2023-01-17 21:30:39
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ጫጩት ዶሮዎችን በማራባት እንቁላል ለግቢው ማህበረሰብ እያቀረበ መሆኑን ተገለፀ
===============
የደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ፥ ጥር/2015 ዓ/ም
የደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ከመማር ማስተማር ተግባሩ በተጨማሪ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ቀርጾ በመስራት ላይ ይገኛል ከእነዚህ ተግባራት መካከል በንብ እርባታ ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ፣ በወተት ላም አርባታ ፣ በሻይ ቅጠልና ቡና እንዲሁም በዶሮ እርባታ ዙሪያ እየሰራ ይገኛል ፡፡
የካምፓሱ ችፍ አክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሐኑ ዓለሙ ካምፓሳችን ለዶሮ እርባታ ምቹ በመሆኑ ጫጩት ዶሮዎችን ከአርባ ምንጭ በማስመጣት በግቢያችን ባዘጋጀነው ማዕከል እያራባን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ዶሮዎች ሙሉ በሙሉ መጣል ሲጀምሩ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አልፈን ለቡሬና አካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል። ከእንቁላል በተጨማሪም የስጋ ዶሮዎችን በማራባት ለማህበረሰቡ ለማቅረብ በዕቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በቡሬ ካምፓስ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ጋሹ እንደሚሉት ይህ ማዕከል በመቋቋሙ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እንደሚሰጥ ጠቅሰው ለአብነትም በዘርፉ ለሚማሩ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች እንደ ስልጠና ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ብለዋል። በዚህ ዘርፍ የተደራጁ ወጣቶች፣ ሴቶች እናቶች የልምድ ልውውጥ የሚያገኙበትና እንደማስተማሪያ ማዕከልም ይገለገሉበታል ሲሉ ገልፀዋል። ማዕከሉ በአሁኑ ስዓት ለ8 ሰዎች የስራ ዕድል እንደፈጠረም ጨምረው ገልጸዋል ፡፡
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ቻላቸው ይትባረክ እንደገለጹት በዚህ ማዕከል ውስጥ አራት ሺ የሚሆኑ የአንድ ቀን ጫጩቶችን አስመጥተው አስፈላጊውን ሳይንሳዊውን መንገድ በተከተለ ሁኔታ እንክብካቤ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
///////////////////////////////
ከታች የተቀመጡትን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዌብሳይት www.dmu.edu.et
ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University
ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia
እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/
ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/
"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!
1.8K viewsedited 18:30