Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐን ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ የኢትዮጵያ | ድሬ Tube™

አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐን ሰዎችን መግደሉ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢ ፕ ድ)

አሸባሪው ሸኔ በጊዳሚ ወረዳ 168 ንጹሐንን መግደሉን በኦሮሚያ ክልል የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጊዳሚ ወረዳ አሸባሪው ሸኔ ዘግናኝ ግድያዎችንና የንብረት ውድመት ፈጽሟል።

በወረዳው በተለያዩ ቦታዎች 81 ሰዎችን እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎችን በድምሩ168 ንጹሐን መገደላቸውን ገልጸዋል። አሸባሪው ሸኔ በወረዳው በቆየበት ጊዜ 30 የመንግሥት ተቋማትን ንብረቶችን ማውደሙንና ዝርፊያ መፈጸሙን አስታውቀዋል።

መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በወሰደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን የጊዳሚ ወረዳ ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ መውጣቱን የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይ እና የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ አስታወቁ።

@Diretube0