Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media

የቴሌግራም ቻናል አርማ bete_amharamedia — ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media
የቴሌግራም ቻናል አርማ bete_amharamedia — ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media
የሰርጥ አድራሻ: @bete_amharamedia
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.03K
የሰርጥ መግለጫ

በሀገራችን ኢትዮጵያ በፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እንድሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥ ምርጥ የቴሌግራም ቻናል።
Offical Group @BeteamhramediaGroup
Telegram፦ https://t.me/Bete_amharamedia
Facebook፦ https://www.facebook.com/beteamharamediaa/

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 13:48:45 ስለቆቦ ከተማ!

“እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የቆቦ ከተማና አካባቢው እስከ አሁኗ ስአት ድረስ በጠላት ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው። አንዳንድ ወገኖችና የማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች የወገን ጦር ቆቦ ገብቷል በማለት የሚሰጡት መረጃ ትክክል አይደለም። ይህም ሆኖ የወገን ጦር በቆቦና አካባቢው እየወሰደው ባለው የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ አማካኝነት ቆቦ ከተማ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነጻ ሊወጣ እንደሚችል ይታመናል።”

- ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ እንደገለፀው!


ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
872 views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:46:18 ያማልም ያሳዝናልም


“በቆቦ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንፁኃን በሕወሓት ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ!

በቆቦ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንፁኃን በሕወሓት ታጣቂዎች መገደላቸውን በስፍራው የሚገኙ ምንጮች ገልፀዋል። እስካሁን የሟቾቹን አስከሬን ማንሳት እንዳልተቻለም የአይን እማኞቻችን አረጋግጠዋል።ቆቦ ከተማ እስካሁን በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ስትሆን ነዋሪዎቿ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ለአማራ ድምፅ አረጋግጠዋል። ታጣቂዎች ቤት ለቤት እየዞሩ በርካታ ንጹኃንን ፋኖ እና ሚሊሻ ናችሁ በሚል ጎዳና ላይ አውጥተው እንደረሸኗቸው የአይን እማኞቹ አረጋግጠዋል።”

- ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እንደገለፀው



ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
814 views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:43:33 ነገሩ የተበላሸው ወራ*ሪው ተኩለሽን ሲቆጣጠረው ነው፤ ተኩለሽ ላሊበላን እና ወልድያን ለመያዝ ቁልፍ የሆነ ስትራቴጂካዊ ቦታ ነው!! እና ሁለቱም ከተሞች የመያዝ እድላቸው ሰፊ ነው፤ የእነዚህ ቦታዎች መያዝ ግን የጦርነቱ ፍፃሜ አይደለም! አዲስ አበባ እንኳን ቢገባ እኛ የሀይል አሰላለፋችን ቀይረን መዋጋት ከቻልን ድሉ የኛ ነው የሚሆነው!!
ድል የሚፈልግ አማራ ሁሉ አሰላለፉን አስተካክሎ፣ አላማውን ለይቶ፣ በፅናት ይታገል!
#ድል ለአማራ!


Veronica Melaku

ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
813 viewsedited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:11:23 Update
News

አሁን ግንባር ላይ የደረሰኝ መረጃ ነው።ጎብየ ዙሪያውን ከፍተኛ ውጊያ አለ።የጠላት ጦር ከባለፈው ሀይል በቁጥር ከፍተኛ ህዝባዊ ሀይል ይዞ የተሰለፈበት ስለሆነ ለወገን ጦር እጅግ አስቸጋሪ ሆኗል።አሁንም ቢሆን ጠላትን ማሸንፍ እምንችልበት እድሉ እጃችን ላይ አለ።አማራም እንደ ትግሬ ህዝብ ማእበል ሆኖ ጠላትን ማሸነፍ ካልቻልን ባለፈው ከተከፈለው መስዋዕትነት በላይ መስዋእትነት እዳይኖር እሰጋለን።

መልእክቱን አድርስልኝ


ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
913 viewsedited  10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:49:50
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ በድሬዳዋ ጀመረ።
******
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ  በዛሬው ዕለት ተከታታይ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ በድሬዳዋ  ከተማ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ፥ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ሂደት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ÷ ደንበኞች በ07 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል፡

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶች የድርጅቱ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚችሉ እና ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሑፍ መልዕክቶች ጥቅል ያገኛሉም ተብሏል፡፡

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን በቀጣይነት መጠቀም እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ፥ ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሑፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ መገለጹን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
956 views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:08:58
ሰበር መረጃ ወለጋ አጋምሳ ሐሮ !
/
ህግ ለማስከበር በሚል ወለጋ የገባው የመከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ልዩሀይል አካባቢውን ለቆ ወደ ነቀምት ሄዷል። ይሄን ተከትሎ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ኦነግ እና ከብርሸለቆ ማሰልጠኛ መሳሪያ ዘርፎ ኦነግን የተቀላቀለው ኃይል በወለጋ አማራ ላይ ዳግም ጦርነት ከፍቷል።

ከትናንት ጀምሮ ወለጋ አጋምሳ እና ሐሮ የሚባል ቦታ የሚገኙ አማራዎችን ከበባ በማድረግ ለመ*ጨ*ፍ*ጨ*ፍ ሙከራ ቢያደርጉም ህዝቡ ራሱን በመከላከል ከመካከላቸው በወጡ ጀግኖች ከበባውን ሰብረው ህዝባቸውን ማውጣት ችለዋል።

በሌላ መኩል ከህወሓት የተማሩትን ሕዝባዊ ማዕበል በማስነሳት ነፍጠኛን እንወራለን በማለት ቅስቀሳ እየተደረገ እንደሆነ ከቦታው መረጃ እየወጣ ነው። በአሁኑ ሰዓትም በኦነግ ሸኔ እና በወለጋ አማራዎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው።

ምንጭ፦ጥላሁን አበጀ


ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
1.1K viewsedited  08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:08:05
የወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ ነው።
ከወራሪው ቡድን ጋር የሚደረገው የጥምር ጦሩ ፍልሚያ አሁንም በሕዝባዊ ደጀንነት ታጅቦ እንደቀጠለ ነው።  የወልድያ፣ የሐብሩ እና የሌሎችም ወረዳዎች ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ ሁሉ ጥምር ጦሩ ጋር ለመቀላቀል ወደ ግንባር እየዘመተ ነው።
በወልድያ ከተማም ከጅቡቲ ወደብ  የሚነሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችንም ከተለመደው ጉዟቸው ያስተጓጎላቸው ሁኔታ አልተከሰተም።


መረጃው የወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው



ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
1.0K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:06:10
የጀመርነዉን ትግል ህዝባችንን ይዘን ለድል እናበቃዋለን።

  በህግ ማስከበር ስም በመንግስት ሲሳደድ የኖረዉን የአማራ ወጣት ከየ አካባቢው በማሰባሰብ የሰው ሃይል አቅማችንን እያጠናከርን ነው። አሁንም ሁሌም ከጎናችን ያልተለየዉን ህዝባችንን ይዘን ድል እናደርጋለን።

ሁሉም የአማራ ወጣት የአማራ ፋኖ ለማይቀረው የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ግንባር እንዲከትና እንዲዘምት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

* ማስታወሻ፡  የአማራ ወጣት ሆይ ነጻነትህን ከማንም አትጠብቅ! ነጻነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም። የአማራ ወጣት ሆይ የትም ብትሄድ የትም ብትሆን ሞት ተደግሶልሃልና ገዳይህን እየገደልክ ሙት። ያኔ ሞትህ ሞት አይሆንም መስዋዕትነት እንጂ! መስዋዕትነት ደግሞ ነጻ ያወጣሃል። ያኔ አባቶችህ በሰሯት አገር ህልውናህ ተጠብቆና ተረጋግጦ ፍትህ እኩልነትና ነጻነት ሰፍኖልህ በሰላም ትኖራለህ።

የአማራ ፋኖ መልእክት ከግንባር


ከግንባር መረጃዎችን የሚያደርሰውን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ:-

https://t.me/Bete_amharamedia
936 views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ