Get Mystery Box with random crypto!

abyssinialaw.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ abyssinialaw — abyssinialaw.com A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abyssinialaw — abyssinialaw.com
የሰርጥ አድራሻ: @abyssinialaw
ምድቦች: ብድር, ግብሮች እና ህጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.20K
የሰርጥ መግለጫ

A complete and easy access to Ethiopian Legal Information!

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-20 13:53:39 ተገዶ የመያዝን ሕጋዊነት ለማጣራት የሚቀርብ ክስ (Habeas corpus) እና የፍትሐብሔር እንድምታው

በ፡ ፋሲካ አበራ

የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ በልዩ ሁኔታ ሥነ-ሥርዓት ካበጀላቸው ክርክሮች መካከል አንዱ ተገዶ የመያዝን ሕጋዊነት ለማጣራት ወይም የአካል ነጻነትን ለማስከበር የሚቀርብ ክርክር አንዱ ነው፡፡ ይህ ሕግ ከቁጥር 177 እስከ 179 ባሉት ድንጋጌዎቹ ክርክሩ የሚመራበትን መሰረታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ዘርግቶ እናገኛለን፡፡ ድንጋጌዎቹ ምንም እንኳ ከሌሎቹ ልዩ ሥነ-ሥርዓት ከተሰራላቸው ጉዳዮች አንጻር ጥቂት ቢሆኑም ይሁን እና በውስጣቸው ትልልቅ ሥነ-ስርዓቶችን ይዘው እናገኛቸዋለን፡፡ በዚህም መሰረት ይህ ክርክር ከመደበኛው የፍትሐብሔር ክርክር የሚለያይባቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ጽሁፉ እንደሚከተለው ተመልክቷቸዋል፡፡

የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋነኛ አላማ አንድ የአካል ነጻነት መብቴ ተገፏል የሚል ሰው ይህ መብቱን ፍ/ቤት እንዲያስከብርለት አቤቱታ ቢያቀርብ ክርክሩ ከመደበኛው የፍትሐብሔር ጉዳዮች ክርክር የሚለይበትን ዋና ዋና የሥነ-ሥርዓት ነጥቦች ለማብራራት ነው፡፡
መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog/habeous-corpus-in-civil-suits-in-ethiopia
1.4K viewsLiku Worku, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 14:17:06 በፍትሐብሔር ክርክር ቅድመ-ሙግት ሂደት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

በ፦ ፍቃዱ አንዳርጌ መኮንን

የዚህ ጽሑፍ ዋና ትኩረት ከሙግት በፊት ያሉ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደቶች አንድን ክርክር ላይ ያላቸዉን ሚና ማጉላት እና ፋይዳቸዉን ማሳየት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ሂደት ቅደመ ሙግት የሚባለዉ ለክርክሩ መሪ ጭብጥ ተይዞ ግራ ቀኙ ማስረጃ ማሰማት ከመጀመራቸዉ በፊት ያለዉ ሂደት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ዋናዉ ሙግት የሚጀምረዉ ጭብጥ ተይዞ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 257 እና ተከታይ ድንጋጌዎቹ ተከራካሪዎች ማስረጃዎቻቸዉ የሚያስረዷቸዉን ጭብጥ እያስመዘገቡ ማስረጃ ማሰማት ሲጀምሩ ነዉ፡፡ ከዋናዉ ሙግት በፊት ባለዉ የቅድመ ሙግት ሂደት በዋናነት ክስና ማስረጃ ማቅረብ፣ መጥሪያ ማድረስ፣ መልስ እና ማስረጃ መቅረብ፣ ክስ መሰማት እና የክስ መቃወሚያዉ ላይ የመወሰን ተግባሮች ይፈፀማሉ፡፡ ይህ የክርክር ሂደት ክርክሩን ለመምራት ዋና መሰረት የሆነዉ ነዉ፡፡ የክርክሩ አቅጣጫ የሚወሰነዉም በዚህ የክርክር ደረጃ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ነዉ፡፡ ክርክሩን ግልፅ እና አጭር በሆነ ሂደት ለመፈፀም የሚያስችለዉም የቅድመ ሙግት ሂደቱ ጤናማ መሆን ከቻለ ነዉ፡፡

ክርክሩ ሳይንዛዛ እንዲያልቅ ከተፈለገ በቅደመ ሙግት ሂደት መከናወን ያለባቸዉ ነገሮች ሁሉ ጥንቅቅ ብለዉ መከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ክርክሩ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ከተፈለገም በቅድመ ሙግት ሂድት የሚከናወነዉ መጥሪያ አደራረስ ሰርዓት በተገቢዉ መንገድ መፈፀም ይኖርበታል፡፡ ከሙግት በፊት በዳኛዉ ሆነ በሬጅስትራር ሊከናወኑ የሚገቡ ብዙ ጉዳዮች ያሉ ቢሆንም ለዚህ ጽኁፍ ዓላማ ሲባል ሶስት ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት ይደረጋል፡፡ የመጀመሪያዉ ክስ እና መልስ ሲቀርብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 145 መሰረት እንዲቀርብ የሚጠየቀዉን ማስረጃ ይመለከታል፡፡ ሁለተኛዉ መልስ በሬጅስትራር የማቀባበል ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ ሶስተኛዉ ክስ ከመስማት ጋር በተገናኘ መቃወሚያ እና ፍሬ ነገር ክርክሮች የሚደረጉበት ሁኔታ ይመለከታል፡፡ ይህ ጽሑፍም ሶስቱን ጉዳዮች በሕግ ያላቸዉን ማዕቀፍ እና ተግባራዊ አፈፃፀማቸዉን በመዳሰስ ከሥነ-ሥርዓት ሕጉ ዓላማ አንፃር ለክርክር ፍጥነት፣ ግልፅነት እና ፍትሐዊነት ያላቸዉን አስተዋጽዖ ይዳስሳል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog/pre-trial-proceedings
2.1K viewsLiku Worku, 11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 12:03:01 ባልና ሚስት በባህል ተጋብተው በ 1989 አመተ ምህረት አንዲት ሊጅ ወልደው ተፋትተዋል። ሚስት ልጇን ብቻዋን አሳድጋለች፤ ባልም ሌላ ትዳር መስርቶ ልጆችን አፍርቷል። እናት ልጇን ስታሳድግ በጥረቷ ንብረት አፍርታ ቤትም ሰርታለጭ። በ 2008 አመተ ምህረት ይህ ሰው ያኛዉን ትዳሩን አፍርሶ እና በጠና ታሞ ከመጀመሪያ ባለቤቱ ጋ እርዳታሽን እፈልጋለሁ በማለት ከቤቷ ይገባል፤ የጋራ ልጅ ስለነበረቻቸዉ በርህራሄ ያስጠጉትና አስታመዉት ከዳነ በኋላ አብረው ሲኖሩ ሶስት አመታትን አሳለፉ። እናም አባት ሁልጊዜ ከቤቱ ባለኩል አድርጊኝ የሚል ጥያቄ ያቀርብላት፤ እሷም ባለመስማማት ትመልሰው ነበር። ቆይተዉ ትርፍ ቦታ ስለነበረዉ ጥቂት ዶርሞችን አብረዉ እያሉ ሰርተዋል። ሁልጊዜ ባለ እኩል ካላደረግሽኝ እያለ ፤ ካልተስማምሽም እያለ ያስፈራራትም ነበር። ከዚህ በኋላ ጥያቄዉን አልቀበለዉ ስትል፤ ከእርሷ እዉቅና ዉጪ የራሱ የሆኑ ሰወችን ይዞ ፤ ገንዘብ እንዳጋባላት እና ከቤቱ ባለቤትነት እንዳስገባችዉ የሚገልጽ ዉል ጽፎ እነዚያን ሰወች ከቤት ይዞ በመምጣት እንድትፈርምለት ይጠይቃታል። ነገር ግን በሃሳቡ ባለመስማማቷ ሳትፈርም ቀረጭ። በዚህ የተናደደዉ ሰዉየዉ ሌሊት በ ተተኳሽ መሳሪያ ያስፈራራታል። ከዚያም ቤቷን ጥላ ወደቤተሰቦቿ ትሄዳለች። ከዚያም የቤት እቃዉን ሁሉ አዉጥቶ ከወሰደ በኋላ ክስ ይመሰርትባታል። ክሱም እሱ በሌለበት ቤቱን እንደዘረፈችዉ ያስረዳል።
አሁን አብረው ያፈሩትን ሃብት ሳይቆጥር ጥራ ግራ የሰርችዉን ቤት እኩል ታካፍለኝ ብሎ ከሷት ይገኛል።
ከሙያ አንጻር የሆነ ነገር በሉኝ።
በዚህ ጉዳይ ጥብቅና የሚቆምልኝም ሰው እፈልጋለሁ!
አመሰግናለሁ
https://www.abyssinialaw.com/discussions/2022-11-12-14-03-47
3.1K viewsLiku Worku, 09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:07:21 ባልና ሚስት ስለግል ንብረቶቻቸው አስመልክቶ የሚያደርጉት ስምምነት በፍርድ ቤት ከጸደቀ በኋላ ሦስተኛ ወገን ስምምነቱን እቃወማለሁ በማለት ስምምነቱን ባጸደቀው ፍርድ ቤት አቤቱታ ሊያቀርብ እና ሊስተናገድ ይችላል ወይ? ፍርድ ቤቱስ ከባል ወይም ከሚስት ውጪ ስምምነቱን እቃወማለሁ ብሎ የሚመጣን አመልካች ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችለው ሥነ-ሥርዓት አለ ወይ?

https://www.abyssinialaw.com/discussions/2022-11-12-10-57-00
1.4K viewsLiku Worku, 11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 12:17:14 የወራሽነት ማረጋገጫ፣ መቃወሚያ እና ልጅነት፡- ክፍተተ ወሕግ ወአሰራር እና መፍትሔዎቻቸው
ፈቃዱ ዳመነ - ጠበቃ

በዚህ ጽሑፍ ወራሽ ለመሆን ወይም ልጅ መሆንን ለማረጋገጥ ስለሚሰጡ ማረጋገጫዎች እንዲሁም እነዚህን ማረጋገጫዎች ስለመቃወም የሚቀርቡ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ጸሐፊው በጽሑፍ በወራሽነት ማረጋገጫ፥ ልጅነት እና መቃወሚያ ያሉ የሕግ እና የአሠራር ክፍተቶችን በማሳያት የመፍትሔ ሐሳቦችን ይሰነዝራል።

መልካም ንባብ!
https://www.abyssinialaw.com/blog/2022-11-11-16-44-28
1.8K viewsLiku Worku, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 17:17:54 We think it’s essential for every business to evolve and develop its branding to ensure they remain relevant while maintaining a consistent and familiar identity.:D :D :D
Abyssinialaw.com is no different, and last week we launched our shiny new look brand and website! If you’re reading this, you’re already on our new website and enjoying our clean, modern, and contemporary new look.

We’ve always had great feedback on our website, with people saying it represents our culture, work, and ethos of “keeping it simple.”

We hope you like our new website and that you find it clear and straightforward to navigate and easy to find what you are looking for.

As with all websites, it’s not quite finished yet, and we’ve got improvements and additional functionality to add. But in the meantime, have a poke around and give us your feedback.

New blog

now you can control all your posts and your profiles. You can also submit your article online without the need to send it to the admin. All you need to do is login and navigate to your profile.

New Discussion Forum

You may now post any questions or suggestions you have.

Enjoy
https://www.abyssinialaw.com/discussions/give-us-your-feedback-on-our-new-look-website
2.9K viewsLiku Worku, 14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 12:44:44 ክስ ስታቀርብ ክሱን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92 ማረጋገጥ ከረሳህና በሬጅስትራርም ሳይታረም መዝገቡ ለችሎት ከቀረበ ፍርድ ቤቱ ስነ-ስርዓት አላሟላም በሚል መዝገቡን ይዘጋዋል። ቀጥሎ ያለው መፍትሔ ሌላ ክስ ማቅረብ ነው። አዲሱ ክስ ደግሞ የይርጋ ጊዜን አያቋርጥም።

በ ሰ/መ/ቁ. 123123 ቅጽ 21 በተሰጠ የህግ ትርጉም ከሳሽ ያቀረበው ክስ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 92 የተደነገገውን አስገዳጅ መስፈርት የማያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መዝገቡ ከተዘጋ ምንም አይነት ክስ እንዳልቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዜ የማቋረጥ ውጤት የሌለው ነው። @Elias K. Law Room

የሰ/መ/ቁ 123123 - በክስ አቀራረብ ሥርዓት ላይ ጉድለት ያለበት መሆኑ ተረጋግጦ የተዘጋ መዝገብ ምንም አይነት ክስ እንዳልቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዜ የማቋረጥ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 278 (2) (ሀ) እና (3)
http://negari.abyssinialaw.com/judgments?id=2731
5.1K viewsLiku Worku, edited  09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 17:27:38 የውርስ ኃብት ማጣራትን የተመለከቱ አንዳንድ ነጥቦች ከሰበር ውሳኔ ጋር ተገናዝቦ የቀረበ
በ፡ ሙሉቀን ሰይድ

የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የተለየ ንብረት ይቆጠራል፡፡ ይህም ማለት የሟች ንብረት ከሌሎች ሰዎች ወይም ወራሾች ንብረት ጋር ሳይቀላቀል የባለቤትነት መብቱ ለወራሾች ሳይተላለፍ እንደ አንድ ልዩ ንብረት ሆኖ ሊያዝ እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 942 ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ የሟች የውርስ ሀብት ወደ ወራሾች ይተላለፍ ዘንድ እንዲሁም ከሟች የውርስ ሀብት ላይ እዳ ጠያቂ ወይም ለሟች እዳ ከፋይ ነን የሚሉ ወገኖች የየፍላጎታቸው እንዲፈጸም፤ የሟች ወራሾች ማንነታቸው እና የሚደርሳቸው ምጣኔ ድርሻ ይታወቅ ዘንድ፤ሟች ኑዛዜ የተናዘዙ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የውርስ ሀብቱ ሊጣራ የሚገባው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 946 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ ተመላክቶ ይገኛል፡፡

ይህ የውርስ ማጣራት ተግባር በምን አግባብ እንደሚከናወን፤ የውርስ አጣሪው ስልጣንና ኃላፊነት እስከምን ድረስ አንደሆነ፤ የውርስ ኃብት ላይጣራ ሚችልባቸው ሁኔታዎች፤ የውርስ አጣሪ ሪፖርትን በማጽደቅ በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ህጋዊ ውጤቱ እስከምን ድረስ እንደሆነና በዚህ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ ተቃውሞ በምን መልኩ ሊቀርብ እንደሚገባ በዚህ ጽሁፍ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ውሳኔዎች ጋር በማገናዘብ አጭር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog/liquidation-process-in-ethiopia
4.9K viewsLiku Worku, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 14:27:42 ከውርስ ኃብት ክፍፍል ጋር የተያያዙ አንዳንድ ነጥቦች ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከሰጣቸው ውሰኔዎች ጋር በማገናዘብ የቀረበ

በ፡ ሙሉቀን ሰይድ

የሟች የውርስ ኃብት ተጣርቶ ከተዘጋ በኋላ የውርስ ኃብት ባለቤትነት ወደ ሟች ወራሾች ይተላለፋል፡፡ በመሆኑም ውርስ ከተዘጋ በኋላ ወራሾች መሀከል ክፍያ እስኪፈጸም ድረስ የሟች ወራሾች በሀብቱ ላይ ያላቸው መብት ምንድነው? ክፍፍሉ ከመፈጸሙ በፊት በጋራ ወራሾች የተያዘ ንብረት በአንደኛው ወራሽ ብቻ ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ቢተላለፍ ፈቃዳቸውን ያልሰጡ ወራሾች መብታቸው እስከምን ድረስ ነው? ገዥውን ያለውስ መብት ምንድነው? የውርስ ሀብት ክፍፍል የሚደረግባቸው ስነ-ስርዓቶችንና ክፍፍል ከተደረገ በኋላ የሚገኙ የውርስ ኃብት የሆኑ ንብረቶች ለወራሾች ሊከፋፈሉ የሚችሉባቸው የህግ ስርዓቶችን በተመለከተ በወራሾችና ወራሽ ባልሆኑ ሶስተኛ ወገኖች መሀከል እስከ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የደረሱ አከራካሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዚህ ጽሁፍ እነዚህን ነጥቦች በተመለከተ ከፍትሐብሔር ሕጉና ከተመረጡና አስገዳጅ ከሆኑ የሰበር ውሳኔዎች አንጻር አጭር ዳሰሳ ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog/some-points-related-to-the-distribution-of-inheritance
6.5K viewsLiku Worku, 11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:23:08
2.9K viewsLiku Worku, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ