Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል ተጥሎ የነበረው የምሽት እንቅስቃሴ ገደብ ለጊዜው ተነሳ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ጀ | ድሬ Tube™

በኦሮሚያ ክልል ተጥሎ የነበረው የምሽት እንቅስቃሴ ገደብ ለጊዜው ተነሳ

3 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11:30 ዜጎች እና ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ አዋጅ ተግባራዊ ተደርጎ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ህጓ፥ የክልሉን እና አገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይጎዳ ከግምት በማስገባት ይህ ውሳኔ ዳግም ተላልፏል ብለዋል።

በቀጣይ ሁኔታዎች እየታዩ አዋጁ እንደገና በመላው ክልሉ እንዲሁም እንደየ አከባቢዎች ሁኔታ ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የእንቅስቃሴ ገደቡ ለጊዜው ቢነሳም÷ አስፈላጊው ፍተሻ በተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ህዝባዊ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል።

@diretube0