2022-02-04 11:57:43
በጽሑፍ የሰፈረን የውል ቃል የምስክርና ሌላ ዓይነት ማስረጃን በማቅረብ ማሻሻል ይቻላል?
Mulugeta Mengist Ayalew (PhD)
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ በመዝገብ ቁጥር 78398 በአቶ ሽፈራዉ ደጀኔ እና ወ/ሮ ጸሀይ ተስፋዬ በአንድ በኩልና በአቶ ሲሳይ አበቡ በሌላ በኩል በተደረገ ሙግት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ጥቅምት 19 2005 የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ፡፡
በመደምደሚያው
1. የፓሮል ሕግ የሚሉትና በተለይ የአንግሎ-አሜሪካን የሕግ ስልትን የሚከተሉ ሀገሮች እዉቅና የሚሰጡት በኢትዮጲያ ሕግ የለም፡፡በኢትዮጲያ የዉል ሕግ መሰረት፤ ሕጉ ወይም ተዋዋይ ወገኖች የተለየ ፎርም ካላስቀመጡ በስተቀር፤ ዉልን በማንኛዉም ፎርም በተደረገ ስምምነት ማሻሻልና መጨመር ይቻላል፡፡ ሕጉ ወይም ተዋዋይ ወገኖች የተለየ ፎርም ካስቀመጡ ግን፤ ዉሉ ሊሻሻል ወይም ሊጨመርበት የሚችለዉ በተመሳሳይ ፎርም በተደረገ ስምምነት ነዉ፡፡
2. የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2005ና 2006 የተቀመጡት ድንጋጌዎች የማስረጃ ድንጋጌዎች በመሆናቸዉ ስራ ላይ የሚዉሉት በsubstantive ሕጉ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በማይሸረሽር መልኩ መሆን አለበት፡፡
3. ሰበር ሰሚ ችሎቱ የቤቱ ባለቤቶች ቤቱን በአርባ ሺ እንዲሸጡ ይገደዳሉ ያለዉ ምንም የሕግ መሰረት የሌለዉ ነዉ፡፡
4. ሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሉ ዋጋ የለዉም ብቻ ሳይሆን በእርግጥ በጽሁፉ እንደተገለጸዉ ሃያ ሺ ብር ተከፍሏል የሚለዉን በተጨማሪ ማስረጃ በመፈተሸ የተከፈለ ብር ካለ እንዲመለስ ማዘዝ ይኖርበታል፤ ወይም ይህን ጠቁሞ ጉዳዮን ለታችኛዉ ፍርድ ቤት መምራት ይገባዉ ነበር፡፡
5. ሰበር ሰሚ ችሎቱ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የ2005ና 2006ን በተመለከተ የማብራሪያ/አሳማኝ ትርጉም (obiter dictum) ሊሰጥ እየቻለ እድሉና አሳልፏል፡፡
https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1560-is-it-possible-to-justify-and-amend-a-written-contract-with-witnesses
14.5K viewsLiku Worku, 08:57