Get Mystery Box with random crypto!

አዋሽ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ በአፋር ሶስት ቀበሌዎች የጎርፍ አደጋ ተከሰተ ጎርፉ ወንዙ ወደ አ | ድሬ Tube™

አዋሽ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ በአፋር ሶስት ቀበሌዎች የጎርፍ አደጋ ተከሰተ

ጎርፉ ወንዙ ወደ አሳኢታ ሶስት ቀበሌዎች ሰብሮ በመግባቱ ያጋጠመ ነው ተብሏል። አንድ መቶ አባዎራዎች መፈናቀላቸውም ነው የተነገረው
በአፋር ክልል አዉሲ-ረሱ ዞን አይሳኢታ ወረዳ በአዋሽ ወንዝ ሙላት በሦስት ቀበሌዎች የጎርፍ አደጋ መከሰቱን የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሀፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤት የቅድመ-ማስጠንቀቅና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን እንደተናገሩት ከሃምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳዉ ሦስት ቀበሌዎች የአዋሽ ወንዝ ሰብሮ በመውጣት ጎርፍ አስከትሏል።

አደጋው ቀድሞ በተከናወኑ የቅድመ-ጥንቃቄቅ ስራዎች ህብረተሰቡ ከአካባቢዉ እንዲወጣ በመደረጉ የተፈናቀሉ ሰዎች ከመቶ አባዋራዎች የማይበልጡ ሲሆን፤ ጎርፉ 50 ሄክታር መሬት በሚሆን የእርሻ መሬት ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።
ጎርፍ የተከሰተባቸዉ ቀበሌዎች የከርቡዳ፣ ኮሎዱራና ሂነሌ ቀበሌዎች ሲሆኑ÷ ጎርፉ የሰበረበትን አካባቢ ለመዝጋት ከሚመለከተዉ የተፋሰስ ባለሰልጣን ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ ነዉ ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

በክረምቱ ከፍተኛ ዝናብ እየተመዘገበ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በክልሉ የአዋሽ ወንዝን ተከትለዉ በሚገኙ አስር ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ እንደሚከሰት ይጠበቃል ያሉት ዳይሬክተሩ÷ ለዚህም ቀደም ሲል አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።

በተለይም በነዚህ ወረዳዎች ስር የሚገኙ 40 ቀበሌዎችን ጨምሮ ከአጎራባች ከፍተኛ ቦታዎች የሚነሱ ተፋሰሶች ምክንያት በነዚህ አካባቢዎች ከ90ሺህ ሰዎች በላይ የጎርፍ ተጠቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

@diretube0