Get Mystery Box with random crypto!

​​​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

​​​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

▣ አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣


#ክፍል_1



ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ
.
.
.
ዛሬ አንድ ግሩም ለግላጋ ስው ኮማ ውስጥ ያለችውን ሴት በክፍሉ ማሳያ በኩል በሀዘን እና በጭንቀት በፍቅር አይን አትኩሮ እያያት ነው ። በጣም
ተመስጧል ። በእርግጠኝነት ይህ ስው የሴቲቱን መንቃት እንደሚጠባበቅ በህይወቱ ምንም ተጠባብቆ
የሚያዉቅ አይመስልም ። አንድ አጠር መጠን ያለች ቀልቃላ ነርስ መጣችና ደንደን ያለውን ትከሻውን መታ አድርጋዉ ከሃሳቡ አነቃችው ። ይህ ስው ከሃሳቡ ቢነቃም የነቃ
አይመስልም ። ይህች ጀርባ መቺ ከማጠሯ የተነሳ ያቀረቀረው አንገቱን ቀና አርጎ መመልከት አልተጠበቀበትም ። ባይኑ ስላምታ ስጥቷት.. ልብ
ሰራቂ የሆነውን ፈገግታዉን በትንሹ የግዱን አሳያት።
" እኔ እምልህ" አለችው አጭሯ ነርስ እሱም ቀጥይ ወሬሽን የሚል በሚመስል
መልኩ አያት "ይህቺ ሴት ምንህ እንደሆነች እስቲ ንገርኝ አለችው "
ረዥም ዝምታ በመካከላቸው ሰፍነ ። ትግስት ያጣችው አጭሯ ነርስ "ምነው ዝም አልክ ...? መቼም ምንህ እንደሆነች ጠፍታብህ እንዳልሆነ ተስፋ አረጋለው ። በቃ ልገምት እእእእ
እህትህ ናት" አለችው...
"አይደለችም" አለ እንባው መተናነቅ የጀመረው ይመስላል...
"እና መቼም ልጅህ አትሆንም" አለችና ፈገግ አለች ። እሱ ግን ስምቶት
ወይስ ችላ ብሎት ፈገግም አላለ...
ፊቱን በአተክሮት አየችው እንደተከዘ ነው ። " እሺ እና ፍቅርኛህ ናት..?" አለችው
"አይ እሷ" አላስጨረሰችውም "እእእ መቼም እናትህ አደለችም ..ወልዳ አንተን
አታደርስ" አሁን የሰማት ይመስላል ፈገግ አለ ።
እሷም "እና ቆይ ሚስትህ ነች ማለት ነዉ ። አለችው...
ዝምም አለ በድጋሜ ። ረዥም ዝምታ
በመሀከላቸው ስፈነ ። አጭሯ ነርስ ግራ ገባት ። ከፊቱ የተኛችውን እንስት ማንነት
ለማወቅ ከፊቷ ከቆመው ሚስኪን ሰው ብጠይቅም መልስ አልሰጣትም ።
" እና ምንህም ካልሆነች እዚህ ምን ትስራለህ...? ወይስ" ስትለው "እንዳጨርሽው በቃ "
አላት እየጮኸ
"እሷ ማለት ለእኔ አለሜ ናት ። ምንህ ነች ስትይኝ ምኔ ነች ልበልሽ...? ሁሉ ነገሬ
ናታ !" የተናነቁት እንባዎች በትንሹ ተከታትሉ። ብዙም ሳይቆዩ እየተሽቀዳደሙ ይፈሱ ጀመር ።
አጭሯ ነርስ በጩኸቱ ተደናገጠች ። በቃላቱም ተገርዠረመች " አለሜ ናት ፤ ህይወቴ ናት ፤ ደስታዬ ናት ፤
ፍቅሬ ናት በቃ ሁሉ ነገሬ ናት ። " አለ መልሶ...
አጭሯ ነርስ አሁን ምኗ እንደሆነ የገባት
ይመስላል ። እየደጋገመ አለሜ ነሽ ፤ አለሜ ነሽ ..አለሜ ናት.. አልተዋትም
አፍቅራታለሁ ። ህይወቴ ናት ።" እንደ መፍክር እየጮኸ መናገር ጀመረ ።
ጭኸቱ በረታ ። ክፍሉን አናወጠው በእዚህ መሀል አጭሯ ነርስ ፈዛ
ደንዝዛ ቀረች ። ጩኸቱ ያስደነገጣት መልሱም ያልጠበቀችው ትመስላለች ። ለቀናት በሀዘን ተክዞ የሷን መንቃት የሚጠባበቀውን ሰው የሀኪም ቤቱ ዘበኞች እና ሁኔታውን እያዩ ሲያዝኑ የነበሩት ሰዎች እያዋከቡ አስወጥተው የሀኪም ቤቱ ግቢ ማረፊያ ወንበር ላይ አስቀመጡት ።
ወደራሱ የተመለስ አይመስልም ። አሁንም አለሜ ነች ፤ ሁሉ ነገሬ !!
ምንህ ናት አትበሉኝ። ሁሉ ነገሬ ናት.. ምንህ ናት እያላቹህ አታስጨንቁኝ ። ስንቴ ነው የምትደጋግሙብኝ ።" ቀስ በቀስ ድምፁ ሰለለ...ድካም ተስማውና ባለበት አግዳሚ ወንበር ላይ ጋደም አለ።
"ዘመድ የለኝም ዘመድ የላትም ። ምንህ ነች አትበሉኝ ..ሁሉ ነገሬ ናት። ይላል አሁንም አልፎ አልፎ ።
ድምፁን እየቀነስ እየቀነሰ በስተመጨረሻ ዝምምም አለ ። ዘበኞችም ፎጣ
ፈላልገው አልብስውት እዛው እንቅልፍ ወሰደው ። ሁሉም በውስጡ ይህቺ ሴት
ማናት ይላል.. እውነትም ይህቺ ሴት ማናት?...

ይቀጥላል...


@ethio_leboled