Get Mystery Box with random crypto!

ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ 157 የጭነት መኪናዎች መቀሌ ደርሰዋል ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ 157 የ | ድሬ Tube™

ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ 157 የጭነት መኪናዎች መቀሌ ደርሰዋል

ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ 157 የጭነት መኪናዎች ትላንት መቀሌ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስፈላጊ መገልገያዎችን የያዙት የጭነት መኪናዎች፣ ከዓለም የምግብ ድርጅት፣ እንደ ዩኒሴፍና ዩ.ኤን .ኤፍ.ፒ.ኤ ካሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች፣ እንዲሁም ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍን ለማቅረብ ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተገኘ ድጋፍን አካትተዋል ብሏል።

@diretube0