2023-01-11 11:56:34
የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች አንድ ጉርሻ ለወገኔ በሚል ድጋፍ አሰባስበው የገና በዓልን አቅም ከሌላቸው ወገኖች ጋር ማሳለፋቸውን ገለፁ
================
የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ከተማሪዎች ህብረት አመራሮች ጋር በመተባበር አንድ ጉርሻ ለወገኔ በሚል ከዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ ድጋፍ በማሰባሰብ በተለያዩ ምክንያቶች በዓልን ለማክበር አቅም የሌላቸው ወገኖችን በመለየትና ለበዓል የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በማሟላት በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ አድርገዋል፡፡
በዩንቨርሲቲው የአራተኛ ዓመት የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ ተማሪ ቶማስ አበባው እኛ በዓልን ተደስተን ስንውል በጎነት ለራስ ነውና ለምን የአቅማችንን በማድረግ ወገኖቻችንን አናስብም በሚል ድጋፉን ለማድረግ እንደተነሳሱና ልምድ ካላቸው ተማሪዎች ህብረት ጋር በመተባበር ገንዘብ ከማሰባሰብ ጀምሮ ከብት ገዝቶ እስከ ምገባ ድረስ በመስራት ከ200 በላይ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ተደራሽ እንዳደረጉ ተናግሯል፡፡
ሌላው የአራተኛ አመት የመካኒካልና ኢንደስትሪያል ምህንድስ ተማሪና እንዲሁም የተማሪዎች ህብረት የፋይናንስ ክፍል ተጠሪ ተማሪ ደርበው መላክ በዓሉን ከግል ደስታ ይልቅ ሌሎችን ማሰብ ትልቅ የአዕምሮ እርካታ እንደሚሰጥ ገልፆ በማማከርና ገንዘቡን በተመለከተ ክትትል በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንደተወጣ ተናግሯል፡፡
ባጠቃላይ ከዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ 30 ሺ ብር አሰባስበው የቀንድ ከብትና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በማሟላት በዓልን ከወገኖቻቸው ጋር ማክበራቸው ለወደፊቱም መነሳሳትን ፈጥሮልናል ብሏል፡፡
ለወደፊቱም ሁሉም ማህበረሰብ ይህንን ቢለምድና በሰፊው ቢሰራበት የተሻለ እንደሚሆን አሳስቦ በእነሱ በኩልም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፁዋል፡፡
የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ጌጤነህ ሸገን ከዚህ በፊትም ተማሪዎች በግላቸው አንዳንድ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልፆ ለበዓልም አቅም የሌላቸውንና የተፈናቀሉ ወገኖችን በተወሰነ መልኩ ስሜታቸውን መጋራት ተችሏል ብሏል፡፡ በተማሪዎች ህብረት በጎ አድራጎት ዘርፍም አልባሳትን በማሰባሰብ ድጋፍ ማድረግ እንደተቻለና ወደፊትም በቋሚነት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በመጨረሻም የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ በቀናነት ትብብር ስላደረገላቸውና የከተማው ማህበረሰብም ሁሌም ከጎናቸው ስለሆነ አመስግኗል፡፡
ዌብሳይት www.dmu.edu.et
ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University
ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q
ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia
እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/
ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/
"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"
ከእኛ ጋር ሰለሆናችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!
3.4K viewsedited 08:56