Get Mystery Box with random crypto!

ድሬ Tube™

የቴሌግራም ቻናል አርማ diretube0 — ድሬ Tube™
የቴሌግራም ቻናል አርማ diretube0 — ድሬ Tube™
የሰርጥ አድራሻ: @diretube0
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.17K
የሰርጥ መግለጫ

"እኛ ኢትዮጵያውያን ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ ነን"

የተመረጡ የፅሁፍ ዜናዎች በፍጥነት እንዲደርሳችሁ
እናረጋለን። ምንም አይነት ዜና ሳያመልጣችሁ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ እናረጋለን።
ሼር በማረግ ቻናሉን ይደግፉ.
#የመረጃ_ፍጥነት መለያችን ነው!!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር
አሜን !!
ለአስተያየት 👉 @Diretube_service_center_bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-17 18:36:43 በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶቹን ሰኞ የካቲት 14 2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ

ኤጀንሲው ሰኞ በሚጀምረው አገልግሎቱ ከአዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ውጭ ያሉ መደበኛ አገልግሎቶቹን መስጠት እንደሚጀምር ይፋ አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው አገልግሎቶችን በሁሉም ክ/ከተማ እና ወረዳው በተዘጋጀ መርሃ ግብር ነዋሪው እንዲስተናገዱ እንደሚደረግ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ኤጀንሲው አዲስ ሴኪውርድ የሰርተፍኬት ፕሪንተር ለክ/ከተማ እና ወረዳ እያሰረጨ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ከ2013ዓ.ም ጀምሮ ፎርጀሪን ሙሉ ለሙሉ ያስቀርልኛል እንዲሁም የውስጥ ሌብነትንም ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለውን “የሴኪውርድ “ ፕሪንተር ወደ ስራ በማስገባት የማሰራጨት እና የኮንፊግሬሽን ስራ በክ/ከተማ እና በወረዳ ጽ/ቤቶች ሲሰራ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

የከተማውን የወሳኝ ኩነት ማስረጃዎች አለም ዓቀፍ ደረጃ እንዲኖራቸው፣ የሰርተፍኬቶቹን ደህንነት ከፍ የሚያዱርግ፣ እና ሲስተም ባለባቸው እና በሌለባቸው ወረዳዎች አገልግሎት በመስጠት የእጅ ፅሁፍ ንክኪን ለመጨረሻ ግዜ የሚያስቀር ነው ተብሎለታል።

ከዚህ ቀደም ከነበረው መደበኛ ሰርተፍኬት በውስጡ የባለማስረጃውን ስም እንዲሁም ፎቶግራፍ በምስጢራዊ ህትመት ይዞ የሚወጣ ሲሆን በ UV ማሽኖች ተፈትሾ በቀላሉ ኦርጅናል መሆን አለመሆኑን ከባለማስረጃው ስምና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማመሳከር መለየት የሚያስችል ሲሆን በውጭ የሚሰራ የፎርጀሪ ስራን ከማስቀረት ባሻገር በሰርተፍኬቱ ላይ በሚኖር ልዩ Licensed QR ኮድ ፈቃድ የሚሰጣቸው ተቋማት ሰርተፍኬቱ ትክክለኛ ስለመሆኑ ማረጋገጥ የሚችሉበት ስርዓት እንደያዘ ኤጀንሲው አስታውቋል።

በአልግሎት ወቅት ታትመው የሚሰጡት የወሳኝ ኩነት እና የያላገባ የምስክር ወረቀቶች በዋናነት ማስረጃው (ሰርተፍኬቱ) በየትኛው ወረዳ፣ በየትኛው ባለሙያ (User) እና ለማን እንደታተመ መረጃ በመያዝ በማዕከል ቁጥጥር የሚያደርግ አሰራር ያለው ከመሆኑ ባሻገር በምን አይነት ኮምፒውተር የህትመት ትዕዛዝ እንደተሰጠው መለየት የሚያስችል ዘመናዊ አስራርን እንደሚያካትት የአዲስ አበባ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

@Diretube0
3.6K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-07 11:55:43 አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐን ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢ ፕ ድ)

አሸባሪው ሸኔ በጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐንን መግደሉን በኦሮሚያ ክልል የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጊዳሚ ወረዳ አሸባሪው ሸኔ ዘግናኝ ግድያዎችንና የንብረት ውድመት ፈጽሟል።

በወረዳው በተለያዩ ቦታዎች 81 ሰዎችን እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎችን በድምሩ168 ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል። አሸባሪው ሸኔ በወረዳው በቆየበት ጊዜ 30 የመንግሥት ተቋማትን ንብረቶችን ማውደሙንና ዝርፊያ መፈጸሙን አስታውቀዋል።

መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በወሰደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን የጊዳሚ ወረዳ ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ መውጣቱን የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይ እና የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ አስታወቁ።

@Diretube0
4.1K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-28 15:18:10 በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም ብለዋል

ጄነራል ብርሃኑ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያላቸው ትስስር ጥብቅ መሆኑን በመግለፅ ጎረቤት ሀገሯን ሱዳንን የምታጠቃበት ምንም ምክንያት የለም ሲሉ ገልፀዋል።

የድንበር ጭቅጭቅ አለ ይሄ የድንበር ጭቅጭቅ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ነው መፈታት ያለበት የሚል ፅኑ አቋም አላት ኢትዮጵያ አሁን ከጁንታው ጋር ጦርነት ላይ እያለች በጣም ብዙ ትርፍ ኃይል ኖሯት ሱዳንን የምታጠቃበት አይነት ቁመና ላይ አይደለችም ያለችው ሲሉ ተናግረዋል። መሬትን በተመለከተ በሰላምና በድርድር በህግ ይመለሳል ብለዋል።

ብዙ ጊዜ የመሬት ጭቅጭቅ መጨረሻ ፍርድ ቤት ነው የሚሄደው ይሄን ስለምናውቅ እኛ ሱዳንን የመተናኮል ፍላጎት የለንም ነገር ግን ሱዳን የመተናኮል ምልክቶች እያሳየች ነው፤ ጁንታውን በብዛት አስገብታለች እንደገና የታላቁ የህዳሴ ግድብን ለማደናቀፍ እየሰራች ነው እናውቃለን፤ እነሱ የላኳቸው ኃይሎች እየመጡ እየደመሰስናቸው ነው።

የራሳችንን ተላላኪ መደምሰስ እንጂ ለምን ትልካላችሁ ብለን ከሱዳን ጋር ወደአታካራ መግባት አንፈልግም ፤ ከሱዳን ጋር ግጭትም ጦርነትም አንፈልግም፤ ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሻሻል ነው የምንፈልገው በጣም ይሻሻላል ብለንም እናስባለን።

እንዳንድ የሱዳንን ህዝብ እና መንግስት የማይወክሉ ግን በሌላ ሶስተኛ ወገን የተገዙ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ግንኙነት ለማበላሸት የሚሰሩ አሉ ፤ እነማን እንደሆኑም ለይተን እናውቃቸዋለን፤ ታሪክ ይፈርዳል፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝብ ችግሩን በህዳሴ ግድብም ይሁን በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ይፈታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

@diretube0
6.7K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-18 11:43:08 በኦሮሚያ ክልል ተጥሎ የነበረው የምሽት እንቅስቃሴ ገደብ ለጊዜው ተነሳ

3 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11:30 ዜጎች እና ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ አዋጅ ተግባራዊ ተደርጎ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ህጓ፥ የክልሉን እና አገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይጎዳ ከግምት በማስገባት ይህ ውሳኔ ዳግም ተላልፏል ብለዋል።

በቀጣይ ሁኔታዎች እየታዩ አዋጁ እንደገና በመላው ክልሉ እንዲሁም እንደየ አከባቢዎች ሁኔታ ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የእንቅስቃሴ ገደቡ ለጊዜው ቢነሳም÷ አስፈላጊው ፍተሻ በተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ህዝባዊ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል።

@diretube0
6.0K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-21 20:59:56 ዛሬ በመቀሌ ተጨማሪ የአየር ድብደባ መካሄዱን መንግስት አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ ከቀትር በኋላ በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የቀድሞው የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ ግቢ ላይ የአየር ድብደባ ማካሄዱን መንግስት ይፋ አደረገ።

የመንግስት ኮሚንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የአየር ድብደባው ከቀትር በኋላ መካሄዱን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል።

የአየር ድብደባው የተካሄደው ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ዋና መቀመጫ በነበረው እና በአሁኑ ወቅት የህወሓት ኃይል ለወታደራዊ አገልግሎት በሚጠቀምበት ግቢ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

@diretube0
7.5K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-20 22:34:32 ዛሬ የህወሓትን የጦር መሳሪያ ማምረቻዎች በአየር መደብደቡን መንግስት አስታወቀ

ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው

በፌዴራል መንግስት ሥር ያለው የ "ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ገፅ" በትግራይ ክልል ስለሚፈፀሙ የአየር ድብደባዎች መረጃ አጋርቷል። በዚህም መከላከያ ሠራዊት እያካሄደ ያለው የአየር ድብደባን በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።

አክሎም "የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችንና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውንና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው" ሲል ገልጿል።
ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ገፅ

@diretube0
6.0K views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 04:37:42 ዛሬ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ መዘገቡን ሮይተርስ በድረገፁ አስነብቧል

ሮይተርስ ፤ በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የትግራይ ቴሌቪዥን ሪፖርት እንዳደረገው በአየር ጥቃቱ በርካታ ሲቪሎች እንደተጎዱ ገልጿል ብሏል።

የክልሉ ቴሌቪዥን 3 ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ10 በላይ ደግሞ መቁሰላቸው ዘግቧል።

የመጀመሪያው ድብደባ ዛሬ ጠዋት በመቐለ ዳርቻ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሚገኝበት አካባቢ የተፈፀመ ሲሆን ሁለተኛዉ ድብደባ እኩለ-ቀን በመቐለ ማዕከላዊ ክፍል ባለሥልጣናት የሚያዘወትሩት ፕላኔት ሆቴል አካባቢ ነው።

ሮይተርስ የእርዳታ ሰራተኞችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም አንድ ዶክተር ዛሬ በመቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን እንደገለፁለት ዘግቧል።

የጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም በጉዳዩ ላይ ወዲያው አስተያየት እንዳልሰጡት ፤ ከኢትዮጵያ ጦርም ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው ፤ "መንግሥት ለምን የራሱን ከተማ ያጠቃል? መቐለ የኢትዮጵያ ከተማ ነች" ሲሉ ለሬውተርስ ተናግረዋል።

ሮይተርስ ከከተማው ስለወጡት ሪፖርቶች ገለልተኛ ማጣራት ማድረግ እንዳልቻለ ጠቁሟል።

@diretube0
5.1K views01:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-08 16:36:46 አዋሽ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ በአፋር ሶስት ቀበሌዎች የጎርፍ አደጋ ተከሰተ

ጎርፉ ወንዙ ወደ አሳኢታ ሶስት ቀበሌዎች ሰብሮ በመግባቱ ያጋጠመ ነው ተብሏል። አንድ መቶ አባዎራዎች መፈናቀላቸውም ነው የተነገረው
በአፋር ክልል አዉሲ-ረሱ ዞን አይሳኢታ ወረዳ በአዋሽ ወንዝ ሙላት በሦስት ቀበሌዎች የጎርፍ አደጋ መከሰቱን የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሀፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤት የቅድመ-ማስጠንቀቅና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን እንደተናገሩት ከሃምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳዉ ሦስት ቀበሌዎች የአዋሽ ወንዝ ሰብሮ በመውጣት ጎርፍ አስከትሏል።

አደጋው ቀድሞ በተከናወኑ የቅድመ-ጥንቃቄቅ ስራዎች ህብረተሰቡ ከአካባቢዉ እንዲወጣ በመደረጉ የተፈናቀሉ ሰዎች ከመቶ አባዋራዎች የማይበልጡ ሲሆን፤ ጎርፉ 50 ሄክታር መሬት በሚሆን የእርሻ መሬት ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።
ጎርፍ የተከሰተባቸዉ ቀበሌዎች የከርቡዳ፣ ኮሎዱራና ሂነሌ ቀበሌዎች ሲሆኑ÷ ጎርፉ የሰበረበትን አካባቢ ለመዝጋት ከሚመለከተዉ የተፋሰስ ባለሰልጣን ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ ነዉ ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

በክረምቱ ከፍተኛ ዝናብ እየተመዘገበ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በክልሉ የአዋሽ ወንዝን ተከትለዉ በሚገኙ አስር ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ እንደሚከሰት ይጠበቃል ያሉት ዳይሬክተሩ÷ ለዚህም ቀደም ሲል አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።

በተለይም በነዚህ ወረዳዎች ስር የሚገኙ 40 ቀበሌዎችን ጨምሮ ከአጎራባች ከፍተኛ ቦታዎች የሚነሱ ተፋሰሶች ምክንያት በነዚህ አካባቢዎች ከ90ሺህ ሰዎች በላይ የጎርፍ ተጠቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

@diretube0
8.5K views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-05 19:59:59 የህወሓት አማጺያን ወደ ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማን መግባታቸው ተነገረ

የህወሓት አማጺያን ዛሬ ሐሙስ ከሰዓት በኋላ ወደ የላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎችና አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በከተማዋ አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የአማጺያን እንቅስቃሴ መኖሩ ሲነገር መቆቱን ቢቢሲ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ዛሬ ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ገልጸዋል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰም የህወሓት አማጺያን ሐሙስ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ "ገነተ ማርያም ተብሎ በሚጠራው በኩል ወደ ከተማዋ ገብተዋል" ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ የምትገኘው ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ባሕር ዳር በስተ ምሥራቅ 310 ኪሎ ሜትሮች እንዲሁም የህወሓት አማጺያን መቀመጫ ከሆነችው መቀለ በስተደቡብ 348 ኪሎ ሜትሮች ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት።

አማጺያኑ ወደ ከተማዋ ሲገቡ ምንም አይነት ውጊያም ሆነ ተኩስ እንዳልነበረ ከንቲባው ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን አማጺያኑ "ከተማዋን ይዘዋል" በማለት በርካታ ለደኅንነታቸው የሰጉ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እወጡ መሆናቸውን ምክትል ከንቲባው ገልፈዋል።ጨምረውም በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የተኩስ ድምጽ እንደማይሰማ የተናገሩት ከንቲባው፤ "የህወሓት ታጣቂዎች በከተማዋ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶችን ያወድማሉ የሚል ስጋት መፈጠሩን" ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ከላሊበላ ከተማ ውጪ እንደሚገኙ የተናገሩት ከንቲባው፤ "ከፌደራል እና ከክልል መንግሥት ጋር ኃይል እንዲገባ እና ቅርስ እንዲታደግ ጥረት እየተደረገ ነው" ብለዋል።"የመላው ዓለም ሕዝብ ቅርስ ስለሆነ የዚህ ቅርስ ደኅንነት እንዲረጋገጥ ግፊት መደረግ አለበት" ሲሉ ምክትል ከንቲባው ስጋታቸውን ገልጸዋል።

@diretube0
6.7K views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-04 20:55:52 ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ 157 የጭነት መኪናዎች መቀሌ ደርሰዋል

ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ 157 የጭነት መኪናዎች ትላንት መቀሌ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስፈላጊ መገልገያዎችን የያዙት የጭነት መኪናዎች፣ ከዓለም የምግብ ድርጅት፣ እንደ ዩኒሴፍና ዩ.ኤን .ኤፍ.ፒ.ኤ ካሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች፣ እንዲሁም ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍን ለማቅረብ ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተገኘ ድጋፍን አካትተዋል ብሏል።

@diretube0
5.2K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ