Get Mystery Box with random crypto!

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_6


ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ(የሽዋ ልጅ)



... ይኸውልሽ ከሳመችኝ በኋላ ምንም ያልኳት ነገር የለም ፈዝዤ ነበር
የሳመችውን ጉንጬን ይዤ የቀረውት እሷ ፊት ላይ ግን ስስመኝ
በመፍዘዜ ምክንያት ሳቅ ይታይባታል ደግማ ጠጋ ብላ "ምነው
ችግር አለ?" አለችኝ አይ ስላት እና "ፈዘካል እኮ
እሺ በቃ ቻው እንገናኛለን በቀጣይ ለእኔም ግጥም ገጥመክ ይዘክ
ና እሺ" ስትለኝ "እሺ መቼ አልኳት".... "ነገ ማታ 12 ስአት ላይ እዚህ
አለችኝና አትፍዘዝ ስስምክ ስትፈዝ እኮ ሳቄም መጥቶ ድንጋጤም
ያዘኝ" ብላ በድጋሚ ግንባሬን ግጥም አድርጋ ስማኝ ሄደች ከሄደች
በሆላ ድንጋጤዬ አለቀቀኝም ዲና በወሬው መሀል ገባችና እንዴት
ግን" አለች ምን እንዴት አለው ያኔ ጓደኛዬ የለከፋት ለት ገና ሳያት
እኮ ነው ልቤን የስርቀችው ኡፍፍፍፍፍፍ በጣም ደስስስስ እሚል
ስሜት ነበር የተሰማኝ የምር ከሳመችኝ በኋላ ያለውን ጊዜ ዝም
ብዬ ስስቅ አሳለፍኩት ነገ በድጋሜ ተገናኝተን ግንባሬን እና
ጉንጭኤን በደንብ እንድትስመኝ ምርጥ ግጥም ልገጥምላት ወስኩኝ
ዲና አፉ ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም እሱም በጣም
በተመስጦ ነበር ሲነግራት የነበርው ጉሮሮውን ጠራርጎ ሊያወራ
ሲል "ንገረኛ" አለችው እሱም ልነግሽ እኮ ነው ከዛ ማታ ለእሷ
ግጥም ስፅፍ አመሸው ዲናም ፈጠን ብላ ምን የሚል እስቲ
በልልኝ ስትል ኧረ ተረጋጊ አላትና ወደወሬው ተመለሰ ማታ
ግጥም ገጥሜላት ግጥሙን12 ሰአት ደርሶ እስከማነብላት
ቸኮልኩኝ በጣምም ጓጓውኝ
ሰአተለ እንደምንም ደረሰልኝ እና 11:40 ላይ የግራሩ ዛፍ
ስር ቁጭ ብዬ
ጠበኳት 11:50 ሆነ ሰአቱ አልሄድ አለ በመከራ 12 ስአት ሞላልኝ
አልመጣችም ባትመጭም ቅጠሪኝ አለ ገጣሚው ባትመጣም ስለ
ቀጠርችኝ ደስስ
ብሎኝ ነበር ከባትመጭም ቅጠሪኝ ግጥም ውስጥ
የነፍስ ጥርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
በቆመ አውሎ ንፍስ ተመቶ እንደመውደቅ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የሚያሳቅቅ ነበር እንደሌለ የገጠመው ግጥም ውል አለብኝ
ትዝዝም አለኝ 12:15ሲል ሄዋኔ ጥቁር የቱታ ሱሪ ሌዘር ጃኬት
አድርጋ እስኒከር ጫማ ተጫምታ ስትመጣ አየዋት ልቤ እሷ
በቀረበችኝ ቁጥር እርምጃዋን ባፈጠነችው ቁጥር የእኔም የልብ
ምት ይፈጥን ጀመር በስተመጨርሻ እኔ ካለሁበት ደረሰች እና
ጉንጬን ስማኝ ቀልጠፍ ብል ተቀመጠች እንደተቀመጠች እጇን
ወደፊቴ ዘርጋችው አፍጠጠች አፈጠጥኩባት እ ምን ታፈጥብኛለክ
ልትለኝ ነው እንዴ በል
ግጥሜን ስጠኝ እንደውም አንተ እራስክ አንብብልኝ አለችኝ ከዛ
እኔም ድምፄን ለሰለስ አርጌ ግጥሙን ማንበብ ጀመርኩ ግጥሙ
እንዲህ ይላል ዲና በጣምም ተመስጣ እሺ በልልኝ አለችው
ከግራሩ ዛፍ ስር
ከግራሩ ዛፍ ስር ልክ እንደለመድኩት
እያነበብኩ ሳለ ግጥም የገጠምኩት
በጩከት ውስጥ እና በመመስጥ ውስጥ
አንድ ድምፅ ተስማኝ የሚመስጥ
ድንገት ከየት መጣ ብዬ ደነገጥኩኝ
አንድ ልጅ ነበርች ግጥሜን ስቀኝ
ከተመጥኩበት ከግራሩ ዛፍስር
ከጀመርዬ ሆና ቃላቶችን ሳስር
ልጅት ብቃቴ እጅክ ተደምማ
ጉንጭና ግንባሬን በአድናቆት ስማ
ለኔም ግጠምኝ ብላ ብጠይቀኝ
12 ሰአት ላይ ልጅት ቀጠርችኝ
ትእዛዝንን አክብሬ ይህው ግጥም ገጠምኩኝ
የሚል ነበር እና ልክ ግጥሙን አንብቤ ሰጨርስ አመሰግናለው የኔ
ውድ ብላ ሁለቱን ጉንጮቼን እና ግንባሬን ሳመችኝ ዲናም ወሬውን
እኔ እምለው ሄዋን ግን እንደተርዳዋት በጣም ሰውን መሳም
ትወዳለች አለች አዳምም ቀጠል አድርጓ ሄዋኔ መሳም ትወዳለች
አዎ መሳም ትወዳለች አለ እና ዝም አለ ዲና እሺ ቀጥላ አለችው
አዳምም ወሬውን ቀጠለ ከዛ በነጋታው ጠዋት ክላስ ልገባ ሰል
ሄዋንን ከብዙ ወንዶች ጋር ቆማ ስትሳሳቅ አየዋት ቅናት ቢጤ
ጫር አረገኝ ቆሜ የሚሆነውን ማየት
ጀመርኩ ትንሽ ካወሩ በኋላ ሄዋኔ ሁሉንም እየዞረች ግንባራቸውን
ሰማቸው ሄደች እራቅ ካለች በኋላም እጆን እያውለበለበች
ተሰናብታቸው ወጣች ልከተላት ስለፈለኩኝ
መከተል ጀመርኩኝ። አዳም ዲናን እንደደከማት እያስተዋለ ውይ
በጣም ደከመሽ አይደል እንቅልፍሽ መጥቷል ታስታውቄያለሽ በቃ
ተኚ ነገ እነግርሻለው አላት አይ ንገርኝ አለችና ድርቅ አለች ግን
ደሞ እሱም ድርቅ ብሎ እንድትተኛ ነገራት እሺ ብላ ካመጣችው
አነስተኛ ኩኪስ ውሀ እና ጋቢ ሰጠችው እሱም ወደ ሄዋን ሄዶ
ሄዋንን በተመስጦ እና በፍቅር አይን ማየት ጀመር...


ይቀጥላል...
@ethio_leboled