2023-01-16 22:09:23
ከደረቅ ቆሻሻ የሚመረት ጭስ አልባ የከሠል ምርት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
====================
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፥ ጥር 8/2015 ዓ.ም
በዩንቨርስቲያችን የማህበረሰቡን ችግር ፈች የሆኑ በርካታ ፕሮጀክቶች ተቀርው ወደስራ ገብተዋል። በዛሬው ዕለትም ጭስ አልባ የከሠል ምርትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት የዩንቨርስቲው አመራሮች፣ ሠራተኞችና ከልማት ባንክ የመጡ እንግዶች በተገኙበት የፕሮጀክቱ ሀሣብና የተገኘውን ውጤት የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር አስካለ ማርያም አዳሙ ይህ ፕሮጀክት በአካባቢያችን ከሚገኙ ደረቅ ቆሻሻዎች የሚመረትና ጭስ አልባ በመሆኑ ለዩንቨርስቲውና ለከተማው ባጠቃላይ ለሀገራችን ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የመስሪያ ቦታና ማሽኖች ተሟልተው በስፋት ወደስራ ይገባ ዘንድ ለፕሮጀክቱ ባለቤት እገዛ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ባለቤት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ ፈቃዱ እንግዳ ይህ የከሰል ምርት ፦ ጭስ አልባ፣ ረዘም ላለ ጊዜ የሚነድ፣ የእሳት ብልጭታ የሌለውና ከአቧራ ነፃ በመሆኑ በባህላዊ መንገድ ከሚመረተው ከሰል እንደሚለይ ገልጿል። ከተማን ፅዱ ለማድረግ፣ደንና አካባቢን ለመጠበቅ፣ የሴቶችና ህፃናትን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ፣የስራ ዕድል ለመፍጠርና የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም አስረድቷል፡፡
ከከሰሉ በተጨማሪም ለተፈጥሮ ማዳበሪያና የዕፅዋትን ተባይና ፈንገስ ለመከላከል የሚያስችሉ የእንጨት ኮምጣጤና የእንጨት ሬንጅ የተሰኙ ምርቶች ማምረት እንደሚቻልም አሳይተዋል፡፡
በኢኖቬሽን ሚኒስቴር እውቅናና ሽልማት እንዳገኘም ተጠቅሷል፡፡
አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይኼይስ አረጉ ተምሮ ራስን ከመለወጥ አልፎ ለማህበረሠቡ ትልቅ ፋይዳ ያለው ስራ መስራት የሚደነቅና የሚበረታታ ስለሆነ የዩንቨርስቲውም ሆነ የከተማው ማህበረሰብ ድጋፍና ክትትል ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
ከታች የተቀመጡትን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዌብሳይት www.dmu.edu.et
ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University
ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia
እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/
ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/
"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"
877 viewsedited 19:09