማፅናናት ያክል መታ አደረገው።
"ከአንድ ሰአት በኋላ ቢሮ ና" ብለውት ሄዱ...
"ምን ሊሉኝ ነው...? አትተርፍም ትሞታለች ሊሉኝ ነው...? ለምን እንዲህ አዘኑ..? እእእ "

ይቀጥላል...
@ethio_leboled