Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና በኡሃን ከተማ የሚኖሩ ሁሉም ዜጎቿ ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ልታደርግ እንደሆነ ገልጻለች | ድሬ Tube™

ቻይና በኡሃን ከተማ የሚኖሩ ሁሉም ዜጎቿ ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ልታደርግ እንደሆነ ገልጻለች

የኡሃን ባለ ሥልጣናት ከ1 ዓመት በፊት በከተማዋ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተከስቶ ወደ ዓለም ሀገራት ተሰራጭቷል በመባሉ ሙሉ ዜጎቻችን የኮሮና ቫይረስ ምርመራን ማድረግ አለባቸው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

የኡሃን ከተማ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሊ ታኦ በበኩላቸው ከሀገር ወደ ሀገር መንቀሳቀስን ከፈቀድን ወዲህ በከተማችን ኑሯቸውን ያደረጉ ስደተኞች ተቀላቅለው አብረውን እየሰሩ በመሆናቸው 7ቱ ላይ የኮቪድ-19 ምልክት በመታየቱ ለሙሉ ነዋሪው ምርመራ ተደርጎ ተጠቂዎች መለያየት አለባቸው ብለዋል፡፡

በቻይና አዲሱ የኮሮና ቫይረስ የዴልታ ዝርያ 61 በሚሆኑ የቻይና አየር መንገድ ሰራተኞች ላይ መታየቱ ተገልጿል፡፡

በኡሃን ከተማ ሁሉም ነዋሪዎች ምርመራ እንዲያደርጉ መመሪያ ሲተላለፍ ዋና ከተማዋን ቤጂንግን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎች ላይም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቻይናውያን ምርመራ እያደረጉ እንደሆነ ሲታወቅ ዳግም በቤት ውስጥ መቆየት የውዴታ ግዴታቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ቻይና የዴልታ ቫይረስ ይጋረጥባት እንጂ ኢኮኖሚዋን በማረጋጋት ላይ እና በኡሃን ከተማ ላይ የነበሩ የወረርሽኙ ተጠቂዎች በመቆጣጠር ረገድ ቁጥሩን ዜሮ አድርጋ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

@diretube0