2023-01-07 22:56:18
ከወላጆቻችን ጋር
– እነርሱ ባሉበት ከራሳችንም ከማንም ማስቀደም
– በሚወዱት ስም መጥራት
– ከእነርሱ ጋር ስናወራ ጥሩ ቃላት መርጦ መጠቀም
– በእነርሱ ላይ አለመቆጣት ደጋግሞ መዘየር
– ሳያዙን በፊት የሚፈልጉትን ማቅረብ
– አጠገባቸው አለመበሳጨት
– ሁል ጊዜ ለእነርሱ ዱዓእ ማድረግ በእዝነት አይንም ማየት
– የሌላን ወላጅ በመስደብ ለእነርሱ መሰደብ ምክንያት አለመሆን
– ጀርባ አለመስጠት እግር ወደእነርሱ አለመዘርጋት
– የኔ ወላጆች ብለህ ክብራቸውን ማውራት
– አይንህን በእነርሱ ላይ አለማፍጠጥ
– ከፊት ለፊታቸው አለመሄድ
– እነርሱ ሳይበሉ ቀድመህ አለመብላት
– አጠገባቸው ድምፅን ከፍ አለማድረግ
– ምክራቸውን መቀበል
– ሲናገሩ መልስ አለመስጠት
– ልጆችህን በፊታቸው አለመቅጣት
– ሲናገሩ ንግግራቸውን አለማቋረጥ
– ሀሳባቸውን ዝቅ አለማድረግ
– እነርሱ አጠገብ አለማንሾኳሾክ
– አብረህ ስትቀመጥ ደረጃቸውን መጠበቅ
– ንግግራቸውን ማዳመጥ
– መልካም ስራቸውን ማውሳት ጥፋታቸውን መርሳት
– ጓደኞቻቸውን ማወደስ
– መጥፎ ወሬ አለማሰማት
– የሚያስደስት ወሬ መንገር
– ትንሽ ነው ሳይባል ስጦታ መስጠት
– እነርሱ አጠገብ ስትቀርብ አዋቂ መስለህ አለመቅረብ
– በትህትናና በአክብሮት ማናገር
– የሚወዱትን የምግብ አይነት ማብላት
– አላህን በማመፅ ካልሆን ትእዛዛቸውን መቀበል
– ሀሳባቸውን ሳታቋርጥ ማዳመጥ
– ሁሌም ለእነርሱ ዱዓእ ማድረግ
– አኼራቸውን የሚያጠፋን ነገር በእርጋታና በመልካም አንደበት ጭንቀትን ሊረዱ በሚችሉበት መልኩ መንገር
– ለእነርሱ ፍፁም ትሁት መሆን
– ፍላጎታቸውን ማስቀደም
– ስለአኼራቸው ማስታወስ
– መጨረሻቸው እንዲያምር አላህን መለመን
አላህ ከወላጆቻችን ሐቅ ይጠብቀን ።
https://t.me/bahruteka
171 views19:56