Get Mystery Box with random crypto!

በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶቹን ሰኞ የካቲት 14 2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የ | ድሬ Tube™

በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶቹን ሰኞ የካቲት 14 2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ

ኤጀንሲው ሰኞ በሚጀምረው አገልግሎቱ ከአዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ውጭ ያሉ መደበኛ አገልግሎቶቹን መስጠት እንደሚጀምር ይፋ አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው አገልግሎቶችን በሁሉም ክ/ከተማ እና ወረዳው በተዘጋጀ መርሃ ግብር ነዋሪው እንዲስተናገዱ እንደሚደረግ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ኤጀንሲው አዲስ ሴኪውርድ የሰርተፍኬት ፕሪንተር ለክ/ከተማ እና ወረዳ እያሰረጨ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ከ2013ዓ.ም ጀምሮ ፎርጀሪን ሙሉ ለሙሉ ያስቀርልኛል እንዲሁም የውስጥ ሌብነትንም ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለውን “የሴኪውርድ “ ፕሪንተር ወደ ስራ በማስገባት የማሰራጨት እና የኮንፊግሬሽን ስራ በክ/ከተማ እና በወረዳ ጽ/ቤቶች ሲሰራ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

የከተማውን የወሳኝ ኩነት ማስረጃዎች አለም ዓቀፍ ደረጃ እንዲኖራቸው፣ የሰርተፍኬቶቹን ደህንነት ከፍ የሚያዱርግ፣ እና ሲስተም ባለባቸው እና በሌለባቸው ወረዳዎች አገልግሎት በመስጠት የእጅ ፅሁፍ ንክኪን ለመጨረሻ ግዜ የሚያስቀር ነው ተብሎለታል።

ከዚህ ቀደም ከነበረው መደበኛ ሰርተፍኬት በውስጡ የባለማስረጃውን ስም እንዲሁም ፎቶግራፍ በምስጢራዊ ህትመት ይዞ የሚወጣ ሲሆን በ UV ማሽኖች ተፈትሾ በቀላሉ ኦርጅናል መሆን አለመሆኑን ከባለማስረጃው ስምና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማመሳከር መለየት የሚያስችል ሲሆን በውጭ የሚሰራ የፎርጀሪ ስራን ከማስቀረት ባሻገር በሰርተፍኬቱ ላይ በሚኖር ልዩ Licensed QR ኮድ ፈቃድ የሚሰጣቸው ተቋማት ሰርተፍኬቱ ትክክለኛ ስለመሆኑ ማረጋገጥ የሚችሉበት ስርዓት እንደያዘ ኤጀንሲው አስታውቋል።

በአልግሎት ወቅት ታትመው የሚሰጡት የወሳኝ ኩነት እና የያላገባ የምስክር ወረቀቶች በዋናነት ማስረጃው (ሰርተፍኬቱ) በየትኛው ወረዳ፣ በየትኛው ባለሙያ (User) እና ለማን እንደታተመ መረጃ በመያዝ በማዕከል ቁጥጥር የሚያደርግ አሰራር ያለው ከመሆኑ ባሻገር በምን አይነት ኮምፒውተር የህትመት ትዕዛዝ እንደተሰጠው መለየት የሚያስችል ዘመናዊ አስራርን እንደሚያካትት የአዲስ አበባ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

@Diretube0