Get Mystery Box with random crypto!

የህወሓት አማጺያን ወደ ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማን መግባታቸው ተነገረ የህወሓት አማጺያን ዛሬ ሐ | ድሬ Tube™

የህወሓት አማጺያን ወደ ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማን መግባታቸው ተነገረ

የህወሓት አማጺያን ዛሬ ሐሙስ ከሰዓት በኋላ ወደ የላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎችና አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በከተማዋ አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የአማጺያን እንቅስቃሴ መኖሩ ሲነገር መቆቱን ቢቢሲ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ዛሬ ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ገልጸዋል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰም የህወሓት አማጺያን ሐሙስ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ "ገነተ ማርያም ተብሎ በሚጠራው በኩል ወደ ከተማዋ ገብተዋል" ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ የምትገኘው ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ባሕር ዳር በስተ ምሥራቅ 310 ኪሎ ሜትሮች እንዲሁም የህወሓት አማጺያን መቀመጫ ከሆነችው መቀለ በስተደቡብ 348 ኪሎ ሜትሮች ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት።

አማጺያኑ ወደ ከተማዋ ሲገቡ ምንም አይነት ውጊያም ሆነ ተኩስ እንዳልነበረ ከንቲባው ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን አማጺያኑ "ከተማዋን ይዘዋል" በማለት በርካታ ለደኅንነታቸው የሰጉ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እወጡ መሆናቸውን ምክትል ከንቲባው ገልፈዋል።ጨምረውም በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የተኩስ ድምጽ እንደማይሰማ የተናገሩት ከንቲባው፤ "የህወሓት ታጣቂዎች በከተማዋ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶችን ያወድማሉ የሚል ስጋት መፈጠሩን" ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ከላሊበላ ከተማ ውጪ እንደሚገኙ የተናገሩት ከንቲባው፤ "ከፌደራል እና ከክልል መንግሥት ጋር ኃይል እንዲገባ እና ቅርስ እንዲታደግ ጥረት እየተደረገ ነው" ብለዋል።"የመላው ዓለም ሕዝብ ቅርስ ስለሆነ የዚህ ቅርስ ደኅንነት እንዲረጋገጥ ግፊት መደረግ አለበት" ሲሉ ምክትል ከንቲባው ስጋታቸውን ገልጸዋል።

@diretube0