Get Mystery Box with random crypto!

🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ🗣

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_mossion — 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ🗣 ወ
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_mossion — 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ🗣
የሰርጥ አድራሻ: @christ_mossion
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.93K
የሰርጥ መግለጫ

ዮሐንስ1፥5 ብርሀንም በጨለማ ይበራል፥ጨለማም አላሸነፈውም
ይህ channel እግ/ርን የምናመልክበት አብረን ተያይዘን
ተደጋግፈን ይህን ዘመን የምናልፍበት ወንጌልን ላልሰሙት የምስራጅ የምናበስርበት channel ነው።

ሀሳብ/አሰተያየት; @Gospel_Worldbot
ዝማሬዎች በየቀኑ ማግኘት ከፈለጉ👇👇
@Enamelkw_tube

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-11-06 07:25:59 . የሚለውጥ ፀሎት!
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
በመፈሳዊ ህይወታችሁ መበርታት ለምትፈልጉ ሁሉ!!
አሁኑኑ አብራችሁኝ ፀልዩ የአለምን ነገር ሁሉ የሚያስንቅና ለውጦ የሚያስቀር መንፈስ ያገኛችኋል!
ክብሩን ለምትራቡ ሁሉ
በአገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ!!
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
Holy Tube Ethiopia
....………….….. •°○......….............
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot
sʜᴀʀᴇ  sʜᴀʀᴇ   sʜᴀʀᴇ
ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion
@christ_mossion
75 viewsKingdom Family, 04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 20:23:00 #የሮሜ_መልእክት_ጥናት

የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ጳውሎስ ሮሜ 2:1-16 ያለውን ክፍል ለማን እንደ ጻፈው በሚመለከት በአሳብ ይለያያሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጳውሎስ ይህንን የጻፈው በሮሜ 1፡18-32 ያለውን ኃጢአት ለፈጸመ፤ ነገር ግን በጥሩ ሥነ ምግባር ለመኖር ለሚሻ አረማዊ ነው ይላሉ፡፡ ለእኔ እንደሚመስለኝ ጳውሎስ የጻፈው ለአይሁዳውያን አንባቢዎቹ ነው። በምዕራፍ 2፡12-16 ስለ ሕግ ያቀረበው ሐተታ ከአሕዛብ ይልቅ ለአይሁዳውያን ትርጉም ይሰጣቸዋል፡፡ በ2:17 ላይ በግልጽ አንባቢዎቹ አይሁዳውያን እንደሆኑ አስፍሯል። በዚህ ስፍራ አይሁዳዊ በማለቱ በምዕራፍ 2 የመጀመሪያ ክፍል ላይ ለአሕዛብ የሚናገር ቢሆን ኖሮ አባባሎ እንግዳ ይሆን ነበር፡፡

አይሁዳውያን ሕግ እንደ ጣሱ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔርን አለመታዘዝ በተመለከተ አይሁዳውያን ሊናዘዙት የማይፈልጉት ነገር ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት እስራኤልን ስለ ኃጢአቷ በመክሰሳቸው ተሰድደዋል።

2. በዚህ ቁጥር ላይ እነዚህ ነገሮች የሚለው ቃል በሮሜ 1፥29–31 ውስጥ የተጠቀሱትን ኃጢአቶች ያሳስበናል። ይህን በሚያደርጉም ሰዎች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ፍርዱን ወስኖአል። የእግዚአብሔር ፍርድ በእውነት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ ፍርዱም በትክክልና ያለ አድልዎ ነው። እርሱ የሚፈርድብን በሥራችን ብቻ ሳይሆን፥ ነገር ግን በልባችን ውስጥ በያዝነውም ነገር ጭምር ነው (መክ. 12፥14፤ ራእ. 2፥23)

3. እነዚያ ሰዎች (በተለይም አይሁዳውያን) ራሳቸውን ጻድቃን አድርገው የሚቆጥሩ ነገር ግን እነዚህን ኃጢአቶች ከማድረግ የማይቆጠቡ ከእግዚአብሔር ፍርድ ማምለጥ አይችሉም። ምንም እንኳ አይሁዳውያን የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ ቢሆኑም፥ በውጪያቸውም ከአረማውያን ይልቅ ጻድቃን መስለው ቢታዩም፤ በኃጢአታቸው ሙሉ ቅጣታቸውን መቀበላቸው አይቀርም።

4. አይሁዳውያን እግዚአብሔር ኃጢአታችንን አይቆጥርብንም ብለው አስቡ ስለዚህም ንስሓ መግባት አያስፈልገንም አሉ። ነገር ግን በጣም ተሳስተዋል። በእርግጥ እግዚአብሔር ለአይሁ ዳውያን ታላቅ ደግነቱን ቻይነቱንና ታጋሽነቱን አሳያቸው፤ እነርሱ ግን ባለውለታ ሆነው አልተገኙም። ለእነዚህ በረከቶች ያሳዩት ንቀት ነበር፤ እግዚአብሔር ምሕረት እንዳደረገላቸውም አልተገነዘቡም። እግዚአብሔር ግን ይህንንም ማድረጉ በኃጢአታቸው ንስሓ እንዲገቡ ነበር። ለአይሁዳዊም ሆነ ለአረማዊ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የመጀመሪያው ደረጃ ንስሓ ነው። ነገር ግን ትዕቢተኞች ሆነን ኃጢአታችንን ሳንናዘዝ ብንቀር በእርግጥ እግዚአብሔርን ልናገኘው አንችልም። ንስሓ ምንድን ነው?

1. በመጀመሪያ ኃጢአትን ተገንዝቦ መናዘዝ፤ ሁለተኛ ከዚያ ኃጢአት መራቅ ነው።

2. ኃጢአታችንን መናዘዝ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ከዚያ ኃጢአት መራቅ ስንችልና ጨርሶ ስንተወው በእውነት ንስሓ ገብተናል ማለት እንችላለን (ምሳ. 28፥13)።

በእውነት ንስሓ ስንገባ አሳባችንና ምኞታችን ሁሉ ይለወጣል፤ ከክፋት ተለይተን ወደ እግዚአብሔር ፊታችንን እንመልሳለን። ንስሓ ማለት የአእምሮአችንና የልባችን መለወጥ ማለት ነው። ማንም ሰው ቢሆን ንስሓ ሳይገባ ወደ እግዚአብሔር መምጣት አይችልም።

አምላካችን ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ እስቲ አስታውሱ! እርሱ አይቃወመንም፥ አይንቀንም፥ ፈቃዱንም እንድናደርግ አያስገድደንም፥ የማያስፈልግ ችግርና መከራ ውስጥ አይከተንም ይልቁንም ከደግነቱ የተነሣ ንስሓ እንድንገባ ይመራናል። ልክ አፍቃሪ አባት ልጆቹን ወደ ራሱ እንደሚጠራ፥ እግዚአብሔርም ወንዶችና ሴቶችን ወደ ራሱ ይጠራል። እግዚአብሔር ፍጹም ታጋሽና ለሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ ዕድል ይሰጣቸዋል (2ጴጥ 3፥9)። ታዲያ እንዴት ንስሓ ገብተን ወደዚህ አፍቃሪ አምላክ አንመለስም?

5. እግዚአብሔር አፍቃሪና መሓሪ አባታችን መሆኑ በፍጹም እውነት ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ሰዎችን በኃጢአታቸው ምክንያት እንደሚቀጣቸው የዚያኑ ያህል እውነት ነው። እርሱ በኃጢአትም ላይ እጅግ ታላቅና አስፈሪ የሆነም ቁጣ አለው (ዕብ. 10፥30311 12፥29)። ንስሓ የማንገባ ከሆነ የእግዚአብሔርን ምሕረት፥ ፍቅርና ይቅርታ ማግኘት አንችልም፤ ይልቁንም ታላቅ ቁጣውን እንቀበላለን። እንግዲህ ምርጫው የራሳችን ነው።

6. የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርድ በሚገለጥበት በታላቁ ፍርድ ቀን እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል (ቁ.5)። ግን እንዴት ነው የሚፈርድብን? ሽልማት የሚሰጠንስ በምን መስፈሪያ ነው? እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው በሥራው መጠን ይከፍለዋል፤ (መዝ. 62፥12፣ ምሳ. 24፥12፤ ኤር 17፥10፤ 32፥19፤ 2ቆሮ. 5:10፤ ራእ. 22፥12)። እዚህ ላይ ሁለት እውነቶችን በአእምሮአችን እንያዝ፤ መጀመሪያ የዳንነው በእምነት ነው፤ ሁለተኛ የሚፈረድብን በሥራችን መጠን ነው።

በክርስቶስ በማመናችን ብቻ ደኅንነትን እንቀበላለን (ኤፌ. 2፥8-9)። በመልካም ሥራ ልንድን አንችልም፤ የቱንም ያህል መልካም ሥራ ብንሠራ፥ እምነት ከሌለን ሊያድነን አይችልም።

በክርስቶስ ላይ እውነተኛ እምነት ካለን ግን፥ እርሱ ሁልጊዜ መልካም ሥራን ያሠራናል። ሥራችንና ጠባያችን መልካም ካልሆነ ግን እምነታችን እውነተኛ እምነት አይደለም (ያዕ. 2፥14-17)። ሰው እምነት ሳይኖረው መልካም ሥራን መሥራት ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን መልካም ሥራን ሳይሠራ እምነት ሊኖረው አይችልም። መልካም ፍሬ የጥሩ ዛፍ ማስረጃ እንደሚሆነው መልካም ሥራ ደግሞ የእምነታችን ጉልህ ማስረጃ ነው። (ማቴ. 7፥17–20)።


ይቀጥላል...

ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፣ ገጽ 347-348፣ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፣ የሮሜ መልእክት ማብራሪያ፣ ገጽ 19-20

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion

         
578 views✞Natneal, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 20:18:05 #የሮሜ_መልእክት_ጥናት


የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርድ (2፥1)

ጳውሎስ እዚህ ላይ ለሰዎች ሁሉ ታላቅ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። በሌሎች ሰዎች ላይ አትፍረድ በሌሎች ሰዎች ላይ ለመፍረድ እንዴት እንቸኩላለን! በእኛ ግምት ራሳችን ጻድቃን
የሆንን ይመስለናል፤ ስለዚህም በሌሎች ላይ ለመፍረድ የበቃን ነን ብለን እናስባለን። የሌሎችን ኃጢአትና ስሕተት ሁሉዐእንመለከታለን ነገር ግን የራሳችንን ከቶ አንመለከትም።

የማደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ብለህ ትገምት ይሆናል፤ እግዚአብሔር ግን የልብህን አሳብ ይመዝናል (ምሳ. 21፥2)። ስለራሳችን ኃጢአት በጣም ብንጨነቅ ኖሮ የሌሎችን ኃጢአት ለመመልከት ጊዜ አይኖረንም።

በእኛ በክርስቲያኖች መካከል እርስበርስ የመፈራረድ ልምድ ስላለብን በዚህ ስሕተታችን ንስሓ መግባት ይኖርብናል። የኢየሱስንም ቃል እናስታውስ፥ «በእናንተ ላይ እንዳይፈረድባችሁ በማንም ሰው ላይ አትፍረዱ” (ማቴ. 7፥1-5፤ ሮሜ 14፥10)።

በቁ. 1 ላይ ያለው ማስጠንቀቂያ ለሰዎች ሁሉ ቢሆንም እዚህ ላይ ጳውሎስ ሊናገር የፈለገው በተለይ ለራሱ ሕዝብ ለአይሁዳውያን ነው። ከሌሎች ወገኖች ሁሉ ይልቅ አይሁዳውያን በሌሎች ሰዎች ላይ የመፍረድ ልምድ አላቸው። በተለይም አይሁዳውያን ባልሆኑ በአረማውያን ላይ ይፈርዳሉ። አይሁዳውያን ትዕቢተኞች ነበሩ፤ ራሳቸውንም እንደጻድቃን ይቆጥሩ ነበር፤ ለምን እንዲህ ሆኑ?

ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆነው ነገር እንዲገባን የአይሁዳውያንን ታሪክ መመልከት ይኖርብናል። በመጀመሪያ፥ ሰዎች ሁሉ የሚያመልኩት ጣዖትን ስለነበር፤ የሚኖሩት በኃጢአት ነበር። እግዚአብሔር ከሕዝብ መካከል አንዱን ወገን በመምረጥ እንዲያከብሩትና እንዲታዘዙለት ለማድረግ አሰበ። ስለዚህ ከክርስቶስ ዘመን ሁለት ሺ ዓመት በፊት፤ እግዚአብሔር አብርሃም (ወይም አብራምን) አዲስ ትውልድ ማለትም የአይሁድን ትውልድ ለማቋቋም ጠራው (ዘፍ. 12፥1-3)። እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ እንዲሆኑ አይሁዳውያንን መረጠ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለአይሁዳውያን የራሱን ሕግ ሰጣቸው። ከዚህም ሕግ ዋናው ክፍል ዐሥርቱ ትእዛዛት ነው (ዘጸ. 20፥1–17)።

እንግዲህ በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሔር የተመረጡ ሕዝብ ስለሆኑና ሕጉንም የተቀበሉ በመሆናቸው፤ አይሁዳውያን እኛ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ጻድቃን ነን ብለው አሰቡ። ስለዚህም አረማውያንን (አይሁዳውያን ያልሆኑትን ሁሉ) መናቅ ጀመሩ፤ አረማውያን አምላክ የለሾችና ኃጢአተኞች ናቸው አሉ።

እዚህ ላይ ግን ጳውሎስ የሚነግራቸው፤ ምንም እንኳ በእግዚአብሔር የተመረጡና ሕጉንም የተቀበሉ ህዝብ ቢሆኑም፥ የእግዚአብሔርን ሕግ ከልባቸው በእውነት የሚፈጽሙት አልነበሩም። ይልቁንም ለሕግ የሚታዘዙት ከውጪ ብቻ ነው፤ በልባቸው ግን ልክ እንደ አረማውያን በኃጢአት የተሞሉ ናቸው። እንዲያውም ከአረማውያን ይልቅ አይሁዳውያን በጣም በደለኞች ናቸው! ምክንያቱም አይሁዳውያን የእግዚአብሔር ትእዛዞች ምን እንደሆኑ በትክክል ያውቃሉ። ይሁን እንጅ የራሳቸውን ኃጢአት ለማየት ጨርሶ አልቻሉም።


ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፣ ገጽ 347


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
799 views✞Natneal, 17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 07:00:29 የኔ ሰላም አንተ ነህ መንፈስ ቅዱስ
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
የእውነት መረጋጋት እና
እውነተኛ ሰላም እንዲሰማችሁ ትፈልጋላችሁ? ስሙት አሁኑኑ
ሁሉን እረሳለሁ ይቀልብኛል ጥያቄዬ አብሬህ ስሆን ፊትህን ሳይ ጌታዬ!

መንፈስ ያለበት ድንቅ ፀሎት!
በአገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ!!
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
Holy Tube Ethiopia
....………….….. •°○......….............
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot
sʜᴀʀᴇ  sʜᴀʀᴇ   sʜᴀʀᴇ
ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion
@christ_mossion
64 viewsKingdom Family, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 20:40:13
ለዘፈን እጅ የማይሰጥ ትውልድ ይሄ ነው።
"በመንፈሳዊ ቅኔ የሰከረ ለክርስቶስ የሸፈተ መልካም ወጣት ነው።"

የማንን አዲስ መዝሙር ማዳመጥ ትፈልጋላችሁ???
ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጫን የተወዳዶቹን ዘማሪያንን መዝሙር ማግኘት ትችላላችሁ።
668 views✞Natneal, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 19:39:56 ​​ የእግዚአብሔር ቃል አያረጅም

አስገራሚው የወንጌላዊ ቦንኬ ገጠመኝ
_



ለወንጌል አገልግሎ
ት ወደ ጀርመን ሀገር ለመስበክ የተጋበዘው ወንጌላዊ ቦንኬ ገና በማለዳው ካረፈበት ሆቴል የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ አንድ መናፈሻ ገብቶ አረፍ አለ። አጠገቡ አንድ በሀያዎቹ የሚገመት አንድ ወጣት ፀሐይ ሲሞቅ አየ። ረዘም ያለውን ዝምታ የሰበረ ንግግር ተናገረ ሁልጊዜም እንደሚያደርገው በዚህ አጋጣሚ የወንጌሉን የምስራች ለመናገር ስለፈለገ።

ቦንኬ፡- "የማለዳው ፀሐይ እንዴት ናት?" ብዬ ዝምታውን ሰበርኩኝ።

ወጣቱ ልጅ፡- "ቆንጆ ነው በጣም ደስ ይላል" አለኝ።

ቦንኬ፡- "ይህን ውብ ፀሐይ በነፃ የሰጠን ማን እንደሆነ ታውቃለህ?" አልኩት።

ወጣቱ ልጅ፡- "አላውቅም" አለ።

ቦንኬ፡- "መጽሐፍ ቅዱስ ታነባለህ?"አልኩት።

ወጣቱ ልጅ፡-  "ፊቱን ጭፍግግ አድርጎ አላነብም ለምን አነባለሁ መጽሐፍ ቅዱስ እኮ ያረጀ መጽሐፍ ነው። እንደምታየኝ እኔ ወጣት ነኝ። የ21 ክፍለ ዘመን ሰው ነኝ ወጣት ነኝ ለእኔ የሚመጥኑ አዳዲስ ፍልስፍናዎችን ያየዙ መጽሐፍትን አነባለሁ እንጂ ያረጀ እና ዘመን ያለፈበትን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ሊያደርግልኝ አነባለሁ" አለኝ፡፡

ቦንኬ፡- ጥቂት ሰኮንዶች ዝም ካልኩኝ በኋላ የውይይቱን አቅጣጫ የቀረኩኝ በማስመሰል "አሁን እዚህ ምን ትሰራለህ" አልኩት።

ወጣቱ ልጅ፡- "ዘና ብሎ እንደምታየው ፀሐይ እየሞኩኝ ነው" አለኝ

ቦንኬ፡- ቆፍጠን ብዬ "ፀሐይ ለምን ትሞቃለህ እንደ አንተ አይነቱ የ21 ክፍለ ዘመን ወጣት ይህችን አሮጌ ፀሐይ መሞቅ አልነበረበትም። የፀሐይ እድሜ ብዙ ሚለየን አመት እንደሆነች ከሳይንስ እንደተማከርክ እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህ እንደ አንተ አይነቱ ወጣት አዲስ ነገር መፈለግ ይኖርበታል እንጂ አሮጌ ነገር መፈልግ አይኖርበትም?" በማለት በማፌዝ ተናገርኩት። ወጣቱ ግራ በመጋባት ማዳመጥ ጀመረ። ቦንኬም በመቀጠል "አየህ ፀሐይ እድሜዋ ረዥም ቢሆንም ዛሬም ብርህን ትሰጣለች፣ ሙቋቷ አልቀነሰም፣ ድምቀቷ አልቀነሰም። ዘር፣ ቀለም፣ሃይማኖት ሳትለይ ለሁሉ ታበራለች። መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ነው። ዛሬም ለሰው ዘር ሁሉ ያበራል፣ ነፃ ያወጣል፣ ይለውጣል። የፀሐይ ብርሃን ወደ አንተ የመጣው ከ93 ሚሊየን ማይልስ ርቀት ነው። አንተ ግን ወደ ፀሐይ ለመድረስ ብዙ አልተጓዝክም። ሲነጋ ለፀሐይ በርህን ከፍተህ አሁን ደግሞ ወጥተህ በፀሐይ ፊት ተቀምጠህ ሁለተናህን ለፀሐይ ብርሃኗ እና ለሙቀቷ ሰጠህ። የእግዚአብሔርም ቃል ከአንተ የሚጠበቀው ይሄ ነው። ልብህን ለቃሉ እና ለኃይሉ ብርሃን ክፈት በውስጡ ላለው እውነቱ ራስህን ስጥ"፡፡

ወጣቱ ልጅ፡- ፊቱ በርቶ ደስ ብሎት መስማት ቀጠለ።

የእግዚአብሔር ቃል አያረጅም ዛሬም ይሰራል፣ ለዘላለም ህያው ነው። ከቃሉ የሚመነጨው ብርሃን በውስጥ የተዳፈነውን እምነት እና ተስፋ ቀስቅሶ ወደ ዘላለም ህይወት ይመራል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የህይወታችን መመሪያችን እንዲሆን ሁልጊዜም ከምንም ነገር በላይ ጊዜ ሰጥተን ልናጠናው፣ ልናሰላስልው ይገባል።

 ምንጭ:- መለከት Tube

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion             
707 views✞Natneal, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 16:38:04 . ኑ ከእኔ ጋራ በመንፈስ
ት/ቤት ደርሰን እንምጣ
      ━━━━━⊱✿⊰━━━━
━
አገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ!
በመንፈስ ት/ቤት መሄድ እና መዋል ይቻላል!
ብዙዎቻችሁ ስፀልይ ህልውናው አይሰማኝም ትሉኛላችሁ እኔ ግን መንገድ ላይ እንኳን እንዲህ መገኘቱ ከቦኛል! ግን እንዴት ስሙት?
ይሄን ፀሎት አብረውኝ በፀለዩ ሁሉ ላይ ከባድ መንፈስ መጣ!!
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
    Holy Tube Ethiopia  
............……….. •°○.......................
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ  @melke1211_bot 
sʜᴀʀᴇ  sʜᴀʀᴇ   sʜᴀʀᴇ                          
           ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion
@christ_mossion
1.2K viewsKingdom Family, 13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 21:35:49 #የሮሜ_መልእክት_ጥናት


የቀጠለ...


26-27 እዚህ ላይ ጳውሎስ የሚናገረው ስለ ገብረ ሰዶማዊነት ነው። ሴቶች ከሌሎች ሴቶች ጋር፥ ወንዶችም ከሌሎች ወንዶች ጋር በግብረ ሥጋ ለመገናኘት ሲፈልጉ ይህ ኃጢአት መሆኑን ጳውሎስ ያስተምራል። ይህ ያልተለመደና ለተፈጥሮዋችን ያልተገባ እግዚአብሔር ለወንዶችና ለሴቶች ካቀደላቸው ነገር ጋር ተቃራኒ ነው። ይህን የመሰለ የፍትወተ ሥጋ ጠንካራ ፍላጎት ለማርካት ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሰዎች መካከል ያልተለመደ ተግባር ለመፈጸም መሞከር እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው። ወንዶች ከሌሎች ወንዶች ጋር ይህን አስጸያፊ ተግባር ቢፈጽሙ በጣም ክፉ የሆኑና ለሞትም የሚያደርሱ እንደ ኤድስ ባሉ በሽታዎች ለመጠቃት ራሳቸውን ያጋልጣሉ (በእርግጥ የሴሰኝነት ጠባይ ያለውም ሰው ቢሆን በእነዚህ በሽታዎች መለከፉ የማይቀር ነው)። እነዚህ በሽታዎች ላልተለመደ ተግባራቸው ተገቢ ቅጣት ናቸው (ቁ. 27)።

28 የሰው የመጀመሪያ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይልቅ የተፈጠሩ ነገሮችን ማምለኩና እነርሱን ማገልገሉ እንደሆነ እናስታውስ! (ቁ. 25)። እግዚአብሔርን በማወቅ መጽናት የሚገባ ነገር ስላልመሰላቸው፥ እግዚአብሔር «አሳልፎ ሰጣቸው»። በተለያየ የሥጋ ኃጢአትም ወደቁ (ቁ. 26–27)። አሁን ደግሞ በቁ. 28 ላይ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ «አሳልፎ ሰጣቸው» ይላል አእምሮ በሰው ዘንድ የክፋት ሁሉ ምንጭ ሲሆን፤ ክፉ አሳባችንና ክፉ ምኞታችን የሚፈልቀው ከዚሁ ከአእምሮ ነው። ስለዚህ የማንም ሰው አእምሮ የማይረባ ሲሆን አሳቡም ሆነ ምኞቱ የማይረባ ይሆናል፤ እንግዲህ ሰው ከዚህ የባሰ አስከፊ ሊሆን አይችልም።

እግዚአብሔር ሰውን ክፉ እንዲያደርግ ጨርሶ አያነሳሳውም። ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን በሚክድበት ጊዜና ጣዖታትንም ማምለክ ሲጀምር፥ እግዚአብሔር የፈቀደውን እንዲያደርግ ይተወዋል። ሰው፣ እግዚአብሔርን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ነፃነት አለው። ይህንንም ነፃነት ለሰው የሰጠው እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን ሰው እያወቀ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ሲክድ ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ ምንም መንገድ የለውም። ያ የእግዚአብሔርን ጸጋና ምሕረት ከሚያገኝበት መንገድ ወጥቶአል።

29–31 ጳውሎስ እዚህ ላይ የተለያዩ ኃጢአቶችን በምሳሌነት አቅርቦልናል። እነዚህን ኃጢአቶች በሌላው ሰው ሕይወት ማየት ቀላል ነው፤ ነገር ግን በራሳችን ሕይወት ለይተን ማወቅ ያስቸግረናል። ራሳችንን ጠማማና ክፉ አድረገን ማየት አይሆንልንም። ነገር ግን ራሳችንን በሚገባ ብንመረምር እነዚህንና እነርሱን የሚመስሉ ኃጢአቶች እናገኛለን። ስስት? ምቀኝነት? ማታለል? እኛ አናማምን? አንሳደብምን? እብሪተኞች አይደለንምን? ትምክሕተኞች አይደለንምን? በነፍሰ ገዳይነት የተሞላን አይደለንምን? በጭራሽ! ነፍስስ አልገደልኩም! በማለት ራሳችንን ነፃ ለማውጣት እንጥር ይሆናል። ነገር ግን እስቲ እንደገና ተመልከቱ ኢየሱስ ወንድማችንን ብንቆጣ የገደልነው ያህል ይቆጠራል ብሎናል (ማቴ. 5፥21-22)። በየጊዜው ወንድማችንን አንቆጣምን? እኅታችንንስ?

ስለዚህ ራሳችንን እንመርምር! እነዚህ የኃጢአት ሥራዎች እኛ «ክፉ» ብለን በምንጠራቸው ሰዎች ላይ ብቻ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኃጢአቶች በእኛም ውስጥ ይገኛሉ፤ ከእነዚህ ኃጢአቶች ሊያጥበንና ሊያነጻን የሚችል ስለ እኛ በመስቀል ላይ የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ብቻ ነው።

32 በሮሜ 6፥23 ላይ ጳውሎስ «የኃጢአት ዋጋ ሞት ነው” ብሎአል። ኃጢአት በአንድ በኩል የሥራ ዓይነት ነው። ይህ ሥራ ለሰይጣን የምንሠራው ሥራ ሲሆን፤ ሰይጣን ደግሞ ለዚያ ሥራ ደመወዝ ይሰጠናል፤ ያም ደመወዝ ሞት ነው! ሰዎች ግን ይህን እንኳ ቢያውቁም ኃጢአት መሥራታቸውን ይቀጥላሉ። እስቲ እነዚህን ሁለት ትንንሽ ምሳሌዎች እንመልከት፥ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣትና ሲጋራን ማጤስ። እነዚህን ነገሮች ማድረግ ሰውነትን ይጎዳል፤ ወደ ሞት ሊያደርስ ወደሚችል ሕመምም ይመራሉ። ሰዎች ግን ይህንንም እያወቁ ማጤስና መጠጣታቸውን ይቀጥላሉ፤ በእርግጥም ለዚህ የኃጢአት ሥራቸው ደመወዝ ይቀበላሉ።

እነዚህን ኃጢአቶች መለማመድ በጣም አስከፊ ነው። እነዚህን ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትን ሰዎች ማበረታታት በጣም የከፋ ነው። ምክንያቱም ሰው በራሱ ሳያውቀውና ሳይረዳው በኃጢአት ሊወድቅ ይችላል፤ ሌላው የሚሠራውን ኃጢአት ሲያበረታታ ግን ሁልጊዜ ይህን የሚያደርገው እያወቀና በማስተዋል ነው። ይህን የሚያደርግ ሰው ግን በእርግጥም የጠፋ ነው።


ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፣ ገጽ 346-347


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
         
1.5K views✞Natneal, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 20:44:24 #የሮሜ_መልእክት_ጥናት

የእግዚአብሔር ቁጣ በሰው ዘር ላይ (1፥18–32)



18 የእግዚአብሔር ጽድቅ በክርስቶስ ወንጌል እንደተገለጠ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ቁጣም በአምላክ የለሾችና በክፉዎች ሁሉ ላይ ተገልጦአል። የመጀመሪያውና ታላቁ ኃጢአት አምላክ የለሽነት ሲሆን፤ ይህም አንዱን አምላክ ለማወቅና ለማምለክ አለመፈለግ ነው። አምላክ የለሽነት በእግዚአብሔር ፈንታ ለሰው የመጀመሪያውን ቦታ መስጠት፥ በሰው መታመንና በእግዚአብሔር ከመደገፍ ይልቅ በራስ መታመን ነው። የሰው ኃጢአትና ርኩሰት ሁሉ የሚመነጨው ከዚሁ ከአምላክ የለሽነት ሲሆን ይህም በእግዚአብሔር ለመታመን እምቢ ማለት ነው (ቁ. 29–3)።

18–20 የእግዚአብሔር የማይታዩ ባሕርያት ማለትም ዘላለማዊ ኃይሉና አምላክነቱ፥ እርሱ በፈጠራቸው ነገሮች ግልጥ ሆነው ታይተዋል። ሰዎች ሁሉ እነዚህን የእግዚአብሔርን ባሕርያት ማየት ይችላሉ። በገዛ ዓይኖቻቸው ተራራዎችንና ከዋክብትን ማየት ይችላሉ፤ ታዲያ እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠረ ማን ነው? እግዚአብሔር ሳይኖር እነዚህ ሁሉ ነገሮች እንዴት ሊፈጠሩ ቻሉ? እነዚህን ሁሉ ነገሮች ማድረግ የቻለ እግዚአብሔር ብቻ ነው (መዝ. 19፥14)። ይሁን እንጂ፥ ሰዎች በክፋታቸው እውነትን አንቀው ይዘዋል፤ (ቁ. 18)፤ የእግዚአብሔርንም መኖር ክደዋል ከዚህም የተነሣ ሰዎች የሚያመካኙት የላቸውም (ቁ. 20)።

21 ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን እያወቁት ሊቀበሉት ባይፈቅዱና፣ እግዚአብሔርን ቢክዱም፤ በተፈጥሮአቸው ግን እርሱ እንዳለ ያውቃሉ። ሰዎች ሁሉ ፍጥረት ካለ፣ ፈጣሪም እንዳለ ያውቃሉ፤ ነገር ግን ይህን ዕውቀት አንቀው ይዘውታል። የሰዎች ልብ ጠጥሮአል፣ ማስተዋላቸውም ጨልሞአል። (ኤፌ. 4፥17-18)። ብዙጊዜ ሰዎች የፈለጉትን ማድረግ እንዲችሉ እግዚአብሔርን መካድ ይመርጣሉ።

22–23 ስለዚህ እግዚአብሔርን በማምለክ ፈንታ፥ ሰዎች ጣዖትን ያመልካሉ ፈጣሪን በማምለክ ፈንታ የተፈጠሩትን ያመልካሉ። እንዲያውም አንዳንዶቹ ድንጋይን ያመልካሉ። እንግዲህ የዓለም ጥበብ ማለት ይህ ነው? እንዲህም ሆኖ የዓለም ሰዎች ራሳቸውን ጠቢባን አድርገው ይመለከታሉ፡ የክርስቶስንም ወንጌል «ሞኝነት ነው» ይላሉ። ጳውሎስ፣ ለቆሮንቶስ ሰዎች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸዋል፥ "የመስቀሉ ቃልና የክርስቶስ ወንጌል ለሚጠፉት እንደ ሞኝነት ነው፤ ለምንድነው ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው።" (1ቆሮ. 1:18-21 )፡፡

24 ስለዚህ እነዚህን አምላክ የለሽ የሆኑ ሰዎች እግዚአብሔር ምን አደረገባቸው? አሳልፎ ሰጣቸው። በሌላ አነጋገር ብቻቸውን ሆነው በኃጢአታቸው እንዲቆዩ ተዋቸው (ኤፌ. 4፥19)። እግዚአብሔር በልባቸው ሞልቶ የነበረውን የሞኞች ኃጢአት እንዲፈጽሙ ተዋቸው።

ጳውሎስ ሦስት ጊዜ አሳልፎ ሰጣቸው ብሎ ይጽፋል (ቁ. 24፥ 26፥ 28) ከራሳችን የሕይወት ልምድ እንደምናውቀው ትንንሽ ኃጢአቶች ወደ ትልልቅ ኃጢአቶች ይለወጣሉ፤ ወዲያውም በከፍተኛ ፍጥነት ትልቅ እየሆኑ ያድጋሉ። ኃጢአት በሠራን ቁጥር ከእግዚአብሔር እየራቅን እንሄዳለን፤ በኃጢአትም ምክንያት ከእግዚአብሔር የምንርቅም ከሆነ፥ እርሱም ከእኛ እየራቀ ይሄዳል። ይህም «አሳልፎ ይሰጠናል» ማለት ነው። ኃጢአታችንን ተናዝዘን ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብ ከሆነ ግን እርሱም ወደ እኛ ይቀርባል (ያዕ. 4፥8)።

25 የአምላክ የለሾች ዋና ኃጢአት ጣዖት ማምለክ ነው። ጣዖት ማምለክ ማለት ከፈጣሪው ይልቅ ፍጡሮችን ማምለክ ማለት ነው። ጣዖት ማምለክ ማለት ሐሰተኛ አምላክን ወይም ጋኔን ማምለክ ማለት ነው (1ቆሮ. 10፥19-20)። ጣዖት ማምለክ በእውነተኛው አምላክ ላይ የሚፈጸም ከፍተኛ ኃጢአት ሲሆን በብሉይ ኪዳን ከዐሥሩ ትእዛዛት ሁለቱ ስለ ጣዖት አምልኮ የሚናገሩ ናቸው፥ "ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ · · · የማንኛውንም ዓይነት ምስል ጣዖት አድርገህ አትሥራ" (ዘጸ. 20፥3-6)።

ጣዖት ከብረት፥ ወይም ከድንጋይ ወይም ከእንጨት ተቀርጾ የሚሠራ ነገር ብቻ አይደለም። ጣዖት ማለት ከእግዚአብሔር ይበልጥ የምንወደው ማናቸውም ነገር ነው። ገንዘብ፥ ንብረት፥ ዝና ኀይል፥ ክብር፥ ወይም ቤተሰብን ቢሆን ከእግዚአብሔር አብልጠን የምንወድ ከሆነ ጣዖት በማምለክ በደለኞች ሆነናል ማለት ነው። እነዚህ ነገሮች በራሳቸው መልካም ቢሆኑም ለእኛ ግን ጣዖት ሆነዋል ማለት ነው። ምን ይህ ብቻ እግዚአብሔርን አለመስማት እራሱ ጣዖት ነው!

"ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።"
(1ኛ ሳሙኤል 15፥25-23)



ይቀጥላል...

ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፣ ገፅ 346

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
1.9K views✞Natneal, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 19:38:28 #የሮሜ_መልእክት_ጥናት


1፥18 የእግዚአብሔር ቊጣ፤

የእግዚአብሔር ቊጣ (በግሪኩ ኦርጌ) የጽድቁና የፍቅሩ መግለጫ ነው:: በሰዎች ክፉ ባሕርይ (ዘፀ 4፥14፤ ዘኊ 12፥ 1 -9 ፤ 2ሳሙ 6፥6-7)፣ በአገሮች ጠማማ አካሄድ (ኢሳ 10፥5፡ 13፥3፣ ኤር 50፡13፤ ሕዝ 30፥15) እና በአግዚአብሔር ሕዝብ ታማኝ አለመሆን (ዘኊ 25፥3፣ 32፥10-13፡ ዘዳ 29፥24-28) የሚነሣሣ የእግዚኣብሔር የግሉ ቊጣና በኀጢአት ላይ የሚሰጥ የማይቀር ፍርድ ነው (ሕዝ 7፥8-9፤ ኤፌ 5፥6፡ … ራእ 19፥15)፡፡

1.  በቀደሙት ዘመናት የእግዚአብሔር ቊጣ የተገለጠው በጐርፍ (ዘፍ 6—8)፣ በራብና በቸነፈር (ሕዝ6፥11)፣ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ (ዘዳ 29፥22-23)፣ በመበተን (ሰቆ. ኤር 4፥16) እና በምድር ቃጠሎ (ኢሳ 9፥18-19) ነበር፡፡

2. በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የእግዚአብሔር ቁጣ በደለኛውን ንጹሕ ላልሆነና ለነውረኛ ፍትወት አሳልፎ በመስጠት (ቊ 24)እንዲሁም በማይታዘዙት ላይ ጥፋትንና ሞትን በማምጣት (1፡18-3፥20፣ 6፥23፤ ሕዝ 18፥4፤ ኤፌ 2፥3) ተገልጧል፡፡

3.  በሚመጣው ዘመን የእግዚኣብሔር ቍጣ በዚህ ዓለም ኀጢአተኞች ላይ የሚወርደውን ታላቅ መከራ(ማቴ 24፥21፤ ራእ 5፥19) እንዲሁም በሰዎችና በመንግሥታት ሁሉ ላይ የሚመጣን የፍርድ ቀን (ሕዝ 7፥19፤ ዳን 8፥19) ያካትታል፤ ይህም "የሁከትና የጥፋት ቀን፣ የጨለማና የጭጋግ ቀን" (ሶፎ 1፥15) እንዲሁም ኃጢአተኞች የሚቀጡበት ቀን (2፥5፣ ማቴ 3፥7፣ ሉቃ 3፥17፣ ኤፌ. 5፥6፤ ቈላ 3፥6፤ ራእ 11፥18፤ 14፥8-10፤ 19፥15) ይሆናል። በመጨረሻም የእግዚአብሔር ቍጣ ያልገቡት ለዘላለም እንዲቃጠሉ ያደርጋል (ማቴ 10፥28)።

4.  የእግዚአብሔር ቊጣ በሰው ልጆች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አይደለም፤ እግዚአብሔር ማምለጫውን መንገድ አዘጋጅቷልና፡፡ አንድ ሰው ከኀጢአቱ ንስሓ ገብቶ በእምነት ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ሊቀርብ ይችላል።

5. ከክርስቶስ ጋር የሆኑ አማኞች በበቀል ሳይሆን በእውነት ጽድቅን በመውደድና ክፋትን በመጥላት ከእግዚአብሔር ቊጣ ጋር ሊተባበሩ ይገባል (ዕብ 1፥9)፡፡ አዲስ ኪዳን እግዚአብሔር የሚጠላውን እንዲጠላ የሚያደርገውን በኢየሱስ ክርስቶስ (ማር 3፡5፤ ዮሐ 2፥12-17፤ ዕብ 1፥9፤ ሉቃ 19፥45)። በጳውሎስ (ሐ 17፥16) እና በሌሎች ጻድቃን ሰዎች (2ጴጥ 3፥7-8፤ ራእ 2፥6) የተገለጠውን ቊጣ ይደግፋል።


ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፣ ገጽ 1734-1738

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
         
2.1K views✞Natneal, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ