2022-05-07 13:38:47
የፌዴራል ጠበቆች ምዝገባ - መራዘሙን ስለማሳወቅ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር በአባልነት ላቀፋቸው ጠበቆች አስፈላጊውን አገልግሎት በመስጠት ኃላፊነት እና ግዴታውን ለመወጣት ይችል ዘንድ እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ
1. በድህረ-ገጽ በኦንላይን በዚህ አድራሻ http://t.ly/RzWs ወይም
2. በፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት ወይም በአራዳ ምድብ ችሎት በሚገኘው የማኀበሩ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት
እንድትመዘገቡ መጠየቁ ይታወሳል።
በዚህ መሠረት በርካታ ጠበቆች በኦንላይን እና በአካል በመገኘት ምዝገባቸውን አከናውነዋል።
ምዝገባው እንዲከናወን የታሰበበት ጊዜ የበዓል ቀናት የተበራከቱበት መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለመመዝገብ ያልቻሉ ጠበቆች ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ተጨማሪ ቀን መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ማኅበሩ አምኗል።
በዚህ መሠረት ያልተመዘገባችሁ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች በሙሉ የምዝገባ ጊዜው
ከሰኞ ከግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ማኅበሩ ያሳስባል።
በኦንላይን ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ http://t.ly/RzWs
በአካል ተገኝተው ለመመዝገብ፦
1. የጥብቅና ደብተርዎን መያዝዎን አይዘንጉ፤
2. የጥብቅና ደብተርዎን የፊት ገጽ እና ፈቃድዎ የታደሰበትን የሚያሳየውን ክፍል ኮፒ አድርገው መያዝዎን አይዘንጉ
3. ለማኅበሩ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ መያዝዎን አይዘንጉ፤
4. የግብር መለያ ቁጥር መያዝዎን አይርሱ፤
የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማኅበር
11.0K viewsLiku Worku, 10:38