Get Mystery Box with random crypto!

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_8


ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ



... የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወርቀቱ እንዲህ ይላል
ሰላም ላንተ ይሁን ጠበቃ አዳም የጠበቃ እስማኤል ወዳጅ ነኝ
ወዳጅ ብቻ አይደለሁም መከታዬ ነው ወንድሜም ጓደኛዬም ሁሉም
ነገሬ ነው ለፍትህ ዘብ የቆመክ ለእውነት የምታድር ሰው
መሆንህን አውቃለው እስማኤል ፍትህ ለተራበ የሚያጠግብ
ለጎደለበት የሚሞላ ነው እስከኖረበት ጊዜ ለእውነት ኖሯል
በመጨረሻም ግን ለአንድ አውሬ ሰው ተበገረ ይህ አውሬ የወዳጄ
እስማኤልን ህይወት ቀጥፎብኛል አንተም እንደሱ ነህ ባንተ በኩል
ፍትህ ያገኙት ስላንተ አውርተው አይጠግቡም እጅግ የጠበቀን
ወዳጄን ህልም እንደምታስጨርስው እርግጠኛ ነኝ ትወጣዋለክ
እንደምትወጣው አምናለው አንብቦ እንደጨርሰ ያን በተለያዩ ልኮች የተፃፈውን እና አርንጎዴ ክር የተያዘውን ደብተር ከፍተው ውስጡ በሉኮቹ ላይ የሰፈሩትን
ተመለከተ ፅሁፎቹ እጅግ የተዋቡ ናቸው በሰማያዊ እና በጥቁር
እስኪብርቶ የተፃፈ ነው የታሪኩ ርእስ መንገደኛው ሎሌ ይሰኛል መንገደኛው ሎሌ መሄድ የለመደው አንድ ቀን ተነስቶ መጓዝ የጀመርው በሄደበት ሁሉ ብዙ ይታዘባል
ተመልካች ታዛቢ ሁሉንም ይሆናል ዛሬ ከቆመበት መንገዱን ጀምሮል
ብሎ አጠር ባለ መልኩ መንገደኛው ሎሌን ገልፇታል መንገደኛ
ስሙን ደሞ በሎሌ ቀይሮ የእዛን አውሬ ስራ አስፍሮታል።
አዳም መፅሀፍን ማንበብ ቀጠለ መፅሀፉም እንዲህ ይላል።
ይገርማችዋል ዛሬ መንገዱኛው ሎሌ እንደለመደው ጉዞውን
ቀጥሏል እየሄደ በመንገዱ ያጋጠሙት ደሀ እናት እና ልጅ ን አየ
እስከሚችለው ሊከተላቸው ወስኖ ሳይሆን እግር መንገዱን
እያያቸው መጓዝ ጀመር እናትና ልጅ በፀጥታ ከተጓዙ በኋላ
ልጅየው እናቷን ሽቅብ አንጋጣ እያየች እናቴ አለቻች እናት
የስማቻት አትመስልም የእኔ እናት እናትዬ እማ እያለች
ስትጎቶጉታት ሀሳቧን እና መንገዷን ገታ አድርጋ ወዬ የእኔ ልጅ
አለች በጣም በደከመና ትንፋሽ በተቀላቀለበት መለኩ እማ እስቲ
አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ እሽ እሺ ልጄ ጠይቂኝ ፍቅር እና መውደድ
ልዩነት አላቸው እንዴ እንዴ እናትም ልጄ በጣም እንጂ በጣም
ልዩነት አላቸው ልጅየው እንዴት አለቻት እናት ልጆ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ልጄ አለቻት ልጅም እሺ እማ አለቻት ጥንድ ጥንድ የሆኑ አካላቶችሽን ንገሪኝ ብላ እናት
ከመናገሯ ልጅት ጥንድ ጥንድ የሆኑት ለምሳሌ አይናችን ሁለት
ነው አለች እናት እሺ ሌላስ አለቻት ሌላ ደሞ እጃችን እግራችን
ሌላስ አለች እናት ልጅቱ ሌላ ጆሮአችን ሌላ ግን የለም አለቻት
እናት ፈገግ ብላ ተሳስተሻል የእኔ ውድ ልጅ አለቻት ልጅም እኔ
የምልሽ እማ ይህ አሁን ከጠየቅሽኝ ጥያቄ ጋር ምን አገናኘው
ያገናኘዋል እንጂ ልጄ እይውልሽ እንዳልሽው እጃችን እግራችን
አይናችን እና ጆሮችን ብቻ ሳይሆን ከልባችን በቀር ሁሉም አጋዥ
አለው ልጅየው ግራ ገባትና እንዴት እናቴ አለቻት ለምሳሌ ጣትሽ
ስንት ነው 10 እሺ ጨንጓራችንንስ እኔጃ እማ እሱም ትንሹ እና
ትልቁ አንጀት የሚባሉ አጋዦች አሉት ፀጉሯችንንም ብዙ አሉት
ከንፍራችን ደሞ ከላይና ከታች አለ ጥርሳችንን ተመልከች ብዙ
ናቸው ሊላም ብዙ ጥንድ ነገሮች አሉ ሁለም አጋዥ የላችውም
ልባችን ግን ብቸኛ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ደሞ ሊ ሌላኛው
ልባችን ጋር ሌላ ሰው ጋረ ስለሆነ ነው አለች እናት ልጅቱ እየተገረመች ማን ጋር? ብላ ጠየቀቻት እናትም የወደፊት የህይወትሽ አጋር ጋር እሱ ጋር ነው ለዛም ነው ፍቅር ሲይዘን ሁሉም ነገራችንን የሚቆጣጠርን ፍቅር ሲይዘን ሁሉም አካላታችን
ስራውን አቁሞ ልባችን የሚስራው ፍቅር ሲይዘን ልባችንን የሚስማን ፍቅር ሲይዝሽ በ ፍቅር ካፍቀሩት ጋር መኖር እድለኝነት ነው። አዳም ንባብን በእዚህ ገታ እና
ወርቀቱን ከደነው።
የማያልፍ ቀናት የለም አለፈ ዛሬ ሄዋን ከጥቄት ሰአታት በኋላ
ትነቃለች አዳም ውስጡ ደስ አለው ቀጥሎ የሚፈጠረው ነገር
መልካም እንደሚሆን አሰበ ስትነቃስ አለ በልቡ ስትነቃስ እንዴት
ነው የምቀርባት ሁሉንም ነገር እኮ እረስታለች ድጋሚ እንድትወደኝ
ላረግ ነው ስቀርባት ማነህ ብትለኝስ ልቡ ፈራ ውዴ እረሳሽኝ ወይ እስቲ መልሽለኝ
ምነው ቢሆን ለእኔ ሁሉን ባርገልኝ ብዬ ለመንኩትኝ ሀሳቤን ቢስማኝ
ብዬ በመጠበቅ ይህው ወራት ሞላኝ ለእሱ ብዙ ነገሩ ናት የሄዋን እጃች
በትንሹ መንቀሳቀስ ጀመሩ አላመነም ዶክተሩ ትነቃለች ቢለውም
የሚንቀሳቀስ እጇን ሲያስ አዳም ደስስስ አለው ዶክተሩን
ለመጣራት ከነፈ አጠገቡ ማንም አልነበርም ዲና በጠዋት ቤቷ
ፍቅድ ጠይቃ ሄዳለች ዲና በመንገድ ላይ እና ቤቷም ከገባች
በኋላ ሰለ አዳም ያለ ማቆርጥ ታስባለች ዲና ስልኳ ጠራ አዳም
ነበር ሄሎ አለችው በተርጋጋ ድምፅ...

ይቀጥላል...
@ethio_leboled