Get Mystery Box with random crypto!

🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ🗣

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_mossion — 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ🗣
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_mossion — 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ🗣
የሰርጥ አድራሻ: @christ_mossion
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.93K
የሰርጥ መግለጫ

ዮሐንስ1፥5 ብርሀንም በጨለማ ይበራል፥ጨለማም አላሸነፈውም
ይህ channel እግ/ርን የምናመልክበት አብረን ተያይዘን
ተደጋግፈን ይህን ዘመን የምናልፍበት ወንጌልን ላልሰሙት የምስራጅ የምናበስርበት channel ነው።

ሀሳብ/አሰተያየት; @Gospel_Worldbot
ዝማሬዎች በየቀኑ ማግኘት ከፈለጉ👇👇
@Enamelkw_tube

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-07-03 09:22:44 ኢየሱስ ነብሴ #ተራበችህ
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
አገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ!
አሁን ላይ ሰዎች ብዙ የሚናፍቁት ነገር ሊኖር ይችላል የኔ ርሀብ እና ናፍቆት ግን ይህ ነው!
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
Holy Tube Ethiopia
............……….. •°○.......................
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot
sʜᴀʀᴇ  sʜᴀʀᴇ   sʜᴀʀᴇ
ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion @christ_mossion
4.8K viewsKingdom Family, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 08:04:18 . #የማለዳ_ጥቅስ

(መጽሐፈ መክብብ ምዕ. 12)
----------
1፤ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤

2፤ ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፤

3፤ ቤት ጠባቆች በሚንቀጠቀጡበት፥ ኃያላን ሰዎችም በሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች ሆነዋልና ፈጭታዎች ሥራ በሚፈቱበት፥ በመስኮትም ሆነው የሚመለከቱ በሚጨልሙበት፥ በአደባባይም ደጆቹ በሚዘጉበት ቀን፤

4፤ የወፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከወፍ ድምፅ የተነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፤

5፤ ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፤ ሰው ወደ ዘላለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤

6፤ የብር ድሪ ሳይበጠስ፥ የወርቅም ኵስኵስት ሳይሰበር፥ ማድጋውም በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፥ መንኰራኵሩም በጕድጓድ ላይ ሳይሰበር፥

7፤ አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።

#ሰናይ_ቀን

SHARE SHARE SHARE
JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
4.4K viewsnatnael , 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 19:55:02 የእግዚአብሔር የሆነ ነገር ሁሉ አይቅለልባችሁ የእርሱ የሆነውን የሚያቀልባችሁን ማንኛውንም ምክንያት አስወግዱት።

የእግዚአብሔር ነገር አክብዶ የቀለለ የለም።የእግዚአብሔር የሆነውን አቅልሎ የከበረ የለም።ዋናው ነገር ዋናውን ነገር ዋና ማድርግ ነውና ዋናውን ሊያቀልባችሁ የተነሳው ተራ አጀንዳ በመተው እግዚአብሔር መጀመሪያ ያለውን አንሡ።

የእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ ዋጋ መስጠት የሚጀምረው ከvalue system ነው።ማንም ሰው ለእግዚአብሔር ነገር ያለው value system እንድ እግዚአብሔር ሃሳብ ወይም እንድ እግዚአብሔር ቃል አቆጣጠር እስካልሆነ ድረስ መቼም የእግዚአብሔር ነገር በእርሱ ዘንድ አያከብርም።

የእግዚአብሔር ጉዳይ በእግዚአብሔር እውነት ይተረጎማል እንጂ በእኛ መረዳት አይብራራም።

Ⓒየእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
4.0K viewsnatnael , 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 08:21:18 . ታውቀኛለህ!
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
ይድረስ ለአማኞች ሁሉ!
ሊሰሙት የሚገባ ድንቅ መልዕክት!
በአገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ !!
መንፈሳዊ ህይወታችሁ የደከመበት ምክንያት ይሄ ነው! #ስሙት!
የልቤ የሚገባው በምድር ላይ ባላገኝም አንተ ግን ታውቀኛለህ!
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
Holy Tube Ethiopia
........................…………………………
#ራስዎን_በቤት_ይገንቡ
............ •°○..........................
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot
ሼር ይደረግ #Share #Share
ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion @christ_mossion
3.9K viewsKingdom Family, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 19:43:37 በውስጣችሁ የሚነደውን እሳት መጠበቅ!!!

በውስጡ የጠፋበት ሰው በውጩ ይጠፍበታል!በእግዚአብሔር መንግስት እጀግ በጣም ልትጠነቀቁለትና ልትጠብቁት ከሚገባ ነገር መካከል በውስጣችሁ ያለውን ግለት ወይም እሳት ነው።

እሳቱ ሲጠፍባችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ፍቅር እንዲሁም የአምልኮና የምስጋና ህይወታችሁ ይደበዝዛል።

እግዚአብሔር የሚሰጣችሁ ትልቅ የሚሆን ትንሽ እሳት ነው።ትንሿን እሳት ትልቅ ማድረግ የእናንተ ሃላፊነት ነው።እግዚአብሔር የሰጣችሁ እሳት በእናንተ ይወሰናል።ትንሿን እሳት ትልቅ እሳት ማድረግ የእናንተ ውሳኔ ነው።ማዳፈንም የእናንተው ጉዳይ ነው።ግን እርግጠኛ ሁኑ ትልቅ የሚሆን ትንሽ እሳት አሁን አላችሁ።

በውስጣችሁ ያለውን እሳት መጠበቂያዎች

1.እንጨት መጨመር

እንጨት የማይጨመርበት እሳት ከሰአታት በኋላ ይጠፍል የእግዚአብሔር ቃል የማይጨመርበት መንፈስ ከጊዜ በኋላ ይጠፍል።በውስጣችሁ ያለውን መንፈሳዊ ግለት የሚያስጠብቀውና ይበልጥ እንዲነድ የሚያደርገው የእግዚአብሔር ቃል ነው።ይህን የእግዚአብሔር ቃል ተመልከቱ፦

ዘሌዋውያን 6
¹² እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፥ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥልበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል።
¹³ ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም።

ቁጥር 13*ላይ እሳቱ በመሰዊያው ላይ ዘወትር እንደሚነድና እንደማይጠፍ ይናገራል ዘውትር እንዲነድና እንዳይጠፋ የሆነው የማይጠፍ ስለሆነ ሳይሆን ካህኑ ዕለት ዕለት በማለዳ እንጨት ይጨምርበት ስለነበረ ነው።

አንተም የእግዚአብሔርን ቃል በመንፈስ ላይ የማትጨምር ከሆነ እርግጠኛ ሁን መንፈስ ይጠፍል መንፈሳዊ ድርቀት ውሰጥ ትገባለህ።

2.ነዳጅን መጨመር

በውስጣችሁ ያለው መለኮታዊ እሳት እንዲነድ መንፈሳዊ ነዳጅ ያስፈልገዋል።እንጨቱ በሚገባ እንዲነድና እንዲቀጣጠል ነዳጅ ሊያረሰርሰው ይገባል።የእግዚአብሔር ቃል ያለ እግዚአብሔር መንፈስ አይሰራም።ፊደል ይሆንና ይገላል።

የማይነድ ብዙ እንጨት ያላቸው ሰዎች አውቃለሁ ግን አይነድም።አያሞቃቸውም ደግሞ አያበስልላቸውም።የማይነድ እንጨት ከመሰብሰብ አለመሰብሰብ ይሻላል።የእግዚአብሔርን ቃል በእናንተ ዘንድ ሰራተኛ የሚያደርገው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።ቃሉ እንዲሰራ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ።

“ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤”
— ሮሜ 12፥11

3.ጓደኛ ምረጥ

በውሳጣችሁ ያለውን መለኮታዊ ግለት ጓደኛ ያነደዋል ወይም ጓደኛ ያጠፋዋል።እንዳታመናፍሰው በጓደኛህና በውሎህ ልክ ትወሰናለህ።

ሰይጣን በቀጥታ ከመታባችሁ መንፈሳዊ ህይወት ይልቅ ሰይጣን ጓደኝነት በሚመስል የመታባችሁ መንፈሳዊ ነገር ይበልጣል።በእግዚአብሔር ነገር የተጠመደ ለእግዚአብሔር ነገር የነቃ ጓደኛ እስከሌላችሁ ድርስ በፍጹም ውስጣችሁ ያለው ግለት አይቀጥልም።ጓደኛህን ምረጥ።

“ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።ምሳሌ 27፥17

Ⓒየእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
4.5K viewsnatnael , 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 22:03:36 . የመንፈስ ቅዱስ ረሀብ!
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
በአገልጋይ #መልካሙ #ሙልጌታ
--------------------------------------------------
ይሰማ #በትውልዱ ልብ ውስጥ #የመንፈስ ቅዱስ #ረሀብ ገባ

አንተ #ትውልድ ስማኝ ወይ #ትነቃለህ ወይ ደግሞ #ምስኪን ሆነህ ታልፋለህ #ምርጫው ያንተ ነው

ጴንጤ ሆኖ ሳይሆን ኢየሱስን ገልጦ ማለፍ የሚፈልግ ብቻ ይስማው!
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
Holy Tube Ethiopia
........................…………………………

#ራስዎን_በቤት_ይገንቡ
............ •°○..........................
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot
sʜᴀʀᴇ  sʜᴀʀᴇ   sʜᴀʀᴇ
ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion @christ_mossion
4.4K viewsKingdom Family, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 17:51:03 #የደሀ እንባ ወደታች አይፈስም
ወደ ላይ እንጂ ወደ ፈጣሪ ነው እሚረጨው::

ያ እንባ ተጠራቅሞ ዝናብ ሆኖ የወረደ ቀን ትጥቅህም ፎቅህም ገንዘብህም አያድንህም::

share @Christ_mossion
3.8K viewsnatnael , 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 08:22:00 . ባለ እዳ ነኝ
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
ይድረስ ለአማኞች ሁሉ!
መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስን የፍቅሩን ልክ እባክህ ለነብሴ አብራላት
ድንቅ የፀሎት ጊዜ
ከአገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ ጋር
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
Holy Tube Ethiopia
........................…………………………
#ራስዎን_በቤት_ይገንቡ
............ •°○..........................
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot
ሼር ይደረግ #Share #Share
ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion @christ_mossion
5.2K viewsKingdom Family, 05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 15:34:17 . ልስከር በህልውናህ
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
ልሰወር በህልውና ውስጥ ራሴን #እስክስት ኢየሱሴ
አባ ህይወት ኑሮ #ይቅርብኝ ነውና #ክስረት አንተ ከሌለህበት!
………………………………………………………
በ youtube ቻናሌም ቤተሰብ በመሆን አገልግሎቴን በስፋት ይከፋፈሉ
https://www.youtube.com/channel/UC7n0Mo4O54Dj66zdQafnilQ
Holy Tube Ethiopia
........................…………………………
#ራስዎን_በቤት_ይገንቡ
............ •°○..........................
አስተያየት ካላችሁ በዚ አናግሩኝ @melke1211_bot
ሼር ይደረግ #Share #Share
ቻናሉን ይቀላቀሉ
@christ_mossion @christ_mossion
5.4K viewsKingdom Family, 12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 19:14:06 እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ትክክለኛው መረዳት ለማምጣት የሚጠቀምበት መንገድ መጠየቅ ይባላል።እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ እርሱ መረዳት ማምጣት ሲፈልግ ጥያቄ ይጠይቃል።

"ሰው ሊያውቃችሁ ይጠይቃል እግዚአብሔር ስለሚያውቃችሁ ይጠይቃል።ሰው ሊፈትናችሁ ይጠይቃል እግዚአብሔር ሊያሳውቃችሁ ይጠይቃል።"

"ሰይጣን የሚጠይቃችሁ ሊጥላችሁ ነው።እግዚአብሔር የሚጠይቃችሁ እንደገና ሊያነሳችሁ ነው።"

Ⓒየእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion
4.9K viewsnatnael , 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ