Get Mystery Box with random crypto!

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_7


ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ



... አዳም ድካም እየተስማው ሲመጣ ሌላኛው አግዳሚ ወንበር ላይ
ሄዶ ጋደም አለ ግን ነገ ሄዋን ስለምትነቃ በጉጉት ሊሞት ነው
ሄዋን ከነቃች በኋላ ለሚፈጠርው ነገር እራሱን አእምሮውን አዘጋጀ
ሄዋን ነገ ከኮማ ስትነቃ ልክ እንደማታቀኝ ልታስመስል ነው ወይ
ብሎ እራሱን ከጠየቀ በኋላ መልሶ ለእራሱ አይ አይ ሄዋኔ ወዳ
አደለም የረሳችኝ እንደዚህ መሆኗስ ለእኔ ስትል አደል አለና
እራሱን አፅናና እንዲ ከራሱ ጋር በሀሳብ ሲሞገት ሳያስበው
እንቅልፍ አሽለበው።

የሆነ የሚያስፍራ ኮቴ ሰማ በቀስታ የሚጓዝ ማን እንደሆነ ለማየት
ቀና አለ ምንም አይነት ሰው አልታየውም መልሶ ተኛ አሁን
የሚንሾካሾክ ድምፅ ሰማ ቀና ሲል ከእሱ ትይዩ የተኛችው ዲና
የለችም የት እንደሄደች ግራ በመጋባት እና በፍርሀት ስሜት ወደ
ሄዋን ክፍል እያመራ ሳለ ዲና በ2 ትልልቅ አቅም ባላቸው ስዎች
ተይዛ በጥቁር ፕላስተር እጇ አፏ እና እግሯ ተይዟል በአስተማሚ
ወንበር ላይ ጥብቅ አድርገው አስርዋታል ። አዳምን ስታየው
በተቀመጠችበት ወንበር ላይ መወዛወዝ ጀመርች አዳም
ከታስረችው ዲና ትይዩ ኮማ ውስጥ ያለችውን ሄዋንን አንድ
ጭንብል ያርገ ሰው በህይወት እና በሞት መካከል እስትንፋሷ
የሆነውን ማሽን አዳምን ፍገግ ብሎ በ ሰራውልክ አይነት
አስተያየት እያየው ነቀለው አጭር ጩሀት ሰማ ዞር ሲል ዲናን
ድምፅ በሌለው መሳሪያ አናቷን በታተኑት አዳም
አይይይይይሆሆሆሆንንምምምምምምም ብሎ ጮከ ኧረ ድረሱልኝ
ሰው የለም እንዴ እያለ ቢጮክም ምንም አይነት ሰው ሊደርስለት
አልቻለም አዳምን የሆነ ባትሪ መሰል መብራት ነገር ስውነቱ ላይ
ጭንብል ከለበሱት ውስጥ አበራበት አዳም አቅም አጠርው
መንቀሳቀስም አልቻለም ከቆይታ በኋላ የአንድ ሰው ኮቴ ተሰማው
ይህንን ኮቴ ያውቀዋል ሁለት እግር አንድ ከዘራ ባለ ከዘራው እና
ባለ ብዙ ሀጢያቶች ባለቤት ይህ ሰው ሄዋን ለእዚህ ችግር
እንድትጋለጥ ያረገው ሰው ነው ፈገግ እያለ ወደ አዳም ቀረበው
አዳምም አይሆንምም ብሎ ከህልሙ ነቃ ዲና ደንግጣ በርግጋ
ተነሳች ምንነው ችግር አለ አዳም አለችው እሱም የለም ተኚ
ብሏት በጥድፊያ ሄዋን ጋር ሄዶ በመስታወቱ ያያት ጀመር።
እውነት ቢሆንስ ቆይ ህልሜ ካንቺ ተለይቼ እንዴት እኖራለው ብሎ
ተንስቀሰቀ።

ይህ ሰው ጌዲዬን ይባላል በወንጀል የታወቀ ነገር ግን መፍትሄ
ያልተገኘለት ሰው ለብዙ ህፃናት ደሀዎች እና ፍትህ ፍላጊዎች
እልቂት ተጠያቂ እጁ እስከ ከፍተኛ የወንጀልም ሆነ የቢዝነስ ነክ
ጉዳዎች ላይ የሚረዝም ከፈለገ ምንም ማድርግ የማያቅተው
ህይወት ያለው ሰው የሚታዘዘው ነው። ታዲያ ለእሱ አለታዘዝ ያለ
ስው በህይወቱ ፈርዶ ነው ባአስቃቂ እና በሚዘገንን መልኩ
ያስቃየዋል በቁሙ በህይወት እንዳለ ያለ በለዚያ ፈፅሞ አይርካም
አንድን ሰው ገደለ ማለት በጣም ጥሩ ስራ እንደስራ ነው
የሚስማው ሰውን በቁሙ ማስቃየት በአለም ላይ ለእሱ ትልቅ
ፌሽታ ነው ሁሉም ሰው የእዚህ ስው ስም ሲነሳ ይንቀጠቀጣል።
አዳም በጥብቅና ሙያው ማንም የማይስተካከለው እልልልል
የተባለለት ጠበቃ ነው ስራ የጀመርው ከአመት በፊት ቢሆንም
ባጭር ጊዜ ባጭር የፍርድ ቀጠሮ ብዙ አልበገር ባይ እና ወንጀል
ስርተው የሚሸሽጉ ስዎችን አጋፍጦ ለፍርድ ልኳል ወደ ሚገባቸው
አስናብቶቸዋል ።ጠበቃ አዳም ማለት ለወንጀለኖች ስይጣን ፍትህ
ለተነፈጉ ደሞ መላክ ነው።

ጌዲዮን የአዳምን የጥብቅና ችሎታ እና ዝናውን ሰምቶ በቢዝነስ
ይሁን በማንኛቸውም አይነት ጉዳዮችን አብሮት እንዲሆን በረብጣ
ገንዘብ ድርድር ያቀርብለታል ጊዲዮን በዙሪያው ሌሎች የእራሱ
ጠበቆች ቢኖሩትም የአዳምን ጥብቅና ግን አብዝቶ ፈልጎታል
አዳም ግን የጊዲዮን ድርድር ሆነ ገንዘብ አላማለለውም ጠበቃ
አዳም ለህሊናው የተገዛ ለፍትህ ጥብቅና የቆመ ለእውነት
የሚኖር ሰው ነው ።

ልክ እንደ አዳም በጊዲዮን አልመራ ያለ እና ጊዲዮን በቁሙ
አስቃይቶ የገደለው እስማኤል የተባለ እሳት የላስ ጠበቃ ነበር
እስማኤል የጊድዮንን ትእዛዝ አለመቀበል ብቻ ሳይሆን
ሊያስፈርድበት ሂደት ጀምሮ ነበር በጊዲዮን ሴራነት ሰውን ያለ
ምክንያት በሀሰት በመፍርድ ተብሎ ተከሶ ለእርዥም አመት ታስሮ
የታሰርበት እስር ቤት ውስጥ በጊዲዮን ትዛዝ መሰርት የታሳሪያን
ሻውር ቤት ውስጥ ሞቶ ነበር የተገኘው ይህንን ጠበቃ መጀመሪያ
የሚወዳቸውን ስዎች በመግደል ነበር አይምሮውን የገደለው
ጌዲዮን ይህ ነው ቁመቱ እጅግ የረዘመ የአይኑ ብሌንን ትኩር
ብሎ ለተመለከተው ልክ እንደ በርበሬ የቀላ መልኩም ወደ ጥቁር
ያደላ ሰው ነው።

ጋሞ ጎፋ እንደሆነና ይህንን ፀባዩን ከአባቱ እስከ ሰውነት አቆሙ
እንደወርሰው ይወራል ብዙ ሴቶችን አስርግዞ አረገዝኩ ብለው
ሲነግሩት የፀነሱትን ፇታ ካወቀ በኋላ ሴት ከሆነች ከእነ እናትየው
ይገላታል የተረገዘው ወንድ ከሆነ ግን እስኪወለድ ጠብቆ እሱን
ካልመስለ ይገለዋል ከመሰለ ግን አሳድጎ ገረዱ ያርገዋል
ይህንን ታሪኩን መንጉደኛው ሎሌ በሚል ርእስ ያ እሳት የላስ
ጠበቃው እስማኤል ፅፎታል እንዲፅፍ የረዳው ደሞ የጌዲዮን
አሽከር ነበር፡፡

አዳም ጠረፔዛው ላይ ፒያሳ አራዳ ጋር 9ስአት ጠብቀኝ የሚል
አጠር ያለ ፅሁፍ አገኘ አዳም የሰውየውን ማንነት ሳያውቅ
የተባለበት ቦታደረሰ ምናልባት ፍትህ የተነፈገ ሰው ስለሱ ሰምቶ
ሊያገኘው እንደፈለገ አልተጠራጠረም
ፒያሳ ጋር እንደደረሰ የሆነ ኩትት ያለ ልብስ የለበሰ ሰው ላዳ ይዞ
ና ግባ እኔ ነኝ የጠራውክ ብሎ ካስገባው በኋላ ጭር ያለ ቦታ
ወሰደው ሲደርሱ የተቀመጥከበትን ወንበር ግለጠው እና እየው
ብቻህን ሆነክ ክፈተው ተጠንቀቅ ማንም እንዳያይክ እዚህ ውስጥ
ስለከተትኩህ ይቅር በለኝ ግን እንደምታስተካክለው አውቃለው
አለውና ቤቱን ሳይነግርው ወደ ቤቱ አደርሰው አዳም ቤቴን እና
መስሪያ ቤቴን እንዴት አወቀ ብሎ ለእራሱ ጠይቆ ለስውየው
ሳይጠይቅ ወረደ ቤቱ በጥድፊያ እንደገባ ቦርሳውን ከፈተው ቦርሳ
ውስጥ በብዙ የተለያዩ ልሙጥ እና ባለ መስመር ሉክ ለሁለት
ታጥፈው በእስቴፕራል ሳይሆን በአርንጓዴ ክር የተሰፋ ደብተር አለ
ሳያነበው እየገላለለጠ ማየት ጀመር የብዙ ስው ፎቶዎች እና
ከፎቶዎች ስር ማብራሪያ ተፅፏል ደብተሩን ከደነው እና ቦርሳ
ውስጥ አንድ ተለቅ ያለ ስአት አገኘ በድጋሜ እጁን ሰደደው
የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወረቀቱ እንዲህ ይላል...

ይቀጥላል...

@ethio_leboled