Get Mystery Box with random crypto!

በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ | ድሬ Tube™

በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም ብለዋል

ጄነራል ብርሃኑ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያላቸው ትስስር ጥብቅ መሆኑን በመግለፅ ጎረቤት ሀገሯን ሱዳንን የምታጠቃበት ምንም ምክንያት የለም ሲሉ ገልፀዋል።

የድንበር ጭቅጭቅ አለ ይሄ የድንበር ጭቅጭቅ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ነው መፈታት ያለበት የሚል ፅኑ አቋም አላት ኢትዮጵያ አሁን ከጁንታው ጋር ጦርነት ላይ እያለች በጣም ብዙ ትርፍ ኃይል ኖሯት ሱዳንን የምታጠቃበት አይነት ቁመና ላይ አይደለችም ያለችው ሲሉ ተናግረዋል። መሬትን በተመለከተ በሰላምና በድርድር በህግ ይመለሳል ብለዋል።

ብዙ ጊዜ የመሬት ጭቅጭቅ መጨረሻ ፍርድ ቤት ነው የሚሄደው ይሄን ስለምናውቅ እኛ ሱዳንን የመተናኮል ፍላጎት የለንም ነገር ግን ሱዳን የመተናኮል ምልክቶች እያሳየች ነው፤ ጁንታውን በብዛት አስገብታለች እንደገና የታላቁ የህዳሴ ግድብን ለማደናቀፍ እየሰራች ነው እናውቃለን፤ እነሱ የላኳቸው ኃይሎች እየመጡ እየደመሰስናቸው ነው።

የራሳችንን ተላላኪ መደምሰስ እንጂ ለምን ትልካላችሁ ብለን ከሱዳን ጋር ወደአታካራ መግባት አንፈልግም ፤ ከሱዳን ጋር ግጭትም ጦርነትም አንፈልግም፤ ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሻሻል ነው የምንፈልገው በጣም ይሻሻላል ብለንም እናስባለን።

እንዳንድ የሱዳንን ህዝብ እና መንግስት የማይወክሉ ግን በሌላ ሶስተኛ ወገን የተገዙ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ግንኙነት ለማበላሸት የሚሰሩ አሉ ፤ እነማን እንደሆኑም ለይተን እናውቃቸዋለን፤ ታሪክ ይፈርዳል፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝብ ችግሩን በህዳሴ ግድብም ይሁን በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ይፈታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

@diretube0